2024-05-12 09:30:03
አዲስ አበባ
ጎሮ አካባቢ በተከሰተ የእሳት አደጋ 13 የንግድ ሱቆችና በጋራዥ ዉስጥ የነበሩ አምስት ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደሙ።
ትናንት ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት 6:50 በለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ገብርዔል ቤተክርስቲያን አጠገብ የተነሳዉ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
በእሳት አደጋዉ በቤተክርስቲን ዙሪያ ያሉ 13 የንግድ ሱቆችና በጋራዥ ዉስጥ የነበሩ አምስት ተሽከርካሪዎች ሙሉ ሙሉ የወደሙ እና በጋራዡ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 12 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች 66 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተሰማሩ ሲሆን የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠርም 4 :10 ሰዓት መፍጀቱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል።
15 ተሽከርካሪዎችን ከቃጠለው ማትረፍ መቻሉንና በአደጋዉ በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አልመድረሱን አቶ ንጋቱ ጨምረው ተናግረዋል።
በጋራዡ ውስጥ የነበሩ ተሽከርካሪዎች የያዙት ነዳጅና ሌሎች ፈሳሽ ተቀጣጣዮች እንዲሁም ንግድ ሱቆቹ እሳትን ሊቋቋሙ ከማይችሉ ቆርቆሮና መሰል ግብዓቶች መገንባታቸዉ ለእሳቱ መባባስ አስተዋጾኦ ማድረጉን አቶ ንጋቱ ተናግረዋል።
የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት የሚሰጡ ጋራዦች ደረጃቸዉን በጠበቁ ግብዓቶች የተገነቡና ከንግድ ሱቆች ከመኖሪያ አካባቢዎች የራቁ መሆን እንዳለበት ኮሚሽኑ አስጠንቅቋል።የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ እያጣራ ይገኛል።
መረጃው ከብስራት ሬዲዬና ቴሌቪዥን የተወሰደ ነው።
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
14.6K viewsW M, 06:30