Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱስ ድልድይ/kidus bridge

የቴሌግራም ቻናል አርማ thorniter — ቅዱስ ድልድይ/kidus bridge
የቴሌግራም ቻናል አርማ thorniter — ቅዱስ ድልድይ/kidus bridge
የሰርጥ አድራሻ: @thorniter
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 343
የሰርጥ መግለጫ

public channel

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2020-07-31 05:03:17 ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ማስመሰሌ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በእርግጥ…..ስስቅ አይተውኛል፤ በደስታ ስቦርቅ ስጮህ ሰምተውኛል። ሀዘንና ጭንቀት ይጋባል ስላሉኝ፤ በሽታዬን ለሌላው እንዳላጋባ፤ የውስጤን ደብቄ ደስተኛ መስዬ መታየት ጀመርኩኝ። የማስመስለው ደስተኛ መስዬ በመታየት የሰዎችን ክብር እንዳገኝ አልነበረም፤ የማስመስለው በእኔ ሀዘንና ጭንቀት ሌሎች እንዳይጨነቁ በማሰብ ብቻ እንጂ። ከዚህ በላይ ለሌሎች የሚሰጥ ምን ስጦታ አለ? የእናትነትን ፍቅር ከሌሎች ፍቅር በላይ የሚያደርገው እኮ የማስመሰል ሀይል ስላለው ነው።የእናት ፍቅር ትልቅ የማስመሰልን ጥበብ ያላብሳል፤ ውስጥ እያለቀሰ ጥርስ በልጅ ፊት ይስቃል፤ ሆድ እየጮኸ እጅ ልጅን ያጎርሳል፤ ልብ እየተከዘ ግን ልጅን ያባብላል። እኔም ትክክለኛው ስጦታ መሰለኝና ተቀበልኩት።
.................ቶ............................
ሀዘኔን ደብቄ ደስተኛ መስዬ መታዬት ጀመርኩኝ። ቢያንስ የኔ መከፋት እንዳያስከፋቸው፤ ለሌላ ሰው ጭንቀት እንዳልሆን በማሰብ። በእኔ ላይ የዳመነው የሀዘን ደመና እንዳይዘንብባቸው የማስመሰል ጸሃዬን በላዬ አኖርኩኝ። በፊታቸው እየሳቅኩኝ እንባዬን ለማታ ማቆየት ጀመርኩኝ። ለሚጠይቁኝ ነገር ሁሉ ምላሼ ተመስገን ሆነ፤ በማስመሰሌ ብዙ ገፋሁበት። ከጊዜ በኋላ ግን እነሱ ከሳቁት በላይ መሳቄን ሲያዩ፤ ሀዘንና ደስታዬን ከገጽታዬ ሲያጡት፤ ቀንና ማታ መልሴ ተመስገን ሲሆንባቸው …… አመኑኝ!!! የምስቀው ከልቤ፤ ተመሰገን የምለው ሁሉ ነገር ሞልቶልኝ እንደሆነ አመኑ።
......................ቶ..............................
ማስመሰሌ እውን ሆኖ ያስከፋኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። ከዚህ ሁሉ ማስመሰል በኋላ ዛሬ ከልባቸው ሲያምኑኝ ግን ከፋኝ። እርስ በእርሳቸው ሲተዛዘኑ፤ እኔ ግን ሁሉ እንደተሟላለት ሰው አይዞኝ የሚለኝ ጠፋ ። ለረጅም ጊዜ የገደብኩት እንባ መፍሰስ ሲጀምር፤ ብዙ ከመሳቅ የመጣ እንጂ የሃዘን እንባ መሆኑን መረዳት አቃታቸው። ተመስገን ስል ይሰሙኝ ስለነበረ፤ ዛሬ ከምር ከፍቶኛል ስላቸው ሀዘን እንደማልችል ደካማ ቆጠሩኝ፤ “ዛሬ ገና ቀን ቢጎድል የምን እንዲህ ማማረር ነው” ብለው ተሳለቁብኝ። ማስመሰሌን አመነው አስቤው በማላቀው መጠን አስከፉኝ።
......................ቶ...............................
ስስቅ የከረምኩት ደስታ ለሰው የሚሰጥ ስጦት ስለመሰለኝ እንጂ እኔም እኮ እንደነሱ ይከፋኝ ነበር። ተመስገን ስል የከረምኩት እኮ ሳይጎድልብኝ ቀርቶ አልነበረም፤ እንዳላሳስባቸው ጭንቀት እንዳልጨምርባቸው ብዬ እንጂ። ። ሲላቀሱ አብሬ ያላለቀስኩት እኮ ሀዘናቸው ላይ ሀዘን እንዳልጨምር ነበር። የሆኑትን ሁሉ እኔም ሆኜ ሳለ ማስመሰሌን አምነው ዛሬ አስከፉኝ።
.....................ቶ............................
የማስመስለው እንዲያምኑኝ አልነበረም? ወይስ የማልችለውን መንገድ ነበር የጀመርኩት? ዛሬ ሁሉ ነገር የማስመሰል ገደቡን ጥሶ ሲያልፍና እኔም እንደነሱ አይዞኝ መባል ሲያምረኝ፤ በቸልታ አለፉኝ። ይሄኔ ነው ማስመሰሌን እንዳመኑት የገባኝ። ያንን ሁሉ የማስመሰል ጥረቴን እረስቼ፤ “ሰው እንዴት በቀላሉ ያምናል?” እያልኩኝ ይኸው ወቀሳ ጀምሬያለው። ሺህ ጊዜ ብስቅ እንዴት “እውነት ከልብ የመነጨ ሳቅ ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ይጠፋል? ሺህ ጊዜ ተመስገን ብል “ይህ ማመስገን የእውነት ነው?” ብሎ የሚሞግት እንዴት ይጠፋል። አንዳንድ ሰው የሚያስመስለው እንዲታመን ሳይሆን የሚሞግተው ሰው እየፈለገ ቢሆንስ?
..... .. . .......ቶ..............

በቅንነት ሼር ያድርጉልን

1.6K viewskidus Ayalneh, 02:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-07-25 17:48:29
1.5K viewskidus Ayalneh, 14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-07-25 17:48:19 ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ልጅ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ብዙዎች፣ የኑሮ ሽክም ጭንቅላታቸዎነ አዝሮት፡ የኑሮ ጫማ ጠቧቸው ፡የቤት ኪራይ የወር አስቢዛ ጉሮሮዎን አንቆ ይዞት ፡ሚስት እያገቡ ልጅ ሲወልዱ ተመልክቻለሁ፡፡
በዚህ ጊዜ፣ የኑሮ አውሬ እንደ ቀን ጅብ ሁሉንም እየነከሰ ባለበት ሁኔታ፣ ልጅ መውለድ ራስ ወዳድነት ነው ብዬ አስብ ነበር፤ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ፡፡
‹ከእጅ ወደ አፍ› ሳይሆን፣ እጅ ታስሮ አፍ ብቻ በሚያዛጋበት የኢኮኖሚ አቅም፣ ሌላ አፍ መጨመር እብደት ይመስለኝ ነበር፤
.........................ቶ.........................
ተሳስቻለሁ:: ለካ ልጅ ከቤት እና ከገቢ በፊት ያስቀደማችሁት፣ ለምታደርጉት መፍጨርጨር, ምክንያት እንዲሆናችሁ ነው፡፡ ልጅ ለካ
ለመኖር ምክንያትን የሚፈጥር ፡የአንተነተህ ነፀብራቅ፡የደመህ ቅጅ
መፍጨርጨርን ለማነሳሳት የሚያገለግል፣ ለመኖር ምክንያትን የሚፈጥር ነው፡፡
ሕይወት መፍጨርጨር በሆነበት ሀገር፣ ልጅ “ማፍጨርጨሪያ” ነው፡፡ እልህ መቀስቀሻ፣ የማታገያ፣ ሮጥ-ሮጥ ማድረጊያ ክኒን ነው፡፡
ጫት ማቆም ያቃታቸው፣ ሲጋራ ላይ መወሰን የተሳናቸው፣ መጠጥ ገንዘባቸውን የመጠጠባቸው ሰዎች፣ ልጅ በመውለድ ሱሳቸውን ሲያቆሙ አስተውዬ ተደስቻለሁ:: ልጅ መፍጨርጨሪያ ብቻ ሳይሆን “Rehab for Addiction” ጭምርም ነው፤ ከሱስ ብዛት ከመጣ የጤና እጦት ምክንያት የቀረበ ሞታቸውን፣ ልጅ በመውለድ ራሳቸውን የሰበሰቡ ብዙ ናቸው፡፡
ልጅ፡- ፣ ወጥሮ ለመኖር የሚያስገድድ መወጠሪያ፣ ማፍጨርጨሪያ፣ የአንተነትህ ነፃብራቅ፣ የስኬትህን ጫፍ ማያ፡የየተበታተነ ሀሳብን መሰብሰቢያ፣ .. .........ልጅ.................
...................( ልጁ ከተወለደ በኋላም ወላጅ መፍጨርጨር ያቃተው ከሆነ፣ አሊያም ተፍጨርጭሮ ድሮ ከነበረበት ምንም ፈቅ ማለት ከተሳነው፣ ልጅ እራሱን እና ቤተሰቡን የማሰደግ ሀላፊነት ትከሻው ላይ መወደቁ አይቀርም.......ምስኪን ልጅ!!!!) #pls በልጁ የሚያድግ አባት እንዳትሆን!!!!!!!!!!!!
...............................................................
Telegram ሊንኩን በመጫን join ያድርጉን
https://t.me/joinchat/AAAAAFcpteqk7o_S4OcJlQ
1.6K viewskidus Ayalneh, 14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-07-19 13:21:32 ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ጭንቀት፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ጭንቀትን ለማብራራት የታላላቅ ምሁራንን ስም ባለመጥቀሴ አትቀየሙኝ። ይብዛም ይነስ ጭንቀት ያላንኳኳዉ ልብ ያልነካዉ ማህበረሰብ የለም። ታዲያ በራሴ ችግር ለምን ብየ ባለሙያ ልጋብዝ? የቤቴን ገበና ከእኔ የበለጠ ማን ሊያዉቅ ይችላል? ይህንን አስቤ እኔ የራሴን አመለካከት ፅፌያለሁ።
ጭንቀት ማለት ደስታ ማጣት ነዉ። ጭንቀት ማለት አሁን ባለህ ህይወት ደስተኛ አለመሆን ነዉ። ጭንቀት ማለት ዉስጣዊ ሰላም ሲርቀን ነዉ። ጭንቀት ማለት መረጋጋት አለመቻል ነዉ። ጭንቀት ማለት የምያባራ ግራ መጋባት ነዉ። ጭንቀት ማለት እበድ፣ እበድ የሚል ስሜት ነዉ። ጭንቀት ማለት እንቅልፍ ሲከዳ ማለት ነዉ። እንቅልፍ የመንፈስ መረበሽ ነዉ። ጭንቀት ማለት የፍላጎት መጥፋት ነዉ። ጭንቀት ማለት የተዘጋ ቤት ዉስጥ የተቀመጡ ያህል ሲሰማን ነዉ። ጭንቀት ማለት በራስ ተስፋ መቁረጥ ነዉ። ጭንቀት ማለት ሞትን መመኘት ማለት ነዉ። ጭንቀት ማለት የህይወት አቅጣጫ መቃወስ ነዉ። ጭንቀት ማለት ወዴት እንደሚሄዱ አለማወቅ ነዉ። ጭንቀት ማለት ሳቅ ሲርቅ ማለት ነዉ። ጭንቀት ማለት ለምን የሚለዉን እንኳ አለማወቅ ነዉ። ጭንቀት ማለት የማይለቅ ራስ ምታት ማለት ነዉ። ጭንቀት ማለት ያለማቋረጥ በሃሳብ መናወዝ ነዉ። ጭንቀት፤ መፍትሄ ልታገኝላቸዉ ያልቻልካቸዉ የእነዚህ ሁሉ መጥፎ ስሜቶች ድምር ዉጤት ነዉ።
ይህንን የግል ስሜትህን ካንተ ዉጭ ሌላ ምንም ሰዉ ሊያብራርልህ የሚችል ሰዉ የለም። ጭንቀትህ ለአንተ ብቻ ነዉ ትልቅ ስሜት ሊሰጥ የሚችለው። የአንተ ጭንቀት ለእኔ ቅንጦት ሊሆን ይችላል። እኔን የሚያስጨንቀኝ አንተ በፍቅር የምትከታተለዉ ቋሚ መዝናኛህ ይሆናል። ስለዚህ ዉበት እንደተመላካቹ ነዉ ወይንም ህልም እንደፈችዉ ነው እንደሚባለዉ ሁሉ ጭንቀት እንደተጨናቂዉ ነዉ በሚለዉ ተስማምተን ይህንን በደንብ ያልታወቀ የህሊና ወረርሺኝ የምናስወግድበትን መንገድ ለምን አንነጋገርም?????
# በጭንቀት ስትረበሹ ምን ነው የምታደረጉት? ????
#ምን በማደረግ ነው ከዚ ሰሜት የምትወጡት?????????????
.....................ቶ..................................
Telegram ሊንኩን በመጫን join ያድርጉን
https://t.me/joinchat/AAAAAFcpteqk7o_S4OcJlQ
1.5K viewskidus Ayalneh, 10:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-07-19 13:21:14
1.3K viewskidus Ayalneh, 10:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-29 18:38:29
 ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ስህተትን መዳኘት፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
 የሌሎችን ስህተት መዳኘቱ ቀላል ሲሆን የራሳችንን ድካም ማስተዋሉ ደግሞ ከባድ ነው፡፡ ቀላሉ ሳያገናዝቡ ማውራት ሲሆን ከባዱ ደግሞ ምላስን መግታት ነው፡፡ የሚወደንን ሰው መጉዳት ቀላል ሲሆን የሚከብደው ደግሞ ያንን ቁስል ማዳኑ ነው፡፡ ሌሎችን ይቅር ማለት ቀላል ሲሆን ይቅርታን መጠየቅ ግን ከባድ ነገር ነው፡፡ ሕጎችን ማውጣት ቀላል ሲሆን እነርሱን መከተሉ ደግሞ ከባድ ነገር ነው፡፡ ቀላሉ በእያንዳንዱ ምሽት ማለሙ ሲሆን ከባዱ ደግሞ ለስኬታማነቱ መዋጋት ነው፡፡
....................ቶ..........................
https://t.me/joinchat/AAAAAFcpteqk7o_S4OcJlQ

በቅንነት ሼር ያድርጉልን

1.3K viewskidus Ayalneh, 15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-29 18:04:24
ማንም ነፃነትን አይሰጥህም።
ማንም እኩልነትና ፍትህን
አይሰጥህም። ወንድ ከሆንክ
ራስህ ትወስደዋለህ።
..................ቶ........................
Telegram ሊንኩን በመጫን join ያድርጉን
https://t.me/joinchat/AAAAAFcpteqk7o_S4OcJlQ
1.2K viewskidus Ayalneh, 15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-29 08:23:51
፡፡፡፡፡፡አትድረስ አይደርሱብህም!፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ከክፋት ራቅ፤ ክፉዎች ካንተ ይርቃሉ።
ከተንኮል ከራቅክ ተንኮለኞች ካንተ ይርቃሉ።
ከዉሸት ከራቅክ ዉሸታሞች ከአጠገብህ አይደርሱም።
አንተ የማታስመስል ከሆነ አስመሳዮች ከህይወትህ ይወጣሉ።
ከስርቆት ከራቅህ ሌቦች በዙሪያህ አይኖሩም።
ከአፍ እላፊ ከሸሸህ ተሳዳቢዎች አይደርሱብህም።
ከከንቱ ከዉዳሴ ከራቅህ ሸንጋዮች አያዩህም።

ወሬ ከወደድክ ግን ወሬኞች በርህ ድረስ ይመጣሉ።
ዘር ከቆጠርክ ደምህን በባቄላ ቆጥረዉ የሚደርሱ ሰዎችን ከጉያህ ትወልዳለህ።
ክፉዉ ትኩረትክን ከሳበዉ፣ ከዚህ የከፋ ርኩሰት ይገጥምሃል።
ወንድሜ፤
አትድረስ፤ ማንም አይደርስብህም።
አትንካ፤ ማንም አይነካህም።
አትፍረድ፤ ማንም አይፈርድብህም።
አትተች፤ ማንም አይተችህም።
ሃያዉን ሳናውቅ በልጅነት፣ ሃያውን ሳንበስል በወጣትነት፣ ሃያዉን በብስለት በሽምግልና ሃያዉን ደክመን በእርጅና ለምናሳልፈዉ ከንቱ 80 እድሜያችን ከክፋት ሸሽተን ከመኖር ዉጪ ሌላ ምን አማራጭ አለን?
አትድረስ፤ ማንም አይደርስብህም!
✦✦ ✦✦
ሊንኩን በመጫን join ያድርጉን
https://t.me/joinchat/AAAAAFcpteqk7o_S4OcJlQ
1.3K viewskidus Ayalneh, 05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-26 14:51:47
ዕውነት ነው፡፡ ሞት የሚጀምረው ሰው፤“ተስፋ የለኝም” ብሎ ማሰብ የጀመረ ጊዜ ነው፡፡ በተስፋ ጊዜ ይገዛል፣ በጊዜም ጊዜ ይቀየራል፡፡ የማይቀየር፣ የማይለወጥ ነገር የለም፡፡ ቢኖርም ራሱ “ለውጥ” የሚባለው ነገር ብቻ ነው፡፡… “Change is the unchanging reality” እንዲሉ፡፡
..............................................................
https://t.me/joinchat/AAAAAFcpteqk7o_S4OcJlQ
1.3K viewskidus Ayalneh, 11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-26 14:49:46
የስልጣኔ ምንጩ እውቀት ነው። ያወቀ ሰው ደግሞ ስልጡን ነው። እርግጥ ምሁራን የተባሉ ሁሉ አውቀዋልና ስልጡን ናቸው ማለት ነውር ቢሆንም።
............................ቶ.................,,,
https://t.me/joinchat/AAAAAFcpteqk7o_S4OcJlQ
1.2K viewskidus Ayalneh, 11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ