Get Mystery Box with random crypto!

የላሊበላ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት ወቅታዊ ሁኔታን መነሻ በማድረግ የሰዓት ዕላፊ ገደብን ጨምሮ ሌሎ | 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የላሊበላ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት ወቅታዊ ሁኔታን መነሻ በማድረግ የሰዓት ዕላፊ ገደብን ጨምሮ ሌሎች ውሳኔዎችን አሳልፏል

ውሳኔዎቹ ፦

ከምሽቱ 1:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ወደ ከተማዋ መግባትም ሆነ መውጣት አይቻልም።

ማንኛውም ተሽከርካሪ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት በኋላ እስከ ንጋቱ 12:00  ድረስ መንቀሳቀስ አይቻልም።

ከተፈቀደለት አካል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።

በመንግስት ዕውቅና ካለው የፀጥታ አካል ውጭ የፀጥታ አካላትን የደንብ ልብስ ለብሶ መንቀሳቀስ በፍፁም አይቻልም።

የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ህዝቡ በሀሰተኛ ወሬ እና አሉባልታ ሳይደናገር አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላልፏል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01