Get Mystery Box with random crypto!

በጎፋ ዞን በአራት ቀናት ውስጥ ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ 60 አህዮች መሞታቸው ተነገረ በጎፋ ዞን | Transit ማለፊያ

በጎፋ ዞን በአራት ቀናት ውስጥ ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ 60 አህዮች መሞታቸው ተነገረ

በጎፋ ዞን በሶስት ወረዳዎች ምንነቱ ባልታወቀ ተላላፊ በሽታ በአራት ቀናት ውስጥ 60 አህዮች ሲሞቱ በርካታዎች በበሽታው እየተጠቁ እንደሚገኙ የጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ አስታውቋል።

ይህ ምንነቱ ያልታወቀውን ተላላፊ በሽታ እያጠቃ የሚገኘው አህዮችን ብቻ ሲሆን ምንነት ለማወቅ ወደ ወላይታ ሶዶ ላብራቶሪ ናሙና ተልዕኮ ውጤት ማግኘት እንዳልተቻለ ተጠቁሟል።

በሽታውን ለመለየት ወደ ሰበታ ላብራቶሪ ተልዕኮ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ የጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ እንስሳትና አሣ ሀብት ሀላፊ የሆኑት አ/ቶ ሙሉቀን ተመስገን ተናግረዋል።

በበሽታው የተጠቁ አህዮች የአንገት መርዘም ፣ የመንቀጥቀጥ ፣ አረፋ መድፈቅ ምልክቶች የሚያሳዩ ሲሆን በተያዙ በሰዓታት ውስጥ እንደሚሞቱ ተገልጿል።

በሽታው መከላከል የሚቻል በሽታ ከመሆኑ ባለፈ የጋማ ከብቶችን ከሚያጠቃው አፒታኖት ሲክነስ ከሚባል በሽታ ጋር የሚመሳሰል ሁኔታ የታየ በመሆኑ ወደ ወረርሽኝ ደረጃ እየተሸጋገረ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት በበሽታው የተጠቁትን የመለየት ስራ እና ወደ ሌሎች እንዳይዛመት የማድረግ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ የበሽታው ምንነት እንደታወቀ ይፋ እናደርጋለን ሲሉ አ/ቶ ሙሉቀን ተመስገን ተናግረዋል ሲል ለብስራት ሬዲዮ ዘግቧል።


ቲክቫህ መፅሔት

ቻናላችንን በመቀላቀል ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን በጣቶ ስር ያድርጉ
@transit_leasons
@transit_leasons
@transit_leasons