Get Mystery Box with random crypto!

ሽቶና ሴቶች!? ➲አንድ ቀን አቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዓንሁ መንገድ ላይ ሽቶ ተቀብታ የምትጓዝን ሴ | ጧኢፈቱል መንሱራ

ሽቶና ሴቶች!?

➲አንድ ቀን አቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዓንሁ መንገድ ላይ ሽቶ ተቀብታ የምትጓዝን ሴት አገኘና
"አንቺ የታላቁ ጌታ ባሪያ የት እየሄድሽ ነው?" አላት። እሷም " ወደ መስጂድ" አለች።

⇛አቡ ሁረይራ " መስጂድ ለመግባት ነው ሽቶ የተቀባሽው?" አላት። እሷም " አዎን" አለች።

➻ አቡ ሁረይራ " ነብዩ የትኛዋም ሴት መስጂድ ለመሄድ ሽቶ ተቀብታ ከቤቷ ከወጣች ወደ ቤት ተመልሳ የጀናባ ትጥበት ካልታጠበች ሶላቷን አይቀበላትም ሲሉ ሰምቻለሁ" አላት።
ኢማሙ አህመድ ዘግበውታል

ታላቁ ዓሊም ሸይክ አልባኒ አላህ ይዘንላቸውና ይህን አስመልክቶ እንዲህ ይላሉ፦ "ሽቶ ወደ መስጂድ ለመሄድ ሀራም ከሆነ ገበያ፣ ቢሮ፣ ጎዳና፣ መዝናኛና መሰል ቦታዎች ሽቶ ተቀብታ የምትሄደው ሴት የበለጠ ትልቅ ወንጀል ውስጥ መውደቋ አያጠራጥርም"።

➛ ኢማም አልሀይተሚም 'አዘዋጂር' የሚባል ኪታባቸው ላይ " ሴት ሽቶ ተቀብታ ከቤቷ መውጣቷ ባሏ ቢፈቅድላትም ትልቅ ወንጀል ነው።" ይላሉ።

ﻣﺨﺘﺼﺮ ﻛﺘﺎﺏ ﺟﻠﺒﺎﺏ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﺔ(٤٤)
https://t.me/ewktyekdem