Get Mystery Box with random crypto!

     @wayandtruth                    የእምነታችን መሰረት እምነታችሁም በእ | መንገድና እውነት

     @wayandtruth

                   የእምነታችን መሰረት
እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 : 4-5

መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ የተሰበከ ወንጌልና የሚሰበክ ወንጌል ተፅዕኖው ከፍ ያለና እውነተኛ ነው። ወንጌል ንግግር ሳይሆን የክርስቶስ የማዳኑና የሃይሉ እንዲሁም የትንሳኤው ብስራት ነው።
ብዙ ሰዎች እምነታቸውን ተረት ተረት ላይ፣የታዋቂ ሰዎች ንግግርና ሃይል አልባ በሆነ አባባል ላይ ሲመሰርቱ ማየት የተለመደ ነው።ብዙ ሰዎች ወንጌልን ከንግግር የዘለለ መልዕክት እንደሆነ አይረዱም።

እንደ ክርስትያን እምነታችን በክርስቶስ የትንሳኤ ኃይል መመስረቱን መገንዘብ ይገባል።የተመሰረታችሁበት መሰረት ወይም የተሰበከላችሁ ወንጌል ኃይል አልባ ከሆነ ቆም ብላችሁ እምነታችሁን መርምሩ።

ወንጌል በሙሉ ሃይልና ስልጣን የሚሰበክ የእግዚአብሔር አጀንዳ ነው። ክርስትና ደግሞ በትንሳኤው ኃይል የምትኖሩበት ድል አድራጊ ህይወት ነው።

ክርስትና በሞት ላይ፣በእርግማን ላይ በበሽታ ላይ እና በየትኛውም የሲኦል መሳሪያ ሁሉ ላይ የበላይነት መቀዳጀት ነው።እውነተኛ ክርስትያናዊ እምነት የትንሳኤን ኃይል አምኖ መዳን ነው። የዳናችሁት በሚያባብል በጥበብ ቃል እንዳልሆነ ተረዱ።
በክርስቶስ ስታምኑ ወደ አስደናቂ መንግስት ተጠርታችኋል።ጌታ ላይ ያላችሁ እምነታችሁ ዘላለማዊ ታሪካችሁን የለወጠ ነው።

መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ የሰማችሁት ወንጌልና የሚያባብለው ወንጌል ልዩነት አላቸው።የሚያባብለው ወንጌል ብታምኑትም ባታምኑትም ለውጥ የማያመጣ የሰው ጥበብ ውጤት ነው።ይህ ማባበያ ኃይል አልባ ነው።ምንም ተአምራታዊና መለኮታዊ ይዘት የለውም።ይህ አባባይ ወንጌል የሃይማኖት መልክ ያለው ነው። ነገር ግን ኃይሉን የካደ ነው።አያድንም፣
አይፈውስም፣አያስመልጥም፣አያሻግርም። ይህ አባባይ ወንጌል በጥሩ ቋንቋ ብቻ ያሸበረቀ ነው።

በዚህም ዘመን ሁለት አይነት ሰዎች አሉ።
1ኛ በኃይል የተሞላውን ወንጌል የተቀበሉና የሚሰብኩ 
2ኛ የሚያባብል ወንጌል የተቀበሉና የሚሰብኩ ሰዎች ናቸው።
ወንጌል ከተሰበከ በኋላ የሃይልና የመንፈስ መገለጥ ከሌለ የተሰበከው ወንጌል መፈተሽ አለበት።

በሀይልና መንፈስን በመግለጥ ያልተሰበከ ወንጌል በኃይል የተሞላ ትውልድ አያፈራም።ይህ ማለት በፈውስ ላይ፣በአጋንንት ላይ እና በሌሎች የህይወት ጉዳዮች ላይ ኃይል የለሽ ትውልድ ያፈራል ማለት ነው።

ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1 : 20-28
@wayandtruth
@wayandtruth
@wayandtruth