Get Mystery Box with random crypto!

ተብዲዕና ተሕዚር ውድ ሰለፍይ ወንድምና እህቶች ከሰለፍያ መርሆች አንዱ የባጢል አንጃዎችን | ጧኢፈቱል መንሱራ

ተብዲዕና ተሕዚር
ውድ ሰለፍይ ወንድምና እህቶች ከሰለፍያ መርሆች አንዱ የባጢል አንጃዎችን ባጢል ለህዝቡ ግልፅ ማድረግና ከእነርሱ ማስጠንቀቅ ነው ። የሰለፍ ዑለሞች ከሙኻሊፍ ማስጠንቀቅን እንደ ጂሃድ ነው የሚቆጥሩት ።
ለኢማሙ አሕመድ አንድ ሰው መስጂድ ቁጭ ብሎ ቢሰግድ ፣ ቢቀራ ፣ ዒባዳ ቢያደርግ ይሻለዋል ወይስ ከሙኻሊፎች ( ከሙብተዲዖች) ቢያስጠነቅቅ ተብለው ሲጠየቅ መስጂድ ቁጭ ብሎ ቢሰግድ ቢቀራ ለራሱ ነው ። ከቢዳዓ ባልተቤቶች ቢያስጠነቅቅ ለህዝቡ ነው ይህ ይሻላል ነው ያሉት ። በዚህ ዙሪያ የመጡ አሳሮች ቁጥር ስፍር የላቸውም ። ቁርኣንና ሐዲስ ከሙኻሊፎች በማስጠንቀቅ የተመሉ ናቸው ።
ከዚህ ጋር በተገናኘ መታወቅ ያለበት
– ተብዲዕ ( እገሌ ሙብተዲዕ ነው ብሎ ብይን መስጠት )
– ተሕዚር ( ከአንድ ግለሰብ ወይም ጀማዓ ማስጠንቅ)
– ረድ ( አንድን ንግግር ወይም ፁሑፍ ትክክል አለመሆኑን በመረጃ በመግለፅ ምላሽ መስጠት )
የሚገናኙበትና የሚለያዩበት ሁኔታ መኖሩን ማወቅ ነው ።
ይኸውም : – ረድ ሰፋ ያለው ክፍል ሲሆን በሰለፍይም ላይ በሙኻሊፍም ላይ ሊደረግ ይችላል ። አላማው ረድ የሚደረግበት ንግግር ወይም ፁሑፍ ስህተት መሆኑን መግለፅና ሰዎች እንዳይሰሩበት ማድረግ ስለሆነ ።
– ተሕዚር ከግለሰብ ፣ ከጀማዓ ፣ ከንግግር ፣ ከፁሑፍ ሊሆን ይችላል ። ከግለሰብ ወይም ጀማዓ በልቅ ተሕዚር ለማድረግ ያ ጀማዓ ወይም ግለሰብ ከሱና የወጣ መሆን አለበት ። ነገር ግን በተገደበ መልኩ ከሰለፍይም ተሕዚር ሊደረግ ይችላል ። በተለይ ያ ሰለፍይ በሆነ መስአላ ላይ ተሳስቶ ፅፎ ወይም ተናግሮ ወደ አኼራ ሄዶ ከሆነ እከሌ በዚህ ንግግሩ ወይም ፁሑፉ ተሳስቷል ያን ንግግር አትስሙት ወይም በዚህ ፁሑፍ ተሳስቷል አታንብቡት ተብሎ ማስጠንቀቅ ይቻላል ። በህይወት ካለ ስህተቱ ይገለፅለታል እንዲያስተካከል ይነገረዋል ። የዓቂዳና ሚንሀጅ ጉዳይ ከሆነና አሻፈረኝ ካለ ከሱና ሊወጣም ይችላል ።
– ተብዲዕ ( እገሌ ሙብተዲዕ ነው ብሎ ሑክም መስጠት ) ይህ ከላይ ከገለፅናቸው ረድና ተሕዚር የሚለየው በቢዳዓ አራማጅ ላይ የሚሰጥ በመሆኑ ነው ። አንድ ሰው ሙብተዲዕ ነው የሚባለው ከሰለፍያ መርሆች አንዱን ወይም ከዛ በላይኻልፎ ሙኻለፋው ዑዝር የማያሰጠው ከሆነ ነው ። ይህን ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያና ኢማሙ አሽሻጢብይ ተቅሪር ያደረጉት ሐቅ ነው ። ይህም ማለት አንድን ሰው ሙብተዲዕ ነው ለማለት የሰራው ቢዳዓ በሸሪዓ ቢዳዓ መሆኑ የታወቀ መሆን አለበት ። ተብዲዕ ሸሪዓዊ ብይን ስለሆነ ቢዳዐነቱ በሸሪዓ መረጋገጡ ግድ ነው ። ቢዳዓ መሆኑ ብቻ በቂ አይደለም ያ ብይን የሚሰጥበት ሰው ይህን ቢዳዓ መስራቱም መረጋገጥ ይኖርበታል ። ቢዳዓው መስራቱ ከተረጋገጠ በኋላ የሰውየው ሁኔታ ይታያል ።
ሱና ላይ ያለ ፣ ሱና የሚያሰራጭ ፣ በሱና የሚታወቅ ከሆነ ብይን ከመሰጠቱ በፊት ያ የሰራው ነገር ቢዳዓ መሆኑና መመለስ እንዳለበት ይነገረዋል ። ከተቀበለና ከተመለሰ አልሐምዱ ሊላህ የሚፈለገው ያ ስለሆነ ያበቃል ። አሻፈረኝ ብሎ አልመለስም ካለ ዑለሞች መስላሀና መፍሰዳውን አይተው ብይን ይሰጣሉ ። ነገር ግን የቢዳዓ አራማጅነቱ የሚታወቅ ከሆነ የሰለፎችን መርህ የጣሱ አንጃዎች አካል ከሆነ ወይም ራሱን ወደዛ አንጃ የሚያስጠጋ እኔ ሱፍይ ነኝ ፣ እኔ ኢዋንይ ነኝ ፣ እና የመሳሰሉ ማንነቱን የሚገልፁ ፁሑፎችና ንግግሮች ነሽር የሚያደርግ ከሆነ የዚህ አይነቱ ሙብተዲዕ ለማለት በያን ወይም ሑጃ አያስፈልገውም እነዚህ አንጃዎች የቢዳዓ አንጃዎች መሆናቸውን ያወቀ ሙብተዲዕ ነው ሊል ይችላል ። ይህ ጉዳይ በጣም ሰፊና ጥቅ እውቀት የሚፈልግ ከመሆኑ አንፃር ወደ ዑለሞች ማስጠጋቱ አስፈላጊ ነው ። ጣሊበል ዒልም የሆነ ሰው ዑለሞች የሚሉትን እንዲህ ብለዋል ነው ማለት ያለበት ። ዑለሞች በመረጃ ያስቀመጡትን ብይን መቀበል ግድ ስለሆነና እንደነዚህ አይነት ጉዳዮች የሚመለከተው እነርሱን ስለሆነ ።
ሌላው ከዚህ ጋር በተያያዘ እገሌ ሙብተዲዕ ነው የሚለው ብይን መስጠት ፈርደል ኪፋኢ ( ከፊል ሰው ከሰራው ወንጀሉ ከሌሎች ላይ የሚወድቅ ) መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል ። በአንድ ሀገር ላይ ያሉ ታዋቂ ዑለሞች በአንድ ሰው ላይ በመረጃ ብይን ከሰጡ ሌላው ይህን ብይን መቀበል ነው ያለበት ። መቀበሉ የዑለሞቹን ብይን በማሰራጩቱና ሳይነቅፍ በሚጠየቅ ጊዘ ዑለሞች እንዲህ ብለዋል ብሎ በማሳወቁ ሊታወቅ ይችላል ።
አላህ ሐቅን አውቀው ከሚሰሩበትና ባጢልን አውቀው ከሚርቁት ያድርገን ።
http://t.me/bahruteka