2022-07-07 21:03:08
➽ ......
ሜርኩሪ......
➛ሜርኩሪ በስርአተ ፀሀያችን ውስጥ ከሚገኙት
9ኙ ፕላኔቶች በመጠን አነስተኛዋ እና ለፀሀይ
ቅርቡዋ ናት።
.
ስሙዋን ልታገኝ የቻለችው በሮማውያን
ሲሆን፤ በዘመናቸው ዝነኛ አምላካቸው
በነበረው በ 'ሜርኩሪ' ነው የሰየሙዋት።
.
መጠን፦ የፕላኔቱዋ ወገብ(equator)
2,439ኪሎሜትሮች ነው። ልክ እንደ
ምድራችን ሁላ ሜርኩሪም መሬቱዋ ከላይ
ወደታች በ 3 ክፍሎች ይከፋፈላል።(2ኛው ምስል ላይ ይመልከቱ)።
ክረስት(crust),
ማንትል(mantel) እና
ኮር(core) ተብሎ።
ክረስት፦ 300ኪሎሜትሮች ይቀጥናል
ማንትል፦600ኪሎሜትሮች ይቀጥናል።
ኮር፦ 1800ኪሎሜትሮች ራዲየስ አለው።
.
አትሞስፌር(atmosphe re)፦ የሜርኩሪ
አየር በውስጡ 42% ኦክስጅን፣ 29%
ሶድየም፣ 22% ሀይድሮጅን፣ 6% ሂልየም
አና 0.5% ፖታስየም ይዙዋል። ስለዚህ
ለመተንፈስ በጭራሽ አይሞከርም።
.
የሙቀት መጠን፦ ሜርኩሪ ለፀሀይ በጣም
ከመቅረቡዋ የተነሳ ቀን ቀን እስከ
427ሴልሽየስ ልትሞቅ ትችላለች። ማታ
ደግሞ ከ0 በታች እስከ 280 ሴልሽየስ
ትቀዘቅዛለች።
.
ሜርኩሪ በራሱዋ ዛቢያ ላይ ለመዞር 59
ቀናት ይፈጅባታል። ይህም ማለት በፕላኔቱዋ
1 ቀን ማለት 708 ሰአት ቀን 708 ሰአት
ሌሊት ነው ማለት ነው። ነገር ግን በፀሀይ
ዙሪያ 1 ዙር ለማጠናቀቅ 116 ቀናት
ይፈጅባታል። ስለዚህ በሜርኩሪ ላይ 1 አመት
116 ቀናት ብቻ ይሆናል ማለት ነው።
.
ፕላኔቱዋ ላይ የስበት መጠን 3.7m/s^2
ነው። ምድር ላይ ካለው የስበት መጠን በ 6.1
ያንሳል ማለት ነው። ይህም ቢሆን ለሰው ልጅ
ፕላኔቱዋ ላይ ለመራመድ በቂ አይደለም።
ከመራመድ ይልቅ መንሳፈፍ ነው የሚሆነው።
.
የሜርኩሪ ምህዋር በምድር ምህዋር የተዋጠ
ነው። ይህም ማለት ያለ ቴሌስኮፕ እርዳታ
በአይናችን ልናያት እንችላለን።
85 viewsTady W/ Giorgis, 18:03