Get Mystery Box with random crypto!

Wasu Mohammed-ዋሱ መሀመድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ wassulife — Wasu Mohammed-ዋሱ መሀመድ W
የቴሌግራም ቻናል አርማ wassulife — Wasu Mohammed-ዋሱ መሀመድ
የሰርጥ አድራሻ: @wassulife
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.21K
የሰርጥ መግለጫ

ትኩስና ወቅታዊ መረጃዎች ብቻ የሚቀርቡበት!

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-03-03 07:00:27
አሳፋሪ ጥቁር ታሪክ በታሪክ ይመዘገባል!

ወያኔ ቤተክርስቲያን የተጠለለ ህዝብ ላይ አስለቃሽ ጭስ የወረወረበት ዘመን የለም። በብልፅግና ዘመን የተፈፀመ ጥቁርር ታሪክ!!
ይሄ አለም በቃኝ ብለው የዚህን አለም ቆሻሻነት ንቀው በምንኩስና ውስጥ ያሉና ቤተክርስቲያኗን የሚያገለግሉ ቢጫ ለብሰው አለምን የናቁ ደናግላንና መነኮሳትም በአስለቃሽ ጭስና በድብደባው ክፉኛ ተጎድተው ራሳቸውን ስተው ወድቀው ይታያሉ!!!
ኧረ ምን አይነት ቆሻሻ ስርዓት ነው????

====≡=============≡=====
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ያለገደብ ለማግኘት ፈጥነው ከታች ያለውን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ፣ አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎች ሼር ያድርጉ መረጃ ህይወት ነው።

http://t.me/wassulife
http://t.me/wassulife
754 views04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 06:46:57 የልባችን እድሜ ከእኛ ቀደሞ እያረጀ ይሆን፤ እንዴትስ ማወቅ እንችላለን?

ጤናማ አመጋገብን መከተል፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግና ከአጉል ሱሶች መራቅ ልባችን ቀድሞን እንዳያረጅ ያደርጋሉ ተብሏል
ልባችን ከእድሜያችን በላይ ሊያረጅ እንደሚችል ያውቃሉ?
የልባችን እድሜ ለልብ ህመም እና ስትሮክ የመጋለጥ እድላችን ይጠቁማል ይላሉ ባለሙያዎች።
ልባችን ከእኛ ቀድሞ የሚያረጀው በተለያዩ ምክንያቶች ቢሆንም ጾታ፣ ክብደት እና የደም ግፊት መጠንን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቤታችን ውስጥ የምናውቅበት የልብ እድሜ ማስያ (ካልኩሌተር) አለ።

የልብ እድሜ ማስያው የሚሰጠን ጠቅለል ያለ መረጃ መሆኑ ግን አጠራጣሪ ነገሮችን ስንመለከት የህክምና ባለሙያዎችን ማማከር ያስገድዳል።
ከዚህ በታች የተዘዘዘሩት ጉዳዮችም ልባችን ከእና ቀድመው እንዲያረጁ የሚያደርጉ ናቸውና አስቀድመን ጥንቃቄ ማድረግ ይበጃል።

1. ጭንቀት

ልብን በፍጥነት ከሚያስረጁ ምክንያቶች ቀዳሚው ጭንቀት መሆኑን ጆን ሆፕኪንስ ያወጣው ጥናት ያሳያል። ጭቅጭቅ የበዛበት ትዳር ውስጥ ያሉ እና ፍቺ የተደጋገመባቸው ሰዎች ለልብ ህመም የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ መሆኑንም ነው ጥናቱ ያመላከተው። በጭንቀት ጊዜ ሰውነታችን የሚለቃቸው ኬሚካሎች የደም ግፊት እና የመጥፎ ኮሊስትሮል መጠን እንዲጨምር ማድረጉም የልብ ጤናን እንዲያውክ ያደርገዋል።

2. ጨውና ስኳር የበዛባቸው ምግቦች

የተቀነባበሩ፣ ጨውና ስኳር የበዛባቸውን ምግቦች ማዘውተርም የደም ግፊትን ጨምሮ ለልባችንም እርጅናን ያስከትላል ነው የተባለው። በመሆኑም አትክልትና ፍራፍሬዎችን፣ እንደ አሳ ያሉ የፕሮቲንን ይዘታቸው ከፍ ያሉ ምግቦችን ከማዕዳችን እንዳይጠፉ ማድረግን ባለሙያዎች ይመክራሉ።

3. የእንቅልፍ እጦት

በቂ የእንቅልፍ ጊዜ ማጣትም የደም ዝውውርን በማፍጠን በልብ ላይ ከፍተኛ ጫናን ያሳድራል። ይህም የልብ ጤናን በረጅም ጊዜ ክፉኛ የሚጎዳው ሲሆን ልባችን ያለጊዜው ያስረጀዋል ይላል የሲ ዲ ሲ ጥናት።

4. የደም ግፊት

የአሜሪካው የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል (ሲ ዲ ሲ) የልብ እርጅና እና የደም ግፊት ጥብቅ ትስስር አላቸው ይላል። የአንዲት እድሜዋ 53 የሆነች እንስት የልብ እድሜ ሲለካ 75 አመት መድረሱን እንደአብነት በማንሳትም የሴትዮዋ የደም ግፊት ከፍተኛ መሆኑ ለልቧ ቀድሟት ማርጀት ዋናው ምክንያት መሆኑን ይጠቅሳል። ወጣቶች የደም ግፊታቸው ንባብ ከ120/80 እንዳይበልጥ የአኗኗር ዘይቤያቸውን ካስተካከሉ ከልብ ጋር የተያያዙ ችግሮችን በብዙ እጥፍ መቀነስ እንደሚችሉም ሲ ዲ ሲ ገልጿል።

5. አካላዊ እንቅስቃሴ አለማድረግ

ማዮ ክሊኒክ በ2019 ባደረገው ጥናት የልብ እርጅናን ለመቀነስ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ትልቅ ድርሻ እንዳለው አመላክቷል። በወር ውስጥ ለ150 ደቂቃዎች የአካል እንቅስቃሴ ማድረግንም የልብ ጤናን ለመጠበቅ ወሳኝ ነው በሚል ይመክራል።

6. ሲጋራ ማጨስ

“ሲጋራ ማጨስ ሳንባን ብቻ ይጎዳል ብላችሁ የምታስቡ ተሳስታችኋል” ሲ ዲ ሲ፥ ማጨስ የልብ ጤና ጸር መሆኑን ይገልጻል። በሲጋራ ውስጥ የሚገኙ ኪሚካሎች የደም መርጋትን በማስከተል በልብ ላይ ጫና እንደሚፈጥሩ በጥናት ተረጋግጧል። እናም ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ልባቸው ከእድሜያቸው በፊት ከማርጀቱ በፊት ማጨስ ያቁሙ ሲልም ያሳስባል ሲ ዲ ሲ።

7. ከፍተኛ ኮሌስትሮል

የመጥፎ ኮሌስትሮል ክምችትም የልብ ጤናንም ሆነ እድሜ ከሚወስኑ ነገሮች አንዱ ነው። በመሆኑም ከፍተኛ የስብ ክምችት ያላቸውን ምግቦች አለማዘውተር ተገቢ ነው ይላሉ ባለሙያዎች።
በአጠቃላይ ጤናማ አመጋገብን መከተል፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግና ከአጉል ሱሶች መራቅ ልባችን ቀድሞን እንዳያረጅ ያደርጋሉ ተብሏል።
====≡=============≡=====
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ያለገደብ ለማግኘት ፈጥነው ከታች ያለውን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ፣ አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎች ሼር ያድርጉ መረጃ ህይወት ነው።

http://t.me/wassulife
http://t.me/wassulife
663 viewsedited  03:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 06:46:52
523 views03:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 06:45:03
በዛሬዋ ቀን ምኒልክ አደባባይ እንደሄደ የጥቁር ጣሊያኖች (ባንዳዎች) ሰለባ የሆነው ወንድማችን መኳንንት ወዳጅ (ሚሊዮን) ይሄ ነው። በዳግማዊ ምኒልክ መሰናዶ ትምህርት ቤት የፊዚክስ መምህር ነበር።ለቤተሰቦቹና ለጓደኞቹ መፅናናትን እንመኛለን።
====≡=============≡=====
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ያለገደብ ለማግኘት ፈጥነው ከታች ያለውን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ፣ አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎች ሼር ያድርጉ መረጃ ህይወት ነው።

http://t.me/wassulife
http://t.me/wassulife
526 viewsedited  03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 06:43:02
በራያ ግንባር የህውሃት ታጣቂዎች ትንኮሳ ለመጀመር መዘጋጀታቸው ታውቋል።ሂደቱን ለመመከት የአማራ ክልል በቂ ዝግጅት እንዳደረገም ተሰምቷል።ከፕሪቶሪያው በኋላ አዲሱ ጦርነት ብዙዎችን ግራ አጋብቷል።
====≡=============≡=====
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ያለገደብ ለማግኘት ፈጥነው ከታች ያለውን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ፣ አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎች ሼር ያድርጉ መረጃ ህይወት ነው።

http://t.me/wassulife
http://t.me/wassulife
486 viewsedited  03:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 22:06:02 አሳዛኝ ዜና

በዳግማዊ አጼ ምኒልክ መሰናዶ ት/ቤት የፊዚክስ መምህር የነበረው መምህር መኳንንት ወዳጅ በዛሬው እለት በሰላማዊ ዜጎች ላይ ያለምንም በቂ ምክንያት በተከፈተው አሰቃቂ ጥቃት ሕይወቱ አልፏል!!

ለመምህር መኳንንት ወዳጅ ቤተሰቦች ፣ ለዳግማዊ ምኒልክ መሰናዶ ት/ቤት መምህራን ተማሪዎች እና የት/ቤቱ ማኅበረሰብ እንዲሁም ላዘኑ ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን።

ጣሊያንን ድል ባደረግንበት የድል በዓል መታሰቢያ ከባርነት ነጻ ያልወጡ ጥቁር ጣልያኖች በገዛ ሀገራችን ነጻነታችንን ሲገፉት ያየንባትን ይህችን ቀን ግን ከቶ አንረሳትም!

Via Reporter Et
====≡=============≡=====
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ያለገደብ ለማግኘት ፈጥነው ከታች ያለውን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ፣ አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎች ሼር ያድርጉ መረጃ ህይወት ነው።

http://t.me/wassulife
http://t.me/wassulife
517 viewsedited  19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 21:58:27
ዛሬ በአዲስ አበባ በዳግማዊ አጼ ምኒሊክ አደባባይ የተከናወነውን የታላቁ አድዋ ድል አከባበር "ለመረበሽ የፈለጉ አካላት ሁከት ለመቀስቀስ ሞክረው ነበር" ሲል ማምሻውን የመንግስት ኮምንኬሽን ጽሕፈት አስታውቋል።ጸጥታ ኃይሎች ድርጊቱን ለመከላከል ሲሞክሩ "በጥቂት ምዕመናን ላይ ጉዳት ደርሷል"በማለትም ሂደቱን ገልፆታል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በበኩሉ"…ታቦታተ ሕጉ ከመንበረ ክብራቸው  ወጥተው የዑደት ሥነ ሥርዓት ከተፈጸመ በኋላ ክብረ በዓሉ እየተከናወነ ባለበት ወቅት ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ወደ ቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ በተወረወረ አስለቃሽ ጭስ የበዓሉ ሥነ-ሥርዓት ሳይጠነቀቅ ታቦታተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብራቸው ተመልሰዋል።ወደቅጽረ ቤተክርስቲያኑ በሚያስገቡ ሁለቱም መግቢያ በሮች በተወረወረው አስለቃሽ ጭስ በርካታ ምዕመናን በመጎዳታቸው ራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።>> በማለት ገልፀዋል።
====≡=============≡=====
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ያለገደብ ለማግኘት ፈጥነው ከታች ያለውን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ፣ አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎች ሼር ያድርጉ መረጃ ህይወት ነው።

http://t.me/wassulife
http://t.me/wassulife
521 views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 08:37:29 የማስታወስ ችሎታን የሚጨምሩ ምግቦች

በቫይታሚን የበለጸጉ ምግቦችን የየእለት ማዕዳችን አካል ማድረግና አትክልትና ፍራፍሪዎችን ማዘውተር ለአዕምሮ ጤና ወሳኝ ድርሻ አለው ተብሏል
አዕምሯችን ለማሰብና ለማንሰላሰል ከፍተኛ ሃይል ይጠቀማል።
በየቀኑ ከምናቃጥለው ካሎሪ 20 በመቶውን አዕምሯችን እንደሚጠቀም ጥናቶች ያሳያሉ።
ማንኛውም አይነት ምግብ ግን ለአዕምሯችን ጤናም ሆነ ለማስታወስ ችሎታችን ይረዳል ማለት እንዳልሆነም ነው ጥናቶች የሚጥቁሙት።
በንጥረ ነገር የበለጸጉ ምግቦችን መውሰድ ብቻም አዕምሯችን ደስተኛና ጤናማ እንደማያደርገው ይነገራል።
አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም አሳ የሚያዘወትሩ ሰዎች የጤናማ አዕምሮ ባለቤት መሆናቸው ተረጋግጧል።

እነዚህ ምግቦች የደም ግፊትን ስለሚቆጣጠሩ ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚገጥሙ የመርሳት ችግሮችን ለማስውአገድ እንደሚያግዙም ነው የሚነገረው።
ከዚህ በታች የተዘረዝሩት ምግቦችም የአዕምሮን ጤና በማስተካከል የመርሳት በሽታን ለመከላከል ወሳኝ ድርሻ እንዳላቸው ጥናቶች አመላክተዋል።

1. ጎመን

አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው አትክልቶች በቫይታሚን ኬ፣ ፎሊክ አሲድ፣ ቤታ ካሮቲን የበለጸጉ ናቸው። እናም እንደ ጎመን ያሉ አትክልቶች ከገበታ አለመጥፋት ለአዕምሮ ጤና ወሳኝ ነው ተብሏል።
 
2. ለውዝ

ለውዝ ወይም ኦቾሎኒ በፕሮቲን እና ጤናማ ስብ የበለጸገ መሆኑ ለአዕምሮ ምግብነት ተመራጭ ያደርገዋል። የኦሜጋ 3 ክምችቱም ከፍተኛ መሆኑ የመርሳት ችግርን ለመቀነስ አይነተኛ ሚና እንዲጫወት ያደርገዋል።

3. ቲማቲም

በቲማቲም ውስጥ በብዛት የምናገኘው ላይኮፒን ንጥረነገር እንደ አልዛይመር ያሉ የአዕምሮ ጤና ችግሮችን ለማስወገድ ትልቅ ድርሻ አለው። በአንድ መጠነኛ ቲማቲም ውስጥ 3 ነጥብ 2 ግራም ላይኮፒን እንደሚገኝ ጥናቶች ያሳያሉ።

4. የብዕርና አገዳ ሰብሎች

እንደ ስንዴ፣ ገብስ እና ሩዝ ያሉ ሰብሎች በቫይታሚን ኢ የዳበሩ ናቸው። እነዚህን ሰብሎች በፋብሪካ አቀነባብሮ ከመጠቀም ይልቅ ተፈጥሯዊ ይዘታቸውን ሳይለቁ ጥቅም ላይ ማዋል ለአዕምሮ ጤና ወሳኝ ድርሽ ኣእንዳለው ጥናቶች አመላክተዋል። በቀን ውስጥ 48 ግራም ቫይታሚን ኢ ለማግኘትም የማዕዳችን አካል ልናደርጋቸው ይገባል ተብሏል።

5. ብሮኮሊ(የአበባ ጎመን)

ብሮኮሊ በቫይታሚኖች ከመበልጸጉ ባሻገር የካሎሪ መጠኑ ዝቅተኛ ነው። በብሮኮሊ በከፍተኛ መጠን የምናገኘው ግሉኮሲኖላትስ ከውሃ ጋር ሲዋሃድ የሚፈጥረው አይዞቲዮካያንትስ የምግብ ውህደትን በማፋጠን የአዕምሮ ጤናም እንዲጠበቅ ያግዛል።

6. አሳ

በኦሜጋ 3 የበለጸገው አሳ በርካታ የጤና በረከቶች አሉት። በደም ውስጥ የሚገኘውና ለመርሳት በሽታ የሚዳርገው ቤታ አምሎይድ የተሰኘ ፕሮቲን መጠን እንዲቀንስም አሳ መመገብ አይነተኛ ድርሻ አለው ተብሏል። 

7. ቤሪ (ሰማያዊ እንጆሪ፣ አፕል)

በቀን አንድ አፕል መመገብ ዶክተር ለምኔ ያስብላል፤ ቤሪዎችን ማዘውተርም የአዕምሮ ሃኪምን ከመጎብኘት ይታደጋል ነው የሚሉት ጥናቶች። በፍላቮኖይድስ የበለጸጉ ቤሪዎች አዕምሯችን በሚገባ ስራውን እንዲያከናውን የሚያስችሉ ንጥረነገሮችን አከማችተው ይዘዋል። የማስታወስ ችግር እየገጠማቸው የሚገኙ ሰዎች ቢጠቀሟቸው ፈጣን ለውጥ ማየት ይችላሉ ነው የተባለው።

8. ጥቁር ቼኮሌት

ጥቁር ቼኮሌት የያዛቸው የካፌይን፣ ፍላቮኖይድስ እና አንቲኦክሲዳንትስ ለአዕምሮ ጤና ተመራጩ ምግብ ያደርገዋል። ከፍተኛውን የጥቁር ቼኮሌት በረከት ለማግኘትና የስኳር ፍጆታን ለመቀነስ ግን ቀለሙ ከ70 በመቶ በላይ ጥቁር መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

9. እንቁላል

በቫይታሚን ቢ6፣ ቢ12 እና ቢ 9 የዳበረው እንቁላል በፕሮቲን ከመበልጸጉም ባሻገር ለአዕምሮ ጤና ወሳኝ ድርሻ ያላቸውን ንጥረ ነገሮች ይዟል። ጥናቶችም እንቁላልን መመገብ የማስታወስ ችሎታን ለመጨመር እንደሚያግዝ አረጋግጠዋል።

10. እርድ

እርድ ለአዕምሮ ጤና ትልቅ ድርሻ እንዳለው በጥናት የተረጋገጠለትን ከርኩሚን የተሰኘ ንጥረነገር በስፋት ይዟል። ከርኩሚን የአዕምሮ ህዋሳት እድገትን በማፋጠን የመርሳት በሽታ (አልዛይመርን) ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ተብሏል።
====≡=============≡=====
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ያለገደብ ለማግኘት ፈጥነው ከታች ያለውን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ፣ አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎች ሼር ያድርጉ መረጃ ህይወት ነው።

http://t.me/wassulife
http://t.me/wassulife
575 viewsedited  05:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 10:05:00
ለቦረና ወገኖቻችን ድጋፉ ቀጥሏል።

#ዓድዋ_127_ለቦረና

ከዛሬ ጀምሮ አ.አ. ስታዲየም የሚገኘው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበር ታገኙናላችሁ።

~ ሕጋዊ የባንክ ሂሳብ ቁጥር እናሳውቃለን።

~ ተከታዮቹን የእናንተን ልገሳዎች በአይነት መቀበል እንጀምራለን

ለበለጠ መረጃ +251911473071 ይደውሉልን

*የማይበልሹ የምግብ ልገሳ አይነቶች
√ የበቆሎ ዱቄት
√ ፉርኖ ዱቄት
√ ሩዝ
√ መኮረኒ
√ ዘይት

√ የህፃናት የታሸጉ ብትን ወተቶች
√ የሕፃናት አልሚ ምግቦች
√ ብስኩቶች

*የንጽህና መጠበቂያ
√ ሳሙና ደረቅ

#ዓድዋ_127_ለቦረና
#BORENA
#Ethiopia
#Guzo_Adwa
#ቅድሚያ_ለሰብአዊነት
#የሰብአዊ_ድጋፍ_ጥምረት
#የኢትዮጵያ_ቀይ_መስቀል_ማኅበር
Yared Shumete - ያሬድ ሹመቴ
====≡=============≡=====
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ያለገደብ ለማግኘት ፈጥነው ከታች ያለውን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ፣ አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎች ሼር ያድርጉ መረጃ ህይወት ነው።

http://t.me/wassulife
http://t.me/wassulife
628 views07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 10:03:06
በደቡብ ኦሞ ዞን ስር በምትገኘው ሐመር ወረዳ እንደ ሶማሌ እና እንደ ቦረና ሁሉ ለወረዳው ለአርብቶ አደሮች ጊዜው ከፍቷል ተብሏል።

በአየር መዛባት ምክንያት በተከሰተዉ የዝናብ እጥረት የአርብቶ አደሩ የኑሮ መሠረት የሆኑት የቀንድ ከብቶቹ በየጫካና ጥሻዎቹ ውስጥ በተኙበት እየሞቱ ይገኛሉ።
528 views07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ