Get Mystery Box with random crypto!

#Somalia ሶማሊያ የአልሸባብ ከፍተኛ መሪ መገደሉን ገለፀች። የሶማሊያ መንግስት ለረጅም ጊዜ | TikvhaEthiopia

#Somalia

ሶማሊያ የአልሸባብ ከፍተኛ መሪ መገደሉን ገለፀች።

የሶማሊያ መንግስት ለረጅም ጊዜ ሲያፈላልገው የነበረው የአልሸባብ ከፍተኛ መሪ አብዱላሂ ናዲር በሶማሊያ ብሄራዊ ጦር እና በዓለም አቀፍ የፀጥታና ደህንነት አጋሮች በተካሄደ ኦፕሬሽን መገደሉን የሀገሪቱ መንግስት አሳውቋል።

የአልሸባቡ ከፍተኛ መሪ የተገደለው በመካከለኛው ጁባ ክልል ሃራምካ መንደር መሆኑ ተገልጿል።

አብዱላሂ ናዲር ከአልሸባብ መስራቾች መካከል እና ከፍተኛ አመራሮች አንዱ ሲሆን ሞቱን ተከትሎ የሶማሊያ መንግስት " እሾሁ ከሶማሊያ ህዝብ ላይ ተወግዷል " ሲል ገልጿል።

ከዚህ ቀደም ይህንን ግለሰብ ላገኘው / ለጠቆመ 3 ሚሊዮን ዶላር እንደሚሰጥ ተገልጾ ነበር።

በሌላ በኩል ፤ የፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ መንግስት በአልሸባብ ላይ እያካሄደ ያለውን መጠነ ሰፊ ዘመቻ የቀጠለ ሰሆን ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሞቃዲሾ የአልሸባብ መረብ በፀጥታ ኃይሎች በተሳካ ሁኔታ መበጣጠሱን እና የቡድኑን አተባባሪዎች፣ ተላላኪዎች እንዲሁም 5 የሚደርሱ ተከራተውበት የነበሩ ቤቶችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተገልጿል።

ምንም እንኳን በአልሸባብ ላይ የተከፈታው ዘመቻ ተጠናክሮ ቢቀጥልም ከሰሞኑን የየሞቃዲሾ ፖሊስ ኮሚሽነር ፋርሃን ሞሐሙድ አዳን በአልሻባብ መንገድ ዳር በተጠመደ የቦንብ ፍንዳታ ተገድለዋል።

በአልሸባብ ላይ እየተካሄደ ካለው ዘመቻ ጋር በተያያዘ ትላንት የሱማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ እያንዳንዱ ሱማሊያዊ አልሸባብ ለመዋጋት መሰለፍ አለበት ያሉ ሲሆን ከአልሸባብ ጋር በሚደረገው ፍልሚያ ገለልተኛ የሚባል አቋም ፈጽሞ ሊኖር አይችልም ብለዋል።

ፕሬዜዳንቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ ዜጎች ከአልሸባብ ጋር የሚደረገውን ውጊያ እየተቀላቀሉ መሆኑን አሳውቀዋል።