Get Mystery Box with random crypto!

ልጅ ቢኖረው በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 43፥81 «ለአልረሕ | Tiriyachen | ጥሪያችን

ልጅ ቢኖረው

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

43፥81 «ለአልረሕማን ልጅ ቢኖረው እኔ ለልጁ የተገዢዎቹ መጀመሪያ ነኝ» በላቸው፡፡ قُلْ إِن كَانَ لِلرَّحْمَـٰنِ وَلَدٌ فَأَنَا أَوَّلُ الْعَابِدِينَ

ዐበይት ክርስቲያኖች፦ "ወልድ ከአብ ባሕርይ ባሕርይን ወስዶ፣ ከአካሉ አካልን ወስዶ እና አብን አህሎና መስሎ ከእርሱ ወጣ፣ ተወለደ፣ ተገኘ" በማለት አሏህን ወላዲ መሢሑን ተወላዲ በማድረግ ለአሏህ ቁራጭን አደረጉለት፦
43፥15 ከባሮቹም ለእርሱ ቁራጭን ልጅ አደረጉለት፡፡ ሰው በእርግጥ ግልጽ ከሓዲ ነው፡፡ وَجَعَلُوا لَهُ مِنْ عِبَادِهِ جُزْءًا ۚ إِنَّ الْإِنسَانَ لَكَفُورٌ مُّبِينٌ

ይህ የባሕርይ ልጅ የሚባል ለአሏህ የለውም፥ አሏህ አንድ ነው፥ እርሱ ከማንነቱ እና ከምንነቱ ማንንም አልወለደም። ከእርሱ ማንነት እና ምንነት የተወለደ ማንም የለም፥ ከእርሱ የተወለደ ማንም አምላክ የለም፦
112፥1 በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ
112፥3 አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ
23፥91 አላህ ምንም ልጅን አልወለደም፡፡ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ مَا اتَّخَذَ اللَّهُ مِن وَلَدٍ وَمَا كَانَ مَعَهُ مِنْ إِلَـٰهٍ

ወደ ፈትለ ነገሩ ስንገባ አምላካችን አሏህ የባሕርይ ልጅ እንደሌለው ለማመላከት የተጠቀመበት ሐርፉ አሽ-ሸርጥ በመጠቀም ነው፥ "ሐርፉ አሽ-ሸርጥ" حَرْف الشَرْط ማለት "ሁኔታዊ መስተዋድድ"conditional particle" ነው፦
43፥81 «ለአልረሕማን ልጅ ቢኖረው እኔ ለልጁ የተገዢዎቹ መጀመሪያ ነኝ» በላቸው፡፡ قُلْ إِن كَانَ لِلرَّحْمَـٰنِ وَلَدٌ فَأَنَا أَوَّلُ الْعَابِدِينَ

"ኢን" إِن ወይም "ለው" لَوْ በሰዋሰው አቀማመጥ ሐርፉ አሽ-ሸርጥ ነው፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "ኢን" إِن የሚለው የገባው ሐርፉ አሽ-ሸርጥ "አሏህ ልጅ የለውምና ስለዚህ ዒሣን አትገዙት" እንጂ "ልጅ ካለው መገዛት ይቻላል" የሚል በፍጹም አይደለም። ለዚህ አንቀጽ ተመሳሳይ አንድ የሙግት ናሙና እናቅርብ፦
7፥143 ሙሳም ለቀጠሯችን በመጣና ጌታውም ባነጋገረው ጊዜ፡- *«ጌታዬ ሆይ! አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና» አለ፡፡ አላህም፡- «በፍጹም አታየኝም ግን ወደ ተራራው ተመልከት፡፡ "በስፍራውም ቢረጋ በእርግጥ ታየኛለህ"» አለው፡፡ ጌታው ለተራራው በተገለጸ ጊዜ እንኩትኩት አደረገው፡፡ ሙሳም ጮሆ ወደቀ፡፡ በአንሰራራም ጊዜ «ጥራት ይገባህ፡፡ ወደ አንተ ተመለስኩ፡፡ እኔም የምእምናን መጀመሪያ ነኝ» አለ፡፡ وَلَمَّا جَاءَ مُوسَىٰ لِمِيقَاتِنَا وَكَلَّمَهُ رَبُّهُ قَالَ رَبِّ أَرِنِي أَنظُرْ إِلَيْكَ ۚ قَالَ لَن تَرَانِي وَلَـٰكِنِ انظُرْ إِلَى الْجَبَلِ فَإِنِ اسْتَقَرَّ مَكَانَهُ فَسَوْفَ تَرَانِي ۚ فَلَمَّا تَجَلَّىٰ رَبُّهُ لِلْجَبَلِ جَعَلَهُ دَكًّا وَخَرَّ مُوسَىٰ صَعِقًا ۚ فَلَمَّا أَفَاقَ قَالَ سُبْحَانَكَ تُبْتُ إِلَيْكَ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُؤْمِنِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ኢን" إِن የሚለው የገባው ሐርፉ አሽ-ሸርጥ "ተራራው አይረጋምና ስለዚህ አታየኝም" እንጂ "ቢረጋ ታየኛለህ" ማለት እንዳልሆነ ሁሉ በተመሳሳይ ከላይ ያለውን አንቀጽ በዚህ ልክ እና መልክ መረዳት ይቻላል።
"በስፍራውም ቢረጋ" ማለት "አይረጋም" ማለት ከሆነ "ልጅ ቢኖረው" ማለት "የለውም" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "በስፍራውም ቢረጋ በእርግጥ ታየኛለህ" ማለት "አይረጋም አታየኝም" የሚለውን ለመግለጽ የመጣ ግነታዊ አገላለጽ እንደሆነ ሁሉ "ለአልረሕማን ልጅ ቢኖረው" ማለት "ለአልረሕማን ልጅ የለውም" የሚለውን የሚለውን ለመግለጽ የመጣ ግነታዊ አገላለጽ ነው።
ዕውቀት አልባ የሆነ ባተሎ እና ዘባተሎ እሳቤ ይዞ የአሏህን ንግግር ለመተቸት የሚያስችል የሞራል ብቃት፣ አቅም፣ ወኔም የላችሁም። አሏህ ሂዳያ ይስጣችሁ፥ ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ

ጥሪያችን በሁሉም ቦታ
Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen