Get Mystery Box with random crypto!

ጥያቄአችን! የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመርያው ማን ነው? ጉማሬ? ሰማይና ምድር? ወይስ ኢየሱስ? | Tiriyachen | ጥሪያችን

ጥያቄአችን!

የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመርያው ማን ነው? ጉማሬ? ሰማይና ምድር? ወይስ ኢየሱስ?

A. ጉማሬ፦

”ከአንተ ጋር የሠራሁትን ጉማሬ እስኪ ተመልከት”፤ እንደ በሬ ሣር ይበላል።
ኢዮብ 𝟒𝟎፥𝟏𝟓

”እርሱ የእግዚአብሔር ፍጥረት “አውራ” רֵאשִׁ֣ית ነው”።
ኢዮብ 𝟒𝟎፥𝟏𝟗

“he Is thE FIRst OF THe worKS OF God; Let HIM Who MaDe hIm BRiNg near HIs swoRD!

enGlish sTAndArD versiOn

“አውራ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “መጀመሪያ”The firsT” ተብሎ ከላይ ተቀምጧል። የዕብራይስጡ ላይ ደግሞ “ረሺት” רֵאשִׁ֣ית ሲሆን ይህ “ረሺት” ቃል ለሰማይና ምድር ጅማሬነት አገልግሎት ላይ ውሏል።

B. ሰማይንና ምድር፦

በመጀመሪያ בְּרֵאשִׁ֖ית እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
ዘፍጥረት 𝟏፥𝟏

“በ” ב ማለት “በ” ማለት ሲሆን መስተዋድድ ነው። “ረሺት” רֵאשִׁ֣ית ደግሞ “መጀመሪያ” ማለት ነው።

c. ኢየሱስ፦

እዚህ አንቀጽ ላይ ደግሞ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ ነው ይለናል፦

አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ ”የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ” የነበረው እንዲህ ይላል፦ The BegInNING Of ThE cReatiOn OF gOD. (EnGLish reVised VERsIon)
ራእይ 𝟑፥𝟏𝟒

ግሪኩ፦ Ἡ ἈΡΧὴ ΤΗ͂ς κΤίΣεως ΤΟΥ͂ ΘεΟΥ͂:

“የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ “መጀመሪያ” ለሚለው የገባው ቃል ልክ እንደ የሙታን መጀመሪያ “አርኬ” ἀΡΧΉ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፦

አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኵር ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።
𝟏 ቆሮንቶስ 𝟏𝟓፥𝟐𝟎

ግሪክ፦ νΥνὶ δῈ ΧρισΤῸΣ ἘγήγΕΡταΙ ἐΚ νΕκρῶΝ, ἀπΑρχῊ Τῶν ΚΕΚοιΜΗΜένωΝ.

“በኵር” የሚለው የግሪኩ ቃል “አፕ-አርኬ” ἀπαΡχὴ ሲሆን የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “አፓ” ἀΠό ማለትም “ከ” እና “አርኬ” ἀΡχΉ ማለትም “መጀመሪያ” ነው፤ ላንቀላፉት ሙታን “መጀመሪያ” ነው ማለት መጀመሪያ የተነሳ ማለት ከሆነ የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ ማለት መጀመሪያ የተፈጠረ ማለት ነው።

ስለዚህ የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመርያው ማን ነው? ጉማሬ? ሰማይና ምድር? ወይስ ኢየሱስ?

ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

ጥሪያችን በሁሉም ቦታ
Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen