Get Mystery Box with random crypto!

*** ያማረ ውሎ! *** ውሏችሁ ያማረ ይሆን ዘንድ የምታደርጉት ምንድነው? ሰዎች ቀናቸውን ያማረ | Vision-power Page

*** ያማረ ውሎ! ***

ውሏችሁ ያማረ ይሆን ዘንድ የምታደርጉት ምንድነው? ሰዎች ቀናቸውን ያማረ ለማድረግ አንዳንዶቹ ፊልም ያያሉ፤ አንዳንዶቹ ሰብሰብ ብለው በመጠጥ ወይም በሌላ ሱስ ያሳልፋሉ፤ አንደንዶቻችን ደግሞ የቴሌቪዥን ፕሮግራም እያማረጥን ደስተኛ ለመሆን እንሞክራለን፤ ይሄ ሁሉ ግን ራሳችንን ከመሸወድ ያለፈ ትርፍ የለውም።

ወዳጄ ሆይ ያማረ ውሎ እንዲኖርህ በቀን ውስጥ ስለምታሳካቸው ጉዳዮችህ አስብ፤ መስራት የሚገባህን በሰዓቱ ተግብር፤ ልታስተናግዳቸው የሚገቡ ሰዎችን አስደስተህ ሸኛቸው፤ በህይወትህ ካቀድከው መካከል አንዷን አከናውን፤ … በቃ አለቀ! ይህንን ካደረግህ ሌላ የሚያዝናና ድራማ፣ ፊልም ወይም ሌላ ነገር ሳያስፈልግህ ውሎህ ያማረ፤ ምሽቱም አስደሳች ይሆናል፤

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!