Get Mystery Box with random crypto!

የአንድ አባት ፀሎት ።።።።።።።።።።።።።።።። ሚበላ የሚላስ የሚጠጣ በሌለበት የአንድ ሚስኪን አባ | ፍቅርና ተስፋ

የአንድ አባት ፀሎት
።።።።።።።።።።።።።።።።
ሚበላ የሚላስ የሚጠጣ በሌለበት
የአንድ ሚስኪን አባት የለመና ፀሎት
በተቆራመተ መንገድ ንፋስ በሚነፍስበት
በብርዳማ አለም ብዙ መንገደኛ በሚተራመስበት
በባዶ ሆድ በብጣቂ ጨርቅ ተሸፍኖ ከሰዋች መሀል በሚታይበት
ስለሀገሩ አንድነት ፀለየ በእውነት
ቀጥሎም ስለ ራሱ እውነት
አብዝቶ ተማፀነ አንድ ሚስኪን አባት
ሰው በሚጓዝበት መንደር
ስለሰው አብዝተው ይፀልዩ ነበር
በችግሮቹ መሀል ሌላው እንዳይቸገር
አንድ ሚስኪን አባት ከራሱ አስቀድሞ ለሀገሩ ይፀልይ ነበር
የሰው እጅ በማየቱ ልቡ ቢያመው በብርቱ
አንዳች አላማረረም ፀሎት ነው ብርታቱ
M.M

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!

@tloveandhope