Get Mystery Box with random crypto!

*** የራሳችንን ሻማ እንለኩስ *** ሁሉም ሰው አነሰም በዛ የራሱ የሆነ ሻማ አለው። ይህ ሻማ | Vision-power Page

*** የራሳችንን ሻማ እንለኩስ ***

ሁሉም ሰው አነሰም በዛ የራሱ የሆነ ሻማ አለው። ይህ ሻማ ሲበራ ለሌሎች ብርሃን ይሆናል። የሁላችን ሻማ ቢበራ ደግሞ የበለጠ ብርሃን ይበራል። ግን ብዙ ጊዜ እኔ ብቻየን ምን ላመጣ እችላለሁ፤ እንዴትስ ለውጥ ማምጣት እችላለሁ፤ … እንላለን።

ከእኔ የሚጠበቀው በእጄ ያለውን ሻማ መለኮስና ለሌሎች ብርሃን መሆን ነው። ምክንያቱም በእጃችን ያለው ሻማ እንዲበራ የሚጠባበቁ በርካታ ሰዎች በዙሪያችን አሉ፤ የእኛን ብርሃን አይተው የራሳቸውን ለማብራት መንገዱን የምንገልጥላቸው ሰዎችም ይኖራሉና፤ ሁላችንም በእጃችን ያለውን ሻማ እናብራ!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!