Get Mystery Box with random crypto!

#Ethiopia በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐ ግ | TIKVAH-ETHIOPIA

#Ethiopia

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐ ግብር ሊጀምር ነው።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው #መስከረም_ወር ጀምሮ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐግብር እንደሚጀምር አስታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው በቅደመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ተመርቀው የስራ ዓለም ውስጥ ለሚገቡ ተመራቂዎች ራሱን የቻለ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

ፕሮግራሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው " ይህ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጥ ነው " ብሏል።

" የፕሮግራሙ መጀመር በሥራ ገበያው ውስጥ ብቁ ሙያተኞችን ለማግኘትና የዩኒቨርሲቲውን አቅምና ብቃት ያለው ባለሙያ የማፍራት ተልዕኮ የሚያሳካ ነው " ሲል ገልጿል።

የሙያ ብቃት ማረጋገጫው #በሁሉም_ዘርፎች ላይ የሚሰጥ ሲሆን ይህ የሚመራበት አሰራር ይዘረጋል ተብሏል።

በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያሉ #ተማሪዎችም ሆኑ በስራ ገበያ ያሉ ሰራተኞችና ምሁራን ለተማሩበት ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ወይም #ፕሮፌሽናል_ሰርትፊኬት መውሰድ እንደሚችሉ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል። #ኢዜአ

@tikvahethiopia