Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ቤታችን ዩኒየን አካዳሚ አዲስ አበባ ላይ ተቀባይነትን ማግኘት የቻለውንና የበርካቶችን ቤተ | unionacademy10th

ትምህርት ቤታችን ዩኒየን አካዳሚ አዲስ አበባ ላይ ተቀባይነትን ማግኘት የቻለውንና የበርካቶችን ቤተሰብ በማንቃት ውጤታማ ልጆች የማፍራትና መልካም ግንኙነቶችን በማጠናከር የሚታወቀውን የስነልቦና አማካሪ እድሜአለም ግዛ (ማይንድ ሞርኒን የስልጠናና የማማከር አገልግሎት) ወደ ሀዋሳ በማምጣት ለወላጆች ስልጠና ያዘጋጀ በመሆኑ ቅዳሜ ሚያዚያ 8 ከጠዋቱ 2፡30 ቀድመው በመገኘት ሊያመልጥዎ የማይገባ በዋጋ የማይተመን የህይወት ዘመን ስንቅዎን ይሸምቱ ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
በስልጠናው የሚዳሰሱ ቁምነገሮች፡-
ሃሳቦች፣ የውስጥ ስሜቶች፣ የህይወት ጥያቄዎች፣ ስለ ራሳችን ያሉን ግራ መጋባቶች መልስ ያገኛሉ
ቁጣ፣ ብስጭት፣ ህመም፣ ድካም፣ አለመርካት፣ አሉታዊ አስተሳሰብ ቦታ ቦታቸውን ያገኛሉ።
ራስን መመልከቻ፣ ችግሮችዎን መፍቻ፣ ከራስ ጋር መታረቂያ፣ ቆሞ ማሰቢያ ስልጠና።
ልጆችዎን በልጅነታቸው የህይወት ክህሎቶችን ሲማሩ ንቃታቸው ይጠበቃል
ትኩረታቸው ይጨምራል
ተነሳሽነታቸው ከፍ ይላል
የመማር ፍቅራቸው ይጨምራል
ወላጆች ያርፋሉ ልጆች ስኬታማ ይሆናሉ::