Get Mystery Box with random crypto!

መቸም ቢሆን አልረፈደም! ከ65 አመቱ ወጣት የምንማረው...! በአንድ ወቅት በአንዲት ኬንታኪ በም | ፍቅርና ተስፋ

መቸም ቢሆን አልረፈደም! ከ65 አመቱ ወጣት የምንማረው...!

በአንድ ወቅት በአንዲት ኬንታኪ በምትባል የአሜሪካ ግዛት ውስጥ ከመንግስት በየወሩ በሚሰጠው 99$ የሚኖር ፣ ገንዝብ አልባ ፣ ትንሽ ቤት ውስጥ የሚኖር እና አሮጌ መኪና የሚነዳ ሽማግሌ ሰው ነበር ።

ይሄ ሰው ልክ 65 አመት ሲሞላው ልጅነቴንማ በዚህ መልኩ ማባከን የለብኝም በማለት ነገሮችን ለመቀየር ተነሳ ። ከዚያም ምን አገልግሎት? ለሰዎች ልስጥ ብሎ ሲያስብ ጓደኞቹ ሁሌ የሚያደንቁለት የዶሮ አሰራሩ ትዝ አለው ። ስለዚህ በህይወቱ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ይቺ የዶሮ አሰራር ቁልፍ እንደሆነች ወሰነ!!!

ከዛም ጥርስ የነቀለባትን ኬንታኪ ትቶ ይቺኑ የምግብ አሰራር ለመሸጥ ብዙ የአሜርካ ክፍሎችን ዞረ። ለብዙ የሬስቶራንት ባለቤቶች እጅ የሚያስቆረጥም የዶሮ አሰራር እንዳለው ነገራቸው። እንደውም ከሽያጫቸው ላይ ትንሽ ፐርሰንት ከሰጡት አሰራሩን በነጻ ሊሰጣቸው ሁሉ ፈቀድ።

የሬስቶራንት ባለቤቶቹ ግን እንደሱ አላሰቡም። 1000 ግዜ አይሆንም አሉት። እሱ ግን እጅ አልሰጠም።

ዶሮ አሰራሩ በጣም የተለየች እንደሆነች አጥብቆ ያምን ነበርና። የመጀመሪያውን እሺ እስኪያገኝ ድረስ 1009 ግዜ አይሆንምን ሰማ ።

በመጨረሻ ግን ኮሎኔል ሃርትላንድ ሳንድራስ አሜርካኖች ብቻ አይደለም በአለም ያለ ሰው ሁሉ ዶሮ የሚበላበትን መንገድ ቀይሯል ።

ኬንታኪ የተጠበሰ ዶሮ መሸጫ (KFC) የተፈጠረው በዚህ መልኩ ነው ።

ከ65 አመቱ ወጣት ጋሽ ሳንድራስ የምንማረው .....

#መቼም ቢሆን አልረፈደም!
40, 50 ወይም 60 አመትም ቢሞላን መንገድ መቀየር ከፈለግን ማለት ያለብን "ልጅነቴንማ እንደዚህ አላባክነውም" ነው ።

በህይወት መዘግየት ማለት አለመድረስ አይደለም። ስለዚህ ሁሌም ጉዞህን ቀጥል!

ሁሌም ካለህበት ጀምር፤ ያለህን ተጠቀምበት፤ የምትችለውን አድርግ!

መልካም ቀን!

@tloveandhope