Get Mystery Box with random crypto!

ነሐሴ 3፣ 2014 በላኒና ተፅዕኖ ምክንያት በመጠኑ የበረታው የዘንድሮ ክረምት በአንዳንድ አካባቢ | Transit ማለፊያ

ነሐሴ 3፣ 2014

በላኒና ተፅዕኖ ምክንያት በመጠኑ የበረታው የዘንድሮ ክረምት በአንዳንድ አካባቢዎች በታሪክ ትልቅ የሆነ የዝናብ መጠን እንዲመዘገብ አድርጓል ተባለ፡፡

እንደ ቆቃ፣ ርብ እና ጣና ያሉ ግድቦች የውሃ መጠናቸው ከፍተኛ ደረጃ ስለደረሰ አስቸኳይ ክትትል ያስፈልጋቸዋል ተባለ፡፡

የክረምቱ ዝናብ በበርካታ ቦታዎች ተጠናክሮ የሚቀጥል በመሆኑ የመሬት መንሸራተትና ከፍተኛ ጎርፍ ሊኖር ይችላል ተብሏል፡፡

የቀሪ ክረምት የጎርፍ ቅድመ ማስጠንቀቂያና የቅድመ ጎርፍ መከላከል ሥራዎች ዙሪያ ዛሬ በቢሾፍቱ ምክክር እየተደረገ ነው፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባዘጋጀው በዚህ ጉባኤ ላይ ሲነገር እንደሰማነው የክረምቱ ዝናብ በበርካታ ቦታዎች ላይ በያዝነው ወርም ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

የዝናብ ውሃና ጎርፍን በወጉ መቆጣጠርና ማስተዳደር ባለመቻሉ ትልቁ ፀጋ የኢትዮጵያ ስጋት እንደሆነባት ያነሱት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ በዚሁ ምክንያት አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎችም ቦታዎች ጎርፍ ለሰው ሕይወት መጥፋት፣ ለንብረት መውደም ምክንያት እየሆነ ነው ብለዋል፡፡

የዝናብ ውሃን በሚገባ መያዝ ብንችል ለዝናብ አጠር አካባቢዎች መፍትሄ ይሆን ነበር ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

በመጪው ጊዜም የዝናቡ መጠን የመሬት መደርመስና ከፍተኛ ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል እንደ አገር እንዴት እናድርግ ብሎ መነጋገር የግድ አስፈላጊ በመሆኑ የዛሬው ዝግጅት ተሰናድቷል ብለዋል፡፡

የክረምቱን የአየር ትንበያ በተመለከተ ማብራሪያ ያቀረቡት የብሔራዊ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ተመራማሪው አቶ ታምሩ ከበደ በሰኔና ሐምሌ የጣለው ዝናብ በአንዳንድ አካባቢዎች በታሪክ ትልቅ መጠን ያለው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በተለይም በምዕራብ እና ሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል የዝናብ መጠኑ ከፍተኛ እንደነበር ያነሱት ባለሙያው በትግራይና አማራ በሐምሌ ወር ብቻ እስከ 800 ሚሊ ሊትር የደረሰ ዝናብ ተመዝግቧል ብለዋል፡፡

በሰኔና ሐምሌ የተመዘገበው የዝናብ መጠን እስከ 1 ሺህ ሚሊ ሊትር መድረሱን ተናግረዋል፡፡

በላኒና ተፅዕኖ ምክንያት የዝናቡ መጠን በብዙ ቦታዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በዚህም ምክንያት የመሬት መደርመስ እንደ ተከዜ ፣ ሐዋሽና ግቤ ያሉ ወንዞች ደግሞ ጎርፍ ሊያስከትል ይችላል ተብሏል፡፡

የግድቦችና የወንዞችን የውሃ መጠንንም በጥንቃቄ መከታተል ይገባል ተብሎ ተመክሯል፡፡

በተለይ ቆቃ፣ ርብ እና ጣና ግድቦች የውሃ መጠናቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ስለደረሰ አስቸኳይ መፍትሄ ይፈልጋሉ፤ ግቤ 1 እና 3 እንዲሁም ከሰምና ተንዳሆም ክትትል ያስፈልጋቸዋል ተብሏል፡፡

ቴዎድሮስ ወርቁ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ላኒና #የውሃና_ኢነርጂ_ሚኒስቴር

ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqzG
ሸገር FM

ቻናላችንን በመቀላቀል ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን በጣቶ ስር ያድርጉ
@transit_leasons
@transit_leasons
@transit_leasons