Get Mystery Box with random crypto!

አርብ - አሁን ሙዚቃው ለስለስ ብሎ ወደ ጆሮዬ እየፈሰሰ ነው ታምቡሬ ተመችቶታል። Dance | የግጥም አብዮት_ልጆች🙏

አርብ - አሁን

ሙዚቃው ለስለስ ብሎ ወደ ጆሮዬ እየፈሰሰ ነው ታምቡሬ ተመችቶታል።

Dance me to the end of LOVE
Leonard Cohen.

ዓይኔ ደግሞ ብዙዎች እጃቸው ቢገባ የሚመኙትን "እስኪ ተጠየቁ" የተሰኘ እጅግ የተከበረውን የዮሃንስ አድማሱ መፅሃፍ አንብቦ ለዓዕምሮዬ ምግብ ይሆን ዘንድ ጀባ እያለው ነው።ታድዬ አይደል? በነገራችን ላይ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ የህይወት ታሪክ የተፃፈው በእርሱ ነው ። እስኪ ከደረስኩበት አንዲቷን ቀዘባ የሚል ግጥም ልጋብዛችሁ

አንዲቱን ቀዘባ
~~

እንደ ሐምሌ ወራት ፊቷ ጭፍና ለብሶ፣
እንደ መኀር ድርቆሽ ልብሷ ተልከስክሶ፣
አየኋት ለየኋት አንዲቱን ቀዘባ፣
ዘንጠፍ ዘና ብላ እንደ መስክ አበባ።

ፊቷ ጭፍን ቢለብስ፣
ልብሷ ቢልከሰከስ፣
ግና ሥግው ሆኖ ውበት ተደብቆ፣
ታየኝ ተገለጠ ድንገት አሸብርቆ።

ልብሷ የባላገር አየሯ ገጠር፣
ኩለንታዊ ውበት ይዛ የምትኖር፣
አየኋት ከመስኩ ወደገጠር ሄጄ፣
ተፈጥሮን ስፈልግ ተፈጥሮን ወድጄ።

ነባይ አባይ ማለት በተፈጥሮ ቤት፣
አንዲቱን ቀዘባ አክሊል የውበት፣
ያልተዳደፈችው በሰው ሰራሽ ፈሊጥ ከንቱ ፈንደለላ፣
አየኋት ለየኋት የገጠሯን ሰንደቅ የገጠሯን አፍላ።

ነሐሴ 1954 ዓ.ም
( ገጣሚ ፦ ዮሐንስ አድማሱ )

* ሥግው = ግልጽ፣ክሱት፣ሥጋ ለበሰ ከሚለው ይመጣል፣በሌላ በኩል ደግሞ ድብቅ፣ሽሽግ ማለት ነው።

*ፈንደለላ = ግዴለሽ፣ከንቱ ።

የምርምር ፣የትርጉም፣የመዝገበ ቃላት ፣የልቦለድ ፀሃፊው እና ዕንቁ ገጣሚው ዮሐንስ አድማሱ መስከረም 1929 ተወልዶ ሰኔ 1967 ከዚህ አለም በሞት ተለየ።

Kida Yegeter Lij