Get Mystery Box with random crypto!

ቲሐርቃ ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ tihark — ቲሐርቃ ዜና
የቴሌግራም ቻናል አርማ tihark — ቲሐርቃ ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @tihark
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 202
የሰርጥ መግለጫ

ያልተሰሙና አዳዲስ ሁሉን አቀፍ መረጃወች
ለተጨማሪ ጥቆማ አስተያየቶች @Piyanki2020 ላይ ያናግሩን

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-25 21:24:56
25 views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 21:24:55
23 views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 20:09:34
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለታዬ ደንዳ የመደበለትን የግል እና የመኖሪያ ቤት ጥበቃዎቹን ማንሳቱን አስታውቋል።

ቲሐርቃ ዜና
53 views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 17:55:22
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሰርጌ ላቭሮቭ ካይሮ ገብተዋል

የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሰርጌ ላቭሮቭ በአራት የአፍሪካ ሀገራት የሚያደርጉትን ጉብኝት በግብጽ ካይሮ የጀመሩ ሲሆን በግብጽ ቆይታቸው ከግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲሰ እና ከአረብ ሊግ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከግብጽ ጉብኝታቸው ቀጥለው ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝትም የፊታችን ማክሰኞ ይጀምራሉ ተብሏል።

sputnik

ቲሐርቃ ዜና
54 views14:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 15:22:45
መንግሥት ኢኮኖሚው ውስጥ የሚለቀቀውን ገንዘብ እንዲቆጣጠር ተጠየቀ

የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር መንግሥት ኢኮኖሚው ውስጥ የሚለቀቀውን ገንዘብ እንዲቆጣጠር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን አሳስቧል። የአሶሴሽኑ የጥናትና የፖሊሲ ዳሰሳ ዳይሬክተር ደግዬ ጎሹ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ ባለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የሚለቀቀው የገንዘብ መጠን፣ የኢኮኖሚ የዕድገት ደረጃን ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በነዚህ ጊዜያት ውስጥ እስከ 44.4 በመቶ የሚያህል ገንዘብ ወደ ገበያ ሲገባ መቆየቱን ገልፀው ይህ ኃላፊነት የሚሰማው መንግሥት ያደርገዋል ተብሎ የማይጠበቅ ነው ብለዋል። መንግሥት የዋጋ ግሽበትን ለማረጋጋት የሚወስዳቸውን ዕርምጃዎች ማጤንና የሚሰጠውን ውጤት መለካት እንደሚገባ አክለዋል፡፡

አሁን ባለው ሁኔታ የብር የመግዛት አቅምን ማዳከም የሚሰጠው ጥቅም እስከተወሰነ ጊዜ መሆኑን መረጋገጡን በመግለጽ፣ ምርቶች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያደርጋል በሚል የተወሰደ ዕርምጃ ቢሆንም፣ ተመልሶ ሌላ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡ በሌለ በኩል የዋጋ ግሽበትና የኢኮኖሚ ዕድገት ማነቆዎች አንዱ ሙስና መሆኑን አክለዋል።

reporter

ቲሐርቃ ዜና
51 views12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 12:41:09
እኛም ኮራን በናንተ እንደ አዲስ ተሰርቶ ተለቀቀ

አትሌቶቻችን ለእናት ሃገራቸው ላበረከቱት ታላቅ ድል እኛም ኮራን በናንተ እንደ አዲስ ግጥምና ዜማው በጆሲ ኢን ዘ ሃውስ ተዘጋጅቶ ተለቋል። ሙዚቃ ቅንብሩን ደግሞ ካሙዙ ካሳ እና አበጋዝ ክብረወርቅ ሸዋታ ሲጠበቡበት አራት ድምጻዊያን ተሳትፈውበታል።

ድምጻዊያን ጀሲ ኢን ዘሃውስ፤ ጌድዮን ዳንኤል፤ ሃይማኖት ግርማ፤ ያሬድ ነጉና ጂ መሳይ በመሆን እንደ አዲስ ለኢትዮጵያ ህዝብ ላኮሩን አትሌቶቻችን አቀንቅነዋል።

እኛም ኮራን በናንተ

ቲሐርቃ ዜና
50 views09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 06:40:51
46 views03:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 19:50:24 የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ “በሩሲያ የተያዘው መሬት ሳይመለስ የተኩስ አቁም የለም” አሉ

ዘሌንስኪ አርብ ዕለት ከዎል ስትሪት ጆርናል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት ከሆነ የዩክሬን ግዛቶች በሩሲያ ኃይሎች ስር በሆኑበት የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረግ ጦርነቱን ማራዘም ነው ብለዋል፡፡የተኩስ አቁም ስምምነቱ የበለጠ ግጭት እንዲባባስ የሚያደርግና ሞስኮ ለቀጣዩ ዙር እንደገና ለማስታጠቅ እድል እንድታገኝ የሚያደረግ መሆኑም አክለዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡

“ህብረተሰቡ ሁሉም ግዛቶች መጀመሪያ ነጻ መውጣት እንዳለባቸው ያምናል፣ ከዚያም በሚቀጥሉት መቶ ዘመናት ምን ማድረግ እና እንዴት መኖር እንዳለብን መስማማት እንችላለን”ም ነው ያሉት ዘሌንስኪ። ዜለንስኪ አሜሪካ ለዩክሬን ስለሰጠቻቸው ከፍተኛ ተንቀሳቃሽነት ያላቸው ሮኬት አርቲለሪ ሲስተምስ (HIMARS) ሲናገሩም “የምዕራባውያን የሮኬቶች አቅርቦቶች ምንም እንኳን ጠቃሚ ቢሆኑም፤ ዩክሬን የተጋረጠባትን መዕበል ለመቀልበስ ከሚያስፈልጋት ድጋፍ አንጻር በጣም ያነሱ ናቸው” ብለዋል።

አሁን አንገብጋቢው ነገር የሩሲያ የረዥም ርቀት የሚከላከል የአየር መከላከያ ሲስተም ማግኘት ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ዎል ስትሪት ጆርናል የዜለንስኪን አስተያየት በመጥቀስ “ከሩሲያ ፌዴሬሽን ጋር ያለውን ግጭት ማቀዝቀዝ ማለት የሩስያ ፌደሬሽን እስትንፋስ እንድታገኝ መፍቀድ እንደማለት ነው” ሲል ጽፏል።

ሩሲያ እና ዩክሬን የዩክሬን ጥቁር ባህር ወደቦች ለእህል መላክ ለመክፈት የሚያስችል አስደናቂ ስምምነት አርብ እለት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

ቲሐርቃ ዜና
50 viewsedited  16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 19:37:12
ሰበር

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ዓለም አቀፍ ድንገተኛ አደጋ ሲል ዛሬ አወጀ።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ድርጅታቸው የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ዓለም አቀፍ ድንገተኛ አደጋ ሲል ማወጁን አሳውቀዋል።

#AFP
45 views16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 16:59:50
46 views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ