Get Mystery Box with random crypto!

የስልክ ሙቀት መጨመር ስልካችን ለምን ይሞቃል? የስልካችን ውስጣዊ የሙቀት መጠን(Tempera | 🇹 🇴 🇲 t҈ u҈ b҈ e҈ 

የስልክ ሙቀት መጨመር

ስልካችን ለምን ይሞቃል?

የስልካችን ውስጣዊ የሙቀት መጠን(Temperature) በአካባቢው ላይ ባለው የአየር ሁኔታ ይወሰናል።ስልካችን በጣም ከሞቀ፤የተለያዩ ችግሮችን ያስከትላል ልክ የባትሪ መጠን በፍጥነት እንደመቀነስ፣እኛ ሳንፈልግ ስልካችን shutdown ያረጋል እና የስልካችን ሲፒዩ(centeral processing unit-CPU) እስከ መቅለጥ ያደርሰዋል።እና ስልካችን በሙቀት ምክንያት እሩሱ shutdown ካረገ ቡኃላ ድጋሚ ያለመክፈት ሰፊ እድል አለው።

ስልካችን ከተገቢው የሙቀት መጠን በላይ እንዲሆን የሚያደርጉ ብዙ ምክንያቶች አሉ።ከእነሱም ውስጥም ጥቂቶቹን እንይ

የተጠቀምናቸው አፖች ሳንዘጋቸው መተው ማለትም Recent App አለማጥፋት

ስልካችን ላይ የምናሳልፈው ጊዜ፤ስልካችንን ለብዙ ሰዓት ምንጠቀም ከሆነ የስልኩ ባትሪ መስራት ካለበት በላይ ይሰራል።ይህም አንዱ የስልካችን ሙቀት እንዲጨምር ያረጋል።

ሌላኛው ደግሞ ቻርጅ የማድረግ ልምዳችን ነው።ለምሳሌ ስልካችን 100% ከሆነ በኃላ እንኳን አለመንቀል ወይም overcharging።

ምክንያቶቹን እና የሚያስከትለውን ጉዳት ካየን መፍትሄዎችንም ማውቅ አለበን።የስልካችን የሙቀት መጠን መጨመር ለማቆም ከሚረዱን መንገዶች ውስጥ

ስልካችንን ከቀጥታ የፀሃይ ብርሃን መከላከል!

Recent Apps ማጥፋት

የስልካችንን ብራይትነስ(brightness) መቀነስ

ስልካችን በሚሞቅ ጊዜ የስልኩን ከቨር ማውለቅ

════❁✿❁ ═══════

@tom_abe