Get Mystery Box with random crypto!

የመጽሀፍ ቅዱስ የእርስበርስ መኮራረጅ አንድ መጽሀፍ ኮረጀ የሚባለው ከሌላ መጽሀፍ ሀሳብን እንደወ | Tiriyachen | ጥሪያችን

የመጽሀፍ ቅዱስ የእርስበርስ መኮራረጅ

አንድ መጽሀፍ ኮረጀ የሚባለው ከሌላ መጽሀፍ ሀሳብን እንደወረደ ሲወስድ ነው። ልብ በሉ “ከሌላ መጽሀፍ”..! መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ግን መፀሀፍቱ እራሱ እርስበርስ እዚያው ሲኮራረጁ ታስተውላላችሁ። የሚኮራረጁት አንድ አንቀጽ ወይንም ሁለት አንቀፅ ብቻ አይደለም፤ ከሞላ ጎደል ሙሉ ምዕራፍ ነው። ይህንን አስቂኝም አስገራሚም ጉዳይ እስኪ በማስረጃ እናድርገው።

መጽሀፍ ቅዱስን ስንከፍት የትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ 𝟑𝟕 ስር ያሉ አንቀፆች ያለምንም መለዋወጥ በመጽሀፈ ነገስት ካልዕ 𝟏𝟗 ላይ ይገኛሉ። እንዲሁ ተራ መመሳሰል ብቻ እንዳይመስላችሁ። ኩረጃ እንደሆነ በሚያሳብቅ መልኩ ቃል በቃል ያለምንም መለዋወጥ ነው አንደኛው ከአንደኛው የቀዳ..!

❐ አንቀፆቹን አስቀምጨ ፍርዱን ለእናንተ ከመስጠቴ በፊት መጽሀፍቶቹ የተፃፉበትን ጊዜ እንደ መረጃ ሰጥቻችሁ ልለፍ፦

፩-በርግጥ ከነ አካቴው መጽሀፈ ነገስት የተፃፈበት ጊዜ እንደማይታወቅ የመጽሀፍ ቅዱስ ምሁራን ይገልፃሉ። መምህር ያሬድ ሽፈራው “የመጽሀፍ ቅዱስ ታሪካዊ አመጣጥ” በሚለው መጽሀፉ ቅጽ 𝟏 ገፅ 𝟐𝟓 ላይ ከመገመት ውጭ ትክክለኛው ጊዜ እንደማይታወቅ ገልፆ ግምቱ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ𝟓𝟖𝟔-𝟓𝟑𝟗 ሊሆን እንደሚችል ያስቀምጣል። ማኅበረ ቅዱሳን ባዘጋጀውና መምህር ቸርነት አበበ ባዘጋጁት “መሠረታዊ የመጽሀፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴ” በሚለው መጽሀፍ ላይ ገፅ 𝟏𝟑𝟖 ጀምሮ በደፈናው ጸሀፊውም ጊዜውም እንደማይታወቅ ጠቅሶ ያልፋል።

፪- ትንቢተ ኢሳያስን በተመለከተ መምህር ቸርነት አበበ እንደገለፁት የተጻፈው ከክርስቶስ ልደት በፊት 𝟖𝟖𝟖-𝟕𝟒𝟎 ሊሆን እንደሚችል ያስቀምጣሉ። iBiD 𝟐𝟎𝟒

ይህንን እንደመግቢያ ካየን ሁለቱን ምዕራፎች ከታች ላስቀምጥላችሁና በፍጹም ተመሳሳይነታቸው ተገረሙ። በርግጥ ኮርጇል ብላችሁ የምትወቅሱት ሰው ላይኖር ይችላል፤ ምክንያቱም የሁለቱም መጽሀፍት ጸሀፊዎች ከግምት ውጭ በትክክል ማን እንደጻፈው አይታወቅም።

ማስታወሻ፦ ቦታ ለመቆጠብ ከምዕራፎቹ የምጠቅሰው ሶስት አንቀፆች ብቻ ሲሆን የቀረውን ክፍል እናንተው ከፍታችሁ ማረጋገጥ ትችላላችሁ።

“እንዲህም ሆነ፤ ንጉሡ ሕዝቅያስ ይህን በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀደደ፥ ማቅም ለበሰ፥ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ገባ። የቤቱንም አዛዥ ኤልያቄምን ጸሐፊውንም ሳምናስን የካህናቱንም ሽማግሌዎች ማቅ ለብሰው ወደ ነቢዩ ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ኢሳይያስ ይሄዱ ዘንድ ላካቸው። እነርሱም፦ ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል ለመውለድም ኃይል የለም።”

ትንቢተ ኢሳይያስ 𝟑𝟕፥𝟏-𝟑

እንለፍ

“ንጉሡም ሕዝቅያስ ይህን በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀደደ፥ ማቅም ለበሰ፥ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ገባ። የቤቱንም አዛዥ ኤልያቄምን ጸሐፊውንም ሳምናስን የካህናቱንም ሽማግሌዎች ማቅ ለብሰው ወደ ነቢዩ ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ኢሳይያስ ይሄዱ ዘንድ ላካቸው። እነርሱም፦ ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል፥ ለመውለድም ኃይል የለም።”
መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 𝟏𝟗፥𝟏-𝟑

(የሕያ ኢብኑ ኑህ)

ጥሪያችን በሁሉም ቦታ
Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen