Get Mystery Box with random crypto!

*** ትልቁ ክብር! *** 'በመኖር ውስጥ ትልቁ ክብር ያለው ባለመውደቃችን ሳይሆን በወደቅን ቁጥ | Vision-power Page

*** ትልቁ ክብር! ***

"በመኖር ውስጥ ትልቁ ክብር ያለው ባለመውደቃችን ሳይሆን በወደቅን ቁጥር መነሳት መቻላችን ላይ ነው።" - ኔልሰን ማንዴላ

በህይወት ጎዳና ብዙ መውደቅ ሊያጋጥም ይችላል። ስኬት ወይም ክብር የሚባለውም በዚህ ጎዳና ላይ ምንም ሳይወድቁ መጓዝ ሳይሆን በወደቅንበት ጊዜ ሁሉ መነሳት እና ያለመታከት ጉዟችንን መቀጠል መቻላችን ነው።

እናም ወዳጄ ሆይ በመውደቅህ አትዘን፤ ይልቁንም ጉዞህ እንዳይቋረጥ ጥረትህን መቀጠሉ ላይ ትኩረትህን አድርግ።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!