#የዘላለም_ሕይወት_ዋስትና (አለመጥፋት) ክፍል ሁለት #The_doctrine_of_eternal_security part two ========(#Small sized audio) #በወንድም_ሀብታሙ_አዲሱ ዋነኛው የአዲስ ኪዳን ትምህርት መሠረት የአንድ አማኝ ደኀንነት የሚያገለግለው ለዘለዓለም መሆኑን ማብሰር ነው።#ዮሐ3:15-18,36፣5:24 ይህ ደኀንነት በአማኙ መልካምነት እና ብርታት ላይ የተመሰረተ አይደለም። ኤፌ 2፡8-9 ማንም አማኝ ዳግመኛ የተወለደው ኃጢአትን ላለማድረግና በጽድቅ ለመኖር ቢሆንም በዚህ ምድራዊ ተፈጥሮ ኃጢያትን ባለማድረ መቀጠል የሚችል አይሆንም ፣ ይህም ሲባል እውነተኛ ክርስቲያን በፀጋ የዳነ ከሆነ በሐጥያት የመቀጠል መብት አለው ማለት አይደለም ይልቅስ የእግዚአብሔር ፀጋ ሃጢያተኝነትን እና አለማዊ ምኞትን ያስክዳል። #ቲቶ 2፡11-14 ክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለ ኀጢአት በመሞት የሰጠን የዘላለም ህይወት እኛ #በድካማችን #ተሣሥተንም ሆነ #አውቀን ስንበድል ከእኛ የሚወሰድና እኛን ለዘላለም ሞት የሚዳርገን አይደለም፡፡#1ኛጴጥ1:23. 1 ጴጥሮስ 1 :23፤ ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ። የወንጌል እውነት አገልግሎት ጅማ Gospel Truth Ministry Jimma. @DawitFassilMinistry 181 viewsDave, 14:40