Get Mystery Box with random crypto!

#Addis_Ababa_Education_Bureau በአዲስ አበባ ከተማ ከመስከረም 03/2015 ዓ.ም | Ministry of education®

#Addis_Ababa_Education_Bureau

በአዲስ አበባ ከተማ ከመስከረም 03/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት መሰጠት ይጀምራል።

በሁሉም የትምህርት ተቋማት የ2015 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ መስከረም 09/2015 ዓ.ም እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አድማሱ ደቻሳ ነሐሴ 27/2014 ዓ.ም ለሁሉም ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤቶች በላኩት ደብዳቤ ነው ይህን የገለጹት።

ትምህርት ቤቶች የ2015 ትምህርት ዘመን ለመጀመር ዝግጅታቸውን መስከረም 06/2015 ዓ.ም ያጠናቅቃሉ ብለዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ ! !

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER