Get Mystery Box with random crypto!

የተማሪዎች መማሪያ ደብተር እስከ 80 ብር እየተሸጠ ነው ተባለ በአዲስ አበባ ራዲካል ተብሎ | Ministry of education®

የተማሪዎች መማሪያ ደብተር እስከ 80 ብር እየተሸጠ ነው ተባለ

በአዲስ አበባ ራዲካል ተብሎ የሚጠራው ባለሃምሳ ገፅ አንድ ደብተር እስከ 80 ብር የሚሸጥ ሲሆን፣ በክፍለ አገር ከተሞች መጠነኛ ቅናሽ እንዳለው አዲስ ማለዳ ዘግባለች። 32 ገፅ ያላቸው መማሪያ ደብተሮችም እንደጥራት ደረጃቸው ከ30 እስከ 60 ብር መሸጫ ዋጋቸው ሆኗል።

ባለፈው ዓመት የትምህርት ዘመን መጀመሪያ እስከ 40 ብር ይሸጥ የነበረ ደብተር ነው በዚህ ዓመት ከእጥፍ በላይ የጨመረው ተብሏል። በዚህም የተማሪ ቤተሰቦች በተማሪዎች መማሪያ ቁሳቁስ አላግባብ የዋጋ መወደድ ቅሬታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ ! !

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER