Get Mystery Box with random crypto!

የቀሲስ አክሊል ዳምጠው ክስ ጉዳይ...! ቀሲስ አክሊል ዳምጠው ከወራት በፊት በኢትዮጵያ ኦርቶዶ | ትርጉም አለው

የቀሲስ አክሊል ዳምጠው ክስ ጉዳይ...!

ቀሲስ አክሊል ዳምጠው ከወራት በፊት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ተፈጥረው የነበሩ ወቅታዊ ችግሮችን ለመፍታት በጠቅላይ ቤተክህነት ፅ/ቤት የተቋቋመ አቢይ ኮሚቴን በሰብሳቢነት እንዲመሩ የተመረጡ እጅግ የተከበሩ አባት ናቸው። ከሰኞ ግንቦት 14 ጀምሮ በቁጥጥር ስር ውለው ይገኛሉ።

ቀሲስ አክሊል ዳምጠው ተጠርጥረው የተያዙበትን የወንጀል ክስ የያዘ ወረቀት ተመለከትኩ፣ እንዲህ ይላል:

- የራሱን የፖለቲካ አላማ በማራመድ ህዝብ በመንግስት ላይ እምነት እንዳይኖረው በማድረግ

- ህገ-መንግስቱን እና ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን በሀይል ለመቀየር

- ህዝብን አሳምፆ መንገድ እንዲዘጋ በማድረግ

- የስራ ማቆም አድማ በመቀስቀስ

- በተቀናጀ መልኩ የፖለቲካ ቅስቀሳ በማድረግ

- ተከታታይ እና ቀጣይነት ያለው አመፅ በማድረግ እና

- ለሁከት እና ብጥብጥ ድርጊት ማስፈፀሚያ የሚሆን በውጭ ሀገር እና በሀገር ውስጥ ገቢ እንዲሰባሰብ በማድረግ

- ህዝብ ለአመፅ እንዲነሳሳ በማድረግ

- ፅንፈኝነትን በማስተጋባት

- የፖለቲካ ተከታዮችን መመልመል እና ማደራጀት

- (ይቺ ታስቃለች...) ወታደራዊ ስልጠና እንዲሰለጥኑ በማድረግ

- የጦር መሳርያ በማስታጠቅ

- የታጠቁ ፅንፈኛ ሀይሎችን በተለያዩ መንገድ በመገናኘት ተልዕኮ መስጠት

- ወደ አዲስ አበባ ከተማ እና ሌሎች ቦታዎች ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር መንቀሳቀስ።

@EliasMeseret