Get Mystery Box with random crypto!

በኦሮሚያ ክልል ከመጪው ሰኞ ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ እንደሚጀመር ተገለ | Ministry of education®

በኦሮሚያ ክልል ከመጪው ሰኞ ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ እንደሚጀመር ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ከመጪው ሰኞ ጀምሮ በሁሉም የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ እንደሚጀምር የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ።

በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤቶች ማሻሻያ ፕሮግራም ዳይሬክተር ወርቅነህ ነጋሳ እንደገለጹት በክልሉ ትምህርት መጀመር የሚያስችል ዝግጅት ተጠናቋል።

የመምህራን ዝግጅት፣ የመማሪያ መጻሕፍት ማዘጋጀትና የትምህርት ቤቶች ዝግጅት ስራ መከናወኑን ተናግረዋል።

የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው ይኸው ስራ እስከ መስከረም 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

በዚሁ የትምህርት ዘመን በክልሉ 11 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን የገለጹት ዳይሬክተሩ በእስከ አሁኑ ሂደት የተማሪዎች ምዝገባ ከ95 በመቶ በላይ መጠናቀቁን አመልክተዋል።

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER