Get Mystery Box with random crypto!

'ውረሱት!' - የዛሬ አመት ተኩል ገደማ በብር ቅየራ ወቅት የገንዘብ ዝውውርን ለመቆጣጠር ሲባል | ትርጉም አለው

"ውረሱት!"

- የዛሬ አመት ተኩል ገደማ በብር ቅየራ ወቅት የገንዘብ ዝውውርን ለመቆጣጠር ሲባል የፀጥታ አካላት ከጎረቤት ሀገራት በድብቅ የሚገቡ ኖቶችን ውረሱ ተብለው ነበር። በዚህም በርካታ የሶማሌ ክልል አርብቶ አደሮች ሶማሌላንድ ሀገር ግመሎችን ሸጠው ሲመለሱ ገንዘባቸው ተወስዶባቸው ነበር። ከጅቡቲም፣ ከኬንያም፣ ከሶማልያም፣ ከሱዳንም የሚመለሱ ዜጎች የዚህ ሰለባ ሆነው ነበር።

- ነዳጅ ከኢትዮጵያ አውጥተው ወደ ጎረቤት ሃገር ወስደው የሚሸጡ ዘራፊዎች እንዳሉ በመንግስት ከሁለት ወር በፊት ተገልጾ ነበር። ይህን ለመከላከል የሁሉም ክልል ሚሊሻዎች፣ ልዩ ሃይሎች እና ፖሊሶች ከሃገር የሚወጣ ነዳጅ ካገኛችሁ ነዳጁንም ቦቴውንም ውረሱ ተብለው ነበር። በርካታ የነዳጅ ጫኝ መኪናዎች እና የጫኑት ነዳጅ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ድንበር አካባቢ ተገደው ጭምር እንዲሄዱ ተደርገው ከዛም በዚህ ትእዛዝ መሰረት ንብረታቻው ተወስዶባቸዋል።

- አሁን ደግሞ መቶ ዶላር እና ተመሳሳይ ምንዛሬ ያላቸውን የውጭ ገንዘቦች ይዞ የተገኘ ሁሉ እንዲወረስበት ትእዛዝ ተላልፏል። በግሌ ከላይ ከተጠቀሱት ሁለቱ የተለየ ውጤት አልጠብቅም። መንግስትም ሳያገኘው፣ ባለቤቱም ለፍቶ ያገኘውን ሳይጠቀምበት በጥቆማ በሚሄዱ ፈታሾች ይበላል።

በአጠቃላይ ግን "ውረሱት" የሚለው አካሄድ ለጉልበተኞች እና ህገ-ወጦች ሲሳይ ነው። በህግ መጠየቅ ሲያቅት ወደ "ውረሱት" መሄድ ህዝብን ይጎዳል።

@EliasMeseret