Get Mystery Box with random crypto!

💝የፍቅር ድርሰት በግጥም💝

የቴሌግራም ቻናል አርማ tube1234channle — 💝የፍቅር ድርሰት በግጥም💝
የቴሌግራም ቻናል አርማ tube1234channle — 💝የፍቅር ድርሰት በግጥም💝
የሰርጥ አድራሻ: @tube1234channle
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 416
የሰርጥ መግለጫ

*💖የፍቅር ድርሰት በግጥም 💗
1 _ስለ ፍቅር በፍቅር እንደርሳለን💖
2_እውነተኛ 💗ሀሳብ ስለፍቅር እንደርሳለን💓
ቻናላችንን ሼር ስላረጉ ከ💗 እናመሰግናለን ካላረጉግን👇🙏🙏🙏🙏🙏🙏👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/TatIOCrLTrV8AxA4
እንወዳችዋለን🌹🌹🌷
💗ስለፍቅር🌷
የዩቱብ ቻናላችንን ሰብስ ክራይብ ያርጉ👇👇👇👇👇
https://you

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-28 12:48:42 ክፋቴን


ሚገርመው አንቺ
ከሴትም በላይ ነሽ
እድሜሽ አለካውም
ይሄንን ታውቂያለሽ
*
እኔን የሚደንቀኝ
አንቺን የማይገባሽ
እኔን የማይስበኝ
አንቺን የሚደላሽ
ለእኔ ግራ ሆኖ
ላንቺ ሁሌም ቀኝ
#ፍቅር ሚሉት
ቀልድ ነው።
:
እኔን ማይጥመኝ!
:
እረቀቅ እያሉ ብዙ
ዝካዝን'ኬ
እንዲው የሚነፉ
ፍቅር መሠዋት ነው!
ፍቅር ሀይለኛ ነው!
እያሉም ያለፉ
አፍቅረው ተፋቅረው
ቀናት ያሳለፉ
በመጨረሻው ሰአት
ጭንቀቱ ሲመጣ
:
ፍቅር ከሚይዝህ
አረ መርዝ ጠጣ!
:
ተብዬ ፈራሁኝ
መልካም ሴት ብትሆኝም
እኔ ክፉ ሰው ነኝ!
:
ፍቅር አይገዛኝም!


ልቤ ሰው አይወድም
ዙሪያዬን አጠርኩት
ይህን ጥሰሽ
የገባሽ እንደሆን
:
#ክፋትቴን ወደድኩት!


ዋ!



ተስፋኹን ተገኔ[ትንሹ]
123 views09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 15:32:41 Watch "አሰተዋሸ መዝሙር ዘማር በሸር prophet Tomas Torche 0932198590" on YouTube


367 views12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-07 11:15:19 እና በቅርቡ የተለያዩ ፎቶ ኤዲት ወይም
እንዲሰራላቹ ለምትፈልጉ በሙሉ ስራ ጀምረናል እንዲሁም ቪድዮ ኤዴትና ምስል ለሌለው ፎቶ ምሆነ ቪድዮ እናም ከለር በመስጠትም ሆነ በተለያዩ ስራችን
አመርቂ ና ጥረት የለስራ በመስራታችን
እንኮራለን እርሶስ ሊኮሩብን ይፈልጋሎ
እንግድያውስ ይደሉ+251 942100985
ናታን ፎቶ ና ቪዲዮ ስራ
ቻናላችንን

https://t.me/tube1234channle
424 views08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-06 12:01:38 Love and trustበግንኙነት ውስጥ ፍቅር እና መተማመን ምንድነው?

ያለ እምነት መውደድ አትችልም እምነት ለግንኙነትህ መሠረት እና ለፍቅር ቁልፍ ነው። የፍቅር ጓደኛክን ስታምን በአስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ እንደማትለቃት ደህንነት ይሰማካል. ይህ ፍቅር ለመገንባት እና ለማደግ ቁልፍ ነው.
370 views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-28 12:54:53 ፅናት

ክፍል 1

ድርሰት ቤዛዊት ፋንታዬ( የሸዋ ልጅ)
.
.
.

፨" የከተማ ገጠር ውስጥ መኖር እኮ ከባድ ነው"። አለች ፅናት እንደ ልማድዋ
በእጅ የምትያዘዋን ሬዲዮ ለመስራት እየታገለች። እንዲ ስትል ዊልቸር ላይ
የተቀመጠችው ማየት የተሳናት ታላቅ እህቷ በፀሎት "እንዴ ፅናቴ አሁን
የምንኖረው ከተማ አደል እንዴ ደሞ አነጋገረሽ ሁለት መልክ ያዘ" አለቻት።
ፅናትም "አይ ፀሎትዬ ባክሽ አንዳንዴ የሌለ ነገረ ያናዝዘኛል መሰለኝ"። አለችና
ሬዲዮኑን መታ አረገችው እሱም በዱላ ይሰራ ይመስል መስራቱን ቀጠለ።
ፅናት "ውይ ይሄ ፕሮግም አላመለጠኝም" አለችና ሬዲዩኑን ወደ ጆሮዋ
አስጠጋችው። እንደው ወደ ጆሮዋ ማስጠጋት ልምድ ሆኖባት እንጂ የሬዲዮኗ
ድምፅ ከእነሱ ቤት አልፎ ጎረቤት ይሰማል። ጓረቤት የላቸውም እንጂ ቢኖራቸው
ኖሮ!.. ሬዲዮኑ ውስጥ አንድ ጓረናና ድምፅ ያለው ተወዳዳሪ የሊለው ደራሲ ስለ
ድረሰቱ ምረቃት ለድረሰቱ ምረቃት በተዘጋጀው መድረክ ላይ ቆሞ የሚናገረ
ይመስላል።
የእነ ፅናት ቤት ሪዲዮኑ ውስጥ ከሚያወራው ሰው በቀር ምንም አይስማም ይህ
ታዋቂ ደራሲ ከታዳሚዎች ጭብጨባ በኋላ ወሬውን ቀጠለ። "ሰላም ጤና
ከአክብሮት ጋረ ይድረሳቹ። ስለ መፅሀፌ ከማውራቴ በፊት ስለ ድረሰት አንዳንድ
ነገረ ልበላቹ። ሁላችንም እዚህ አለም ላይ ስንኖር የፈጠረን አምላክ አለ ብለን
በማሰብ ነው። እና ለምሳሌ አውሮፕላን የስራው ስው ከወፍ ነው የአሰራር
ብልሀቱን የተማረው ፤መኪና የስራው ስው ከስው ውስጣዊ ሆድ እቃ አካል
ተነስቶ ነው መኪናን የስራው፤ኧኧኧኧ ሊሎችም እንደዛው ደራሲም ከህይወት
በመነሳትና እና ፈጠረን ካለው ፈጣሪ ህይወትን በመውሰድ ነው የሚደረሰው።
ልዩነቱ ፈጣሪ የፈጠረቻው ፍጥረታት በእውን አሉ እኛ የፈጠረኛቸው ደሞ
በምናብ አሉ። እኒን ምናባችን ውስጥ ያሉትን ስዎች በአካል ማምጣት በጭራሽ
አንችልም።ኧኧኧኧ ለምሳሌ እኔ በምፅፈው ድረሰት ውስጥ 3ሜትረ ቁመት ያላት
እምምምም ፤ ፀጉሯ እስከ እግረ ጥፍሯ የሚደረስ እእእእ፤ አፈንጮዋ በጣም
ትንሽ፤ አይኗ በጣም ትልልቅ፤ እጅ እና እግሯ የአራስ ህፆን መጠን ያላቸው፤
እእእእእ ስትሄድ አንካሳ ሴት በምናቤ ፈጥሬ መፃፍ መብቴ ነው።
፨ታዲያ እኔ መብቱ የግሌ ነውና ብገላትም ፣ባኖራትም፣ ባሳምማትም፣
ባድናትም ፣ባስቆዝማትም፣ ክፉ ባረጋትም፣ ደግ ባረጋትም ፣መብቴ ነው።
በተቃራኒው ቁመቷንም አጭረ አረጌ ፁጉሯን ረዥም ማረግ መብቴ ነው ብዙ
አፈቃሪ ወንድ ወይም ወንድ የማይጠጋት ማረግም የእኔ ውሳኔ ነው።
በእረግጠኝነት ይህቺ የነገረኮችሁን ሴት በምናባቹ አስባችዋታል ግን በአካል
የለችም።
፨እኔ በምናቤ የሳልኳትን ስው እንኳን እሷኑ አምጣ ብትሉኝ አላመጣም። ግን
በሀሳባቹ አኑሬያታለው ምክንያቱም የእኛ ስልጣን እዚህ ድረስ ስለሆነ ነው።
ፈጣሪ ግን ካሻው አሁን በእዚህ ስአት ከሁለት ቁመት አብዝቶ ከነሳቸው ስዎች
መጀመሪያ የገለፅኩላችሁን 3ሜትረ ቁመት ያላትን እንስት ፈጠሮ እና ህይወት
ስጥቶ ማኖረ ይችላል።እኔም የሆነ ደራጃ ድረሰ መሄድ እችላለው። ፈጣሪ በአንድ
እንስት መሀፀን ውስጥ ይህቺን ሴት ሲፀንሰሰ እኔ በሀሳቤ ይህቺን ሴት ፀነስኩ
ይባል። ታዲና ይህቺ ሴት ፈጣሪ በውልደት ወደ እዚህ አለም ሲያመጣት እኔ
የእሱ ተፈጣሪ ደሪሲ ደሞ ይህቺን ሴት በምናቤ አረግዤ በብእሬ እወልዳታለው።
፨ እኔም ሀሳቤን እሷም በእኩል ህመም እናስተናግዳለን። ይህንን ካልኩ ዘንዳ
ስለ ድረስቴ አንዳንድ ነገረ ልበላቹ ያው ይህ መፅሀፈ በእውነቱ ብዙ ዋጋ
አስከፈሎኛል። ውስጡ ያለውን ሀሳብ ትወዱታላቹ ብዬ አስባለው
አመስግናለው"። ሲል የታዳሚ ጭብጨባ አጀበው።
፨ በመሀል የሙዚቃ መሳሪያ ድምፅ ገባና የፕሮግራሙ አቅራቢ ሰው አመስግኖ
ተባባሪ አቅራቢውም "አብራችሁን እንድትቆዩ በአክብሮት እንጋብዛለን" አለች።
ወዲያው የሙዚቃ ክላክሲካል ተስማ። እረዥም ደቂቃዎች ካስቆጠረ በኋላ
የፕሮግራሙ መሪ ድምፅ ተሰማ "ተመልሰናል አድማጭ ተመልካቾቻችን አሁን
በመቀጠል የደራሲ መሀመድ ሳላዲን ባለቤት የሆነችው ወይዘሮ ከድጃ
ኢብራሂም ንግግረ እንድታረግልን በማክበር እንጋብዛታለን" አለ ወንዱ አቅራቢ።
ከዛ ጭብጨቦ ተከተለ መድረግ ላይ እንድትወጣ አበረታቶት። ጨብ
ጨብ.......... ጨብ ጨብብብብብብብብብብ የደራሲ መሀመድ ሳላዲን ሚስት
በሙዚቃ እና በጭብጨባ ታጅባ ወደ መድረክ እየሄደች ይመስላል።ከደቂቃዎች
በኋላ መድረክ ላይ ወጥታ ወደ ማይኩ ተጠጋች
" ሰላም እንዴት ቆያቹ"
አለች። ከዛን በኋላ ጭብጨባ አጀባት። እሷም "በመጀመሪያ ፣በመሀል እና
በመጨረሻም ጥሉ ለማይጥለን አምላክ አልሃምዱሊላህ እኔ ምን ማለት
እንዳለብኝ አላውቅም ማሚዬ ሁሌም ጥሩ ስራ ለመስራት እንደጣረ ነው። እሱ
ለእኔም ለልጆቹም እንዲሁም በዙሪያው ላሉ ስዎች ሁሉ ጥሩ ሰው ነው።ይህ
የፆፈው መፅሀፍም በህይወታቸው ተስፋ ለቆረጡ ስዎች የህሊና ብረታት
ይሆናል። ይህ መፅሀፈ በቃ አንብባቹ ተረዱት ምንም ማለት አልችልም
አመስግናለው" አለች።
ሁሉም አጨበጨብ ሴቷ የፕሮግራም አቅራቢም "እናመስግናለን ወይዘሮ ከድጃ
፣ተመልካቾቻን እና አድማጮቻችን ፍቅረን እና ስላምን እንዲሁም ደስታን
እንዲሰጣቹ እየተመኘን ፕሮግራማችንን በእዚሁ እንደዘጋለን" አለች። ወንድ
አቅራቢውም "መልካም ጊዜ ስናይ እለታትን እንድታሳልፉ እንመኝላችዋለን"
አለ። እና ፕሮግራሙ አበቃ።
፨ፅናት "ውይይይ ደስ አይሉም በፀሎቴ እንዲህ አይነት ፍቅረ ሲኖረ አለ እንጂ
የእኛ አባት" አለችና አንገቷን አቀረቀረች። ፅናት አባት እና እናቷን በፎቶ እንጂ
በአካል ያየቻቸው ማስታወስ በማችልበት የጨቅላ እድሜዋ ላይ ነው በፀሎት
ግን በትንሹ ታስታውሳቸዋለች። እሷም "እውነትሽን ነው ፅናቴ የእኛ አባት እኮ
በጭራሽ ሰው አይደለም" አለች። ሁለቱም አይምሮ ውስጥ የአባታቸው
እረኩስት ታወሳቸው።
ፅናት እህቷ በፀሎት በነገረቻት መሰረት በፀሎት ደሞ አይኗ ባየው መሰረት
አስታውሰው ፊታቸው ጭር አለ።በፀሎት በሀሳብ ጭልጥ አለች።ያሰብት ስለ
እናታቸው የሙት ቀን ስለሚወዶት እናታቸው አስቃቂ ግድያ እና ስለ ገዳዩ
አባታቸው ነበር።
፨ጊዜው 11 አመታትን አስቆጥሯል።እናታቸው ያኔ ፅናትን ወልዶ አራስነቷን
ጨረሳ የፅናት ክረስትና በአል የተከበረበት ጊዜ።በፀሎት ያን ጊዜ 5 አመቷ ነበረ።
በጊዜው የፅናት የክረስትና ቀን ስለሆነ ሁሉም ደስተኞች ነበሩ።እናታቸው
ከስፈራቸው ባለ ሀብት ገንዘብ ተበድራ በደመቀ መልኩ አክብራው ነበረ።
አባታቸው ለድግሱ አልገኝም ብሎ ወደ እህቱ ቤት ሄደ። የአባታቸው እህት
የስይጣን አለቃ ባህሪ ያላት ሴት ናት። አባታቸው እናታቸውን ካገባ በኋላ
"ሚስትክን ከሊላ ወንድ ጋረ አየዋት እሷ በጭራሽ ላንተ ፍቅር የላትም" በማለት
በመከረችው መስረት በፀሎት ሆዷ ውስጥ እያለች ልጅቷ የኔ አደለችም በማለት
ይነዘንዛት እና ይጨቃጨቃት ነበረ።
፨ የሆነው ሆኖ ለፅናት ክረስትና ቀን ጠዋት የድግሱን ብረ ውሽማሽ ነው
የስጠሽ ብሎ ለክፏት ወጣ።እናትየው ሁሌም መልስ አትሰጠውም የህይወቷን
ምእራፍ በትንሿ ልጇ ፅናት ብላ ስይማዋለች።በእዚህ መሰረት የመጨረሻ ልጆ
ስም ሴት ከሆነች ፅናት እላታለው ብላ አባ ስለነበር።ስትወልድ ሴት ልጅ
ወለደች።ይህቺ ልጅ ለህይወቴ ፅናት ናት አንቺንም በህይወት አቆይቶኝ
እንድወልድሽ ስለፀለይኩ ነው በፀሎት ያልኩሽ ብላ ለበፀሎት ይህንን የነገረቻት

ይቀጥላል

#የፍቅር_ቀን
575 views09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-19 15:44:40 بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيْمِ
السَّلاَمُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكَاتُهُ ዉድ የተከበራችሁ የቁርአን )quran channel ቤተሰቦች እዴት ናችሁልኝ አልሀምድሊላህ እኔ ደህና ነኝ እናተንም አላህ ይጠብቃችሁ ባለፈዉ መጀመሪያ ላይ አከባቢ እደገለፅኩላችሁ የቁርአንን ትርጉም በአማረኛ እናያለን ብየ ቃል በገባሁላችሁ መሰረት በእናንተ ምርጫ እዴት እንየዉ ትርጉሙን በአማረኛ ብቻ ከተለቀቀልን እኛ ከቁርአን እናያን፡ ወይም ቁርአኑንም የአማረኛ ትርጉሙንም አያይዘህ ብትለቅልን የሚሀዉን ሀሳብ በሁለቱ ላይ የናንተን ሀሳብ አይተን እንጀምራለን ከታች vote በመስጫዉ ታሳዉቁኛላችሁ ወይም በ botu አሳዉቁኝ በመቀጠል ደግሞ ከምን እንጀምር ከማን ሱራ ከመጀመሪያዉ ወይስ ከየት የሚለዉን በእናንተ ምርጫ በዉስጥ በቦቱ እድትነግሩኝ ፈልጋለሁ ፡፡
ትርጉሙ ብቻ ይለቀቅልን
ትርጉሙም ቁርአኑንም በአንድ ላይ ይለቀቅልን

ከየት ይጀመር የሚለዉን ደግሞ
@Quran_channelbot አድርሱኝ ወሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ፡፡
468 views12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-19 13:59:28 Channel photo updated
10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-18 11:07:54 Channel photo updated
08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-16 13:05:52 ከሌሊት ከዋክብት ይልቅ እወድሻለሁ; በየእለቱ ስንጣላ እንኳን ፍቅሬ በትንሹም ቢሆን አይለወጥም። እኔ ብቻ እወድሻለሁ ; በቃ አደርገዋለሁ።

በፈለኩክ ቁጥር፣ ለዘላለም አብረን እንድንሆን እመኛለሁ። በልቤ ውስጥ ስለምትኖር ይህ እውነት እንደሚሆን አውቃለሁ። እወድሃለሁ.

ሁሌም ፈገግ እንድል አንድ ሚሊዮን ትንሽ ምክንያቶችን ትሰጠኛለህ። በህይወቴ እንደ እንዳንተ የሚገርም ሰው ኖሮኝ አያውቅም። እወድሃለሁ!

አይንሽን ስመለከት በፍቅር እና በፍቅር የተሞላ አለም አያለሁ። በዓይንህ ውስጥ መጥፋት እና ራሴን በአዲስ ዓለም ውስጥ እንደገና ማግኘት እፈልጋለሁ። እወድሃለሁ!

አይንህን ስመለከት፣ በፍቅር በተሞላ ውቅያኖስ ውስጥ እጠፋለሁ። በህይወቴ ውስጥ ስለሆንክ እድለኛ ነኝ. እወድሃለሁ!

አንድ ቀን፣ ውበትሽን ለመግለጽ ግጥም ወይም ላንቺ ያለኝን ፍቅር ለመግለጽ ግጥም ልፅፍ እችላለሁ። አሁን ግን በፍቅርህ ብቻ ጠፍቻለሁ!

‍ ‍ ‍ ‍ እወድሃለሁ
አንተን መውደድ ህይወቴን የሚያስቆጭ ብቸኛው ነገር ነው። አንተን በመውደድ ባጠፋሁበት ጊዜ ሁሉ ደስ ይለኛል። በህይወቴ ውስጥ የእኔ የፀሐይ ብርሃን ነህ!

እራሴን ከምወደው በላይ ብዙ ጊዜ ወድጄሃለሁ። ሁል ጊዜ ደስተኛ እና ደስተኛ የምሆንበት ምክንያት አንተ ነክ ። እጅግ በጣም እወድሃለሁ !

እኛ የተለየ እና አሁንም ዓለም መሆን እንችላለን; ፍቅሬ ያገኝሃል። የልቤ ሁሉ ባለቤት አንተ ነህ። በጣም እወድሃለሁ

ያለአንተ ልኖር እችላለሁ፣ ግን ያ ህይወት ትርጉም የለሽ ይሆናል። መቼም ላጣህ አልፈልግም ምክንያቱም እኔ በነፍስህ በፍቅር ስለምወድ።

ፍቅር ለማዳበር ጊዜ ይወስዳል ነገር ግን ለአንተ ያለኝ ፍቅር በየቀኑ በከፍተኛ ደረጃ ያድጋል። የማደንቅህ አጋሬ እወድሃለሁ።

እኔ ካንተ ጋር ስሆን፣ የማደርገው ነገር ቢኖር ጊዜውን እንዳይፈስ ወደ እግዚአብሔር መጸለይ ነው። በህይወቴ የምፈልገው ከአንተ ጋር ለዘላለም ማሳለፍ ነው። እወድሃለሁ ውዴ!

ለምን በጣም እንደምወድህ ከጠየክኝ በአንተ ውስጥ የራሴን ቁራጭ ስላየሁ እና ካንተ ጋር ስሆን ራሴን እንድሆን ስለፈቀድክ እላለሁ።

ካንተ ጋር ካገኘሁህ ጊዜ ጀምሮ ልቤን ተቆጣጠረህ። አሁን የልቤ ባለቤት አንተ ነህ። ተንከባከበው እና የሚፈልገውን ስጠው . እወድሃለሁ!

አንተን እስክገናኝ ድረስ ጥቁር እና ነጭ ህይወት ኖሬያለሁ። ቀለሞችን ወደ ውስጥ አምጥተሃል እና አሁን ቀስተ ደመና በየቦታው አይቻለሁ። እወድሃለሁ!

474 views10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-15 10:19:00 @voicelovef
እንኳን ለፍቅር ቀን አደረሳችሁ

እንኳን ለፍቅረኛሞች ቀን አደረሳችሁ
@voicelovef
423 views07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ