Get Mystery Box with random crypto!

ለማርያም ክብር ገና እዘምራለሁ21

የቴሌግራም ቻናል አርማ theorthodox21 — ለማርያም ክብር ገና እዘምራለሁ21
የቴሌግራም ቻናል አርማ theorthodox21 — ለማርያም ክብር ገና እዘምራለሁ21
የሰርጥ አድራሻ: @theorthodox21
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.91K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የመዝሙር ግጥሞች እና መፈስን የሚያድሱ መዝሙሮችን መንፈሳዊ ጽሁፎችን
እንዲሁም ህይወትን ይሚለዉጥ መልካም የሆነውን መልዕክት ወደናተ እናደርስ አለን !! @Theorthodox21 ይቀላቀሉን !!
ለማነኛዉም ሀሳብ እና አስተያየት @TiGi21
እንዲሁም መንፈሳዊ መልእክት ማስተላልፍ ለምትፈልጉ
@TiGi21/ @Abraham912 ይላኩልን
እግዚአብሔር ይመስገን !!

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-22 16:04:57

983 views13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 08:37:00 ግንቦት አንድ በዚህችም ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች::

እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኅነት የሆነባት ናት::

ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ::

ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ በዚያ ወራት የመካኖችን መባዓ ካህናቱ አይቀበሉም ነበር::

እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኀዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር::

ሰውን የሚወድ እግዚአብሔር ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ኀሳባቸውን ተመለከተ::

ክቡር ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው::

በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት:: ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገኑት::

የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርግ ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች::

ከዚህም በኋላ ይቺን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች ስሟንም ማርያም ብላ ሰየመቻት ትርጓሜውም እመቤት ማለት ነው::

ደግሞም ሀብትና ሥጦታ ማለት ነው:: በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ናት:: ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነት ያገኘንባት::

እንግዲህ እዚህ ጋር ልብ ይሏል::

በዚህ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም መወለድ የኛ ልጅነት የኛ የመዳንችንን መንገድ እግዚአብሔር እንዴት እንዳከናወነልን እንረዳለን::

እግዚአብሔር ሰውን ሲያድን ማዳኑን የፈጸመው እጅግ በጣም ልዩ በሆነ ሁኔታ ነው::

ይህም ገናናነቱን ከእኛ ታናሽነት ጋር አዋሕዶ፤ ከሃሊነቱን ከእኛ ነፃነት ጋር አስማምቶ በመሆኑ ነው::

ይህ ማለት ምን ማለት ነው?

ሊያድነን ሲነሣ እንዲሁ በማንኛውም መንገድ ቢያድነን ታላቅ ቸርነትና ደግነት ሆኖ ሳለ እርሱ ግን ከዚያም በላይ በሆነ መንገድ እኛን አሳትፎ ፈቃዳችንን ተቀበሎ አስፈቅዶ አስወድዶ ያዳነን::

እርሱ ሁሉን ማድረግ ስለሚችል ብቻ ያለ እኛ ፈቃድ ሱታፌ እንዲሁ አፍአዊ በሆነ ሁኔታ እና ያለ ፈቃዳቸው አላዳነንም::

ባሕርያችንን ሲዋሐድም ያለ እኛው ፈቃድና ሱታፌ አላደረገውም:: የሚጠቅመንን የመዳናችንን ነገር ሲፈጽም እኛን አስወድዶና አሳትፎ ነው::

አካላዊ የእግዚአብሔር ቃል እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት ሲወርድ መከራ ተቀብሎ እኛን የሚያድንበትን መሣሪያ የወሰደው ከእኛው መዳኑ ከሚያስፈልገንና ከሚደረግልን ከሰዎች ነበር::

ይህ እንዲሆን ደግሞ ሰዎችን የሚወክልና እኛን ሁሉ ወክሎ የሚሳተፍ አንድ ሰው ያስፈልግ ነበር::

በዚህም ያ የሚያስፈልግ አንድ ሰው በዛሬዋ ቀን የተወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት:: በእወነት ምስጋና ይድረሳትና።

ከዚህ በኋላ ነው እንግዲ የነቢያት ትንቢታቸው ከተፈጻሚነት የደረሰው:: ታዲያ የዛሬውን በዓል ስናከብርና ተድላ ደስታ ስናደርግ ከመንፈሳዊነት ሳንወጣ ልንጠነቀቅ ይገባል::

ይህን በዓል ስናከብርም ሌሊት በቤተ ክርስቲያን በማኅሌት÷ በዝማሬ÷ ጠዋት በኪዳንና በቅዳሴ÷ ታምሯን በመስማት÷ ወንግል በመማር ነው:: ክርስቲያኖች ከዚህ የወጣ ባዓል የላቸውም::

ብዙዎች የእኛን መንፈሳዊ በዓል ይዘው የራሳቸውንና የቤታቸውን ጣጣ ይዘውና አስታከው መንፈሳዊ በዓላ ላይ ለጥፈው ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንም ከመንፈሳዊነታችን ጋርም የሚፃረር ነገር ሲፈጽሙ ይታያል ይህ አግባብ አይደለም::

የበግና የፍየል ከለር እየመረጡ÷ ቄጣና ፈንዲሻ እየረጩ÷ የቡና አተላ እየገለበጡ የሚከበር መንፈሳዊ በዓል የለም:: አስፀያፊም የተወገዘም ግብር ነው።

እስኪ አንድ በዓለም ያለ ሰው ልደቱን ሲያከብር ወይ ሲደግስ የበግ ከለር መርጦ የሚያርድ ማን አለ? ወይ ቡና እያንቃረረ ቂጣና ፈንዲሻ በየጥጋ ጥጉ የሚጥል ማን አለ? ታዲያ እንደዚህ ያለን ኮተታ ኮተት ከየት የመጣ ነው::

የኛ አይደለም እንዲህ ያለ ነገር እንዲህ የሚያደርጉ ካሉ ፈጥነው ንሰሐ ሊገቡና ከክርስቲያኖች ማኅበር ሊገቡ ይገባል::

የእመቤታችንን የልደቷን በዓል ግን የምናከብረው በዝማሬ÷ በማኅሌት÷ በኪዳን÷ በቅዳሴ ጊዜ ሥጋወ ደሙ እየተቀበልን÷ ወንጌልን እየተማርን÷ የተራበ እያበላንና የታረዘ እያለበስን እየዘመርን ነው::

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን።
@ethiopianorthodoxs
1.2K views05:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 08:10:39 የዕለቱ መልእክት፦
(ያዕ 2 )
------------
23 መጽሐፍም፦ አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ።

24 ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ።

25 እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?

26 ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።

@ethiopianorthodoxs
1.0K views05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 20:00:00 አለምን እየመራት ያለው ሰይጣን ማን ነው?

“ወደድንም ጠላንም ህይወታችን ለፈጣሪ ባለን የምስጋና መጠን ይወሰናል። ህይወታችንን እጅግ መልካም ለማድረግ አልያም እርግማን ወደሞልው የሰቀቀን ኑሮ ለመለወጥ የሚያስችለን የገዛ አመለካከታችን ነው። አንዳንዶቻችን በቤታችን ጓሮ የተተከለውን ጽጌሬዳ ስንመለከት ጽጌሬዳው በእሾህ መወረሱ ያበሳጨናል፤አንዳንዶች ደግሞ እሾሁ ጽጌሬዳ ማብቀሉ ይገርማቸዋል። ሁሉ ነገር እኛ በሚኖረን የህይወት መነጽር ይወሰናል።...ሙሉውን ለማንበብ
882 views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 08:44:11 ✞ዕለተ_ዓርብ✞
* መስቀል በቁሙ መስቀያ፣ መመዘኛ፣ መሰቀያ፣ መንጠልጠያ፣ ለሞት የሚያበቃ መከራ በማር 8:34

ወጸውዖሙ ለሕዝብ ምስል አርዳኢሁ ወይቤሎሙ
ዘይፈቅድ ይፀመደኒ ይጽልአ ለነፍሱ ወያጥብዕ ወይፁር መስቀለ ሞቱ ወይትለወኒ፤ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ሕዝቡን ጠርቶ እንዲህ አላቸው።
ሊከተለኝ የሚወድ ሰው ራሱን ይካድ፤ ጨክኖም የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ ይላል።

* ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በ /1ኛ ቆሮ. 1:17/ ላይ ወኢኮነ በጥበበ ነገር ከመ ኢንስዐር፤ መስቀሉ ለክርስቶስ የክርስቶስን መስቀሉን ከንቱ እንዳናደርግ ነገርን በማራቀቅ አይደለም ይላል።

* ጌታችን በተሰቀለ ዕለት ከስድስት ሰዓት ጅምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ
፩.በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ። /ፀሐይ ጨለመ/
፪.ጨረቃ ደም ሆነች
፫.ከዋክብትን ረገፉ እንሆም
፬.የቤተ መቅደስ መጋረጃም ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፤
፭.ምድርም ተናወጠች፤ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤
፮. መቃብሮችም ተከፈቱ፤
፯.ሙታን ተነሱ ተኝተውም ከነበሩት ቅዱሳን ብዙዎች ተነሱ፤ ከትንሳኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ለብዙዎች ታዩ። /ማቴ 27:51/

* ጌታችን ለዓለሙ ያሰበውን ቤዛነት ሊፈጽም በመስቀል ላይ መሰቀሉ የሚታሰብበት ነውና ለስቅለቱ መታሰቢያ የሚሆን አጎበር ተዘጋጅቶ
ከርቤ እየታጠነ ስቅለቱን የሚመለከት ምንባባት ሲነበብና ሲሰገድ ይዋላል። የሰው ልጅ በሙሉ በእግረ አጋንንት ተረግጦ ከፈጣሪው ተጣልቶ ለ5500 ዘመን በጨለማ መኖሩን ለማስታወስም መንበሩ ታቦቱ በዚህ ቀን በጥቁር ልብስ ይሸፈናሉ። ዲያቆኑም በቤተ ክርስቲያን በመዞር የሚያሰማው የቃጭል ድምጽ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለቅሶ አንድም ዋይ ዋይ እያሉ የተከተሉት የኢየሩሳሌም ሴቶችን ሙሾም ምሳሌ ነው። /ሉቃ 23:31/

✞. በዕለተ አርብ ነፍሳት ከሲኦል ወጡ። አንቀጸ ገነት ተከፈተልን፣ ርስተ መንግስተ ሰማያት ተመለሰችልን፣ አባታችን አዳምም ከፈጣሪው ጋር ታረቀልን በማለት ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሳኤሁ አግሃዶ እያልን የተድላ፣ የደስታ ምልክት ወይም መገለጫ የሆነ ልምላሜ ያለውን ቆጽለ ሆሳዕና ወይም ቄጤማ ግጫ ይዘን የምስራች እንባባላለን። /ኤፌ. 2:15-15/ ወዘእንበለ ምሳሌሰ ኢተናግሮሙ፣ ያለ ምሳሌ አልተናገረምና እንዳለ /ማቴ 13:34-35/ በኖኀ ጊዜም ርግብ ሐጸ ማየ አይኀ፣ ነትገ ማየ አይኅ፣ የጥፋት ውኃ ጎደለ፣ አለቀ እያለች ቅጠል
ዕፅ ዘይት ይዛ ለኖኀ አብስራዋለች። /ዘፍ 8:8-11/

* ርግብ የካህናት፣ ኖኀ የምእመናን፣ ኖኀ እጁን ዘርግቶ ርግብን እንደተቀበላት ካህናትም በየመንደሩ እየዞሩ ክርስቶስ ተመረመረ ዲያብሎስ ታሰረ በማለት ቄጤማ ሲያድሉ ምእመናንም እጃቸውን
ዘርግተው መቀበላቸው የዚህ ምሳሌ ነው። ስለዚህ አሁንም ቢገኝ የወይራ ልምላሜ ቢታጣ ግጫን እየታደልን የምስራች መባባላችን ነፍሳት ከሲኦል ለመውጣታቸው መታሰቢያ ነው።

ሳይገባን በቸርነቱ በፊቱ ስንሰግድ ሥጋችንን በማድከም ለፈቃደ ነፍስ ማስገዛት አንዱ ዓላማ ሆኖ እኛን ከሀጥያት ባርነት ነጻ ለማውጣት አምላካችን የዋለልንን የፍቅር ውለታ፤ የሰማዕታትን መከራ፤ በጠቅላላው የፈጣሪያችንን አሰረ ፍኖት ተከትለው የተቀበሉትን መከራ እንዲሁም ሀጥያታችንን እያሰብን መስገድ ተገቢ እንደሆነ ቅድስት ቤተ ክርስትያን ታስተምራለች፡፡
@ethiopianorthodoxs
776 views05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-21 09:56:34 ✞ሐሙስ✞

* ከስቅለትና ከትንሣኤ በፊት ያለው ሐሙስ በቤተክርስቲያናችን የተለያዩ ስያሜዎች አሉት።
1. ሕጽበተ እግር ይባላል።
ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት ነው። ይህም የሚያሳየው የዓለምን ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው። ይህንን ለማስታወስ ዛሬ ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝቡን ኃጢአት እጠብ ሲሉ በቤተ ክርስቲያናችን የተገኙትን ምእመናን
እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ሲያጥቡ ያረፍዳሉ። / ዮሐ.13:4-15/
2. የጸሎት ሐሙስ ይባላል።
የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ የሚደክም ሥጋን የተዋሐደ አምላክ ፍፁም ሰው መሆኑን ለመግለጽና ለአርአያነት አይሁድ መጥተው እስኪይዙት ድረስ በጌቴሴማኒ ሲጸልይ በመቆየቱ ነው /ማቴ26:36 ፤ ዮሐ 17:1/
3. የምስጢር ቀንም ይባላል።
ከሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን አንዱ በዚህ ዕለት ተመስርቷል። ይኸውም ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ስጋዬ ነው፤ እንካችሁ ብሉ ጽዋውንም አንስቶ አመሰገነ ይህ ስለ እናንተ ነገ
በመስቀል ላይ የሚፈስ ደሜ ነው፤ ከእርሱም ጠጡ በማለት እኛ ከእርሱ ጋር አንድ የምንሆንበትን መንገድ ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ስያሜ ነው።
~ በዚህ ዕለት ቅዳሴ ይቀደሳል። የሚቀደሰውን በለሆሳስ /በዝግታ/ ሲሆን እንደ ቃጭል በመሆን የሚያገለግለውም ጽናጽል ነው። ይህም
አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ ሲመጡ ድምፃቸውን ዝግ አድርገው በለሆሳስ እየተነጋገሩ መምጣታቸውን ለማሰብ ነው።
~ በቅዳሴውም ኑዛዜ አይደረግም። ሥርአተ ቁርባን ግን ይፈጸምበታል። ይህም ጌታችን የሰጠውን ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ለማሰብ ነው። በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሀ ታጥቦ ተዘጋጅቶ ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ይኖርበታል።
4. የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።
ምክንያቱም መስዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንሰሳ ደም የሚቀርበው መስዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኀነቱ ዓለም ራሱን የተወደደ መስዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው። /ሉቃ 22:18-20/ ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው ደሜ የሚሆን የአዲስ ኪዳን ነው።

ከእርሱም ጠጡ በማለቱ ይታወቃል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘላለማዊ ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት መሆኑን በማሰብ የቃል ኪዳኑ ፈጻሚዎች ጠባቂዎች መሆን እንደሚገባን እንማራለን።

5. የነጻነት ሐሙስ ይባላል።
ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፤ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው። ራሱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጅ ነፃነት ሲናገር ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆቼ ግን ብያችኋለሁ በማለቱ /ዮሐ 15:15/
ከባርነት ነፃ የወጣንበት ቀን መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል። ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ከኃጢአት ባርነት በመራቅ ከእግዚአብሔር ሕይወቱን በቅድስና መምራት ይኖርበታል። እርሱ
ጠላቶቹ ስንሆን ወዳጆቹ አድርጎናል። /ማቴ 26:17-19/

6. አረንጓዴው ሐሙስ ይባላል።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአትክልት ቦታ ስለ ጸለየ።
@ethiopianorthodoxs
666 views06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 08:56:41 "ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ለእናንተ ያለኝ መውደድ፣ ለእናንተ ያለኝ ፍቅር የገለጽኩት መከራ መስቀልን በመቀበልም ነው እንጂ ብዙ ጸጋዎችን በመስጠት ብቻ አይደለም፡፡ ለእናንተ ስል ተተፋብኝ፡፡ ለእናንተ ስል ተገረፍኩኝ፡፡ ለእናንተ ስል አርአያ ገብርን ይዤ፣ ራሴን ባዶ አድርጌ [ክብሬንም እንደ መቀማት ሳልቆጥር] ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ ወደ እናንተ ወደምትጠሉኝ፣ ወደ እናንተ ፊታችሁን ከእኔ ወዳዞራችሁት፣ አዎ! ስም አጠራሬን እንኳን ለመስማት ወደ ተጠየፋችሁት ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ እፈልጋችሁ ዘንድ ከእኔ ርቃችሁ ወደ ኼዳችሁት ወደ እናንተ መጣሁ፤ አግኝቼ ከራሴ ጋር አዋሕዳችሁ ዘንድም እናንተን ተከትዬ ሮጥሁ፡፡ ፈልጌና አግኝቼም አልቀረሁ ከራሴ ጋር አዋሐድኳችሁ፡፡ ሥጋዬንና ደሜን ሰጥቼ ‘ብሉኝ ጠጡኝም’ አልኳችሁ፡፡ ባሕርያችሁን ከራሴ ጋር አዋሕጄ በዘባነ ኪሩብ ላይ አስቀመጥኩት፡፡ በታች በምድርም በሥጋዬና በደሜ ያዝኳችሁ፡፡ ሌላውስ ይቅርና፥ ከትንሣኤ ዘጉባኤ በኋላ እኔን መስላችሁ ለምትነሡት ትንሣኤ ባሕርያችሁን ይዤና በኵር ኾኜ መነሣቴ በቂ አይደለምን? ይህ እናንተን ደስ ለማሰኘት በቂ አይደለምን? ከሰማየ ሰማያት የወረድኩት ግን ባሕርያችሁን በመዋሐድ ብቻ ለማክበር አይደለም፤ ቅዱስ ሥጋዬን ክቡር ደሜን በመስጠት ከእናንተ ጋር ለማዋሐድም ጭምር ነው እንጂ፡፡ አዎ! የተፈተትኩት የተቆረስኩት የእኔና የእናንተ ትስስር፣ ውሕደትና አንድነት ይበልጥ ጽኑዕና ፍጹም እንዲኾን ለማድረግ ነው፡፡ የዚህ ዓለም ነገሮች ቢዋሐዱ ተዋሕዶአቸው ጽኑዕ ስላልኾነ ሚጠት አለበት፡፡ እኔ ግን ራሴን ከእናንተ ጋር ያዋሐድኩት እንደዚህ እንዲኾን አይደለም፡፡ ራሴን ከእናንተ ጋር ያዋሐድኩት፣ አንድ ያደረግኩት ተዋሕዶአችን ለዘለዓለም ጸንቶ እንዲኖር ነው፡፡”

ከኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ የተቀነጨበ

@ethiopianorthodoxs
722 views05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-12 09:01:51
የጌታችን መስቀል ኢራቅ ውስጥ እንዲህ በክብር ቆሟል አዲስ አበባ ላይ ግን...?
796 views06:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-07 07:54:47 “ምን ፍሬ አፈራን?”
በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ልጆቼ! እስኪ ፍቀዱልኝና ዛሬ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡፡ ብዙውን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ትመላለሳላችሁ፡፡ መልካም ነው፡፡ ግን ምን ለውጥ አመጣችሁ? ምን ፍሬ አፈራችሁ? ታገለግላላችሁን? ከአገልግሎታችሁ ምን ረብሕ አገኛችሁ?
ጥቅምን ካገኛችሁ በእውነት ምልልሳችሁ የጥበበኛ ምልልስ ነበር ማለት ነው፡፡ ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ወንጌላውያን እንዲህ እያስተማሩን ሳለ የማንለወጥ ከሆነ ግን የእስከ አሁን ምልልሳችን የአይሁድ ምልልስ ነበር ማለት ነው፡፡ አይሁዳውያን ሕገ ኦሪትን የተሰጠቻቸው ኃጢአታቸውን በእርሷ መስታወትነት አይተው ንስሐ እንዲገቡባት ነበር፡፡ እነርሱ ግን የንስሐ ፍሬ ሳያፈሩባት እንዲሁ ይመኩባት ነበር፡፡ ስለሆነም ለሕይወት የተሰጠቻቸው ሕግ ሞት ሆና አገኟት፡፡ እኛም እንዲህ ለኵነኔ ያይደለ ለጽድቅ የተሰጠችን ወንጌል ፍሬ የማናፈራበት ከሆነ ከአይሁዳውያን የባሰ ቅጣት ትፈርድብናለች፡፡

እስኪ ምሳሌ መስዬ ላስረዳችሁ፡፡ አንድ የሚታገል ሰው (wrestler) በየጊዜው ተጋጣሚውን እንደምን ማሸነፍ እንዳለበት ልምምድ የሚያደርግ ከሆነ ክህሎቱ ይዳብራል፡፡ ተጋጣሚውም በቀላሉ ማሸነፍ ይቻሏል፡፡ በየጊዜው ራሱን የሚያሻሽል (Update) የሚያደርግ ሐኪም ጐበዝ አዋቂና ሕመምተኞችን በአግባቡ የሚረዳ ይሆናል፡፡ በየቀኑ ቃሉ የሚነገረን እኛስ ምን ለውጥ አመጣን? ምን ፍሬ አፈራን?
እየተናገርኩ ያለሁት ለአንድ ዓመት ብቻ በቤተ ክርስቲያን የቆዩትን ምእመናን አይደለም፡፡ እየተናገርኩ ያለሁት ከልጅነታችን አንሥተን በቤቱ ለምንመላለስ እንጂ፡፡ ይህን ያህል ዘመን በቤቱ እየተመላለስን ፍሬ ካላፈራን ቤተ ክርስቲያን ደርሰን ብንመጣ ምን ጥቅም አለው? አባቶቻችን አብያተ ክርስቲያናት ያነጹልን ለምንድነው? ዝም ብለን እንድንሰባሰብ ነውን? እንደዚህማ በገበያ ቦታም መሰባሰብ አንችላለን፡፡ አበው አብያተ ክርስቲያናትን ያነጹለን ቃሉን እንድንማርበት፣ በተማርነው ቃልም የንስሐ ፍሬ እንድናፈራበት፣ ሥጋ ወደሙን እንድንቀበልበተ፣ እርስ በእርሳችን እንድንተራረምበት እንጂ ለሌላ ዓላማ አይደለም፡፡
ታዲያ ምን ፍሬ አፈራን? …
ራሳችንን አንጠይቅ

(ሰማዕትነት አያምልጣችሁ ገጽ 127-128 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ)
@ethiopianorthodoxs
855 views04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-02 07:59:16 ጾም

ጾም የመልካም ነገር ዋዜማና መጥቅዕ ስለ መሆኑ ሲናገር እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦

"የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሴትም በዓላት ይሆናል ስለዚህ እውነትንና ሰላምን ውደዱ።" ዘካ. 8:19

ጾም የአምልኮ መንገድ ነው። በአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን የነበሩበት ነቢያትና መምህራን ጌታን ካመለኩበት መንገድ አንዱ ጾም ነበር።

ይህንንም ቅዱስ መፅሐፍት እንዲህ ይናገራል፦ "እነዚህም ጌታን ሲያያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ። በዚያን ጊዜም ከጦሙ ከፀለዩም እጃቸውንም ከጫኑ በኋላ አሰናበቷቸው። የሐዋ. 13: 1-2

እንዲሁም ጾም ለእግዚአብሔር ከሚደረጉ አገልግሎቶች አንዱና ዋናው ነው።

ከአሴር ወገን የነበረችውና ሰማንያ አራት ዓመት በብቸኝነት በቤተ መቅደስ እግዚአብሔርን ስላገለገለች ስለ ነቢይቱ ሐና ሲናገር መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ አለ፦(በጾምና በፀሎትም ሌሊትና ቀን እያገለገለች ከመቅደስ አትለይም ነበር) ሉቃ. 2:37። የሐና አገልግሎት ጾምና ፀሎት ነበር።ምክንያቱም ጾም ታላቅ አገልግሎት ነውና።

ጾም አጋንንትን የሚያወጣቸው ርኩሳን መናፍስትን የምንዋጋበት የምናስወግድበት መሣሪያ ነው።

ውስጣችንን ተቆጣጥሮ በየመጠጡ ቤትና በየመሸታ ቤቱ በየጭፈራ ቤት አውሎ የሚያሳድረንን የመጠጥ መንፈስ የዝሙት የሌብነት በአጠቃላይም ክፉ መንፈስን ከውስጣችን የሚያወጣ ጾም ነው።

"አሳድጌ አሳድጌ አሁን የት ልሒድ" የሚል አጋንንት ፀበል ሰፀበልና መስቀል ሲታሽ የሚስቸግር ርኩስ መንፈስ የጾም ተጋድሎ ሲጨመርበት ድራሹ ይጠፋል።

ይንንም ጌታችን ደቀ መዛሙርቱ ማውጣት አቅቷቸው የነበረውን ጋኔን እርሱ ካወጣው በኋላ ወደ እርሱ ቀርበው "እኛ ልናወጣው ያልቻልን ስለ ምን ነው?" ብለው ሲጠይቁት "ይህ ወገን በፀሎትና በጦም ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም" አላቸው። ማር. 9:29

ታዲያ ምን እንላለን ከጌታ ቃል ሌላ ምስክር አናመጣም። በውስጣችን መቼም አንድ ደንቃራ ወይ ኮተት አይጠፋም ሰውም አይደለን! በጾም ድራሹን ማጥፋት እንደምንችል ጌታ ነግሮናልና።

ጾም ታላቅ የመንፈሳዊ ተጋድሎ መንገድ ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋለ ሥጋዌው የሥራው ሁሉ መጀመሪያ ጾምን ያደረገው ለዚሁ ነበር።

ቅዱስ ጳውሎስም የጌታውን አርአያ በመከተል "በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም" ይላል። 2ቆ. 11:27

ቅዱስ ጳውሎስ ከተጋደለባቸው ነገሮች አንዱ ጾም ነው። "ነገር በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን በብዙ መፅናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ በመገረፍ፥ በወኅኒ፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥ በመጦም፥ በንፅህና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ ግብዝነት በሌለው ፍቅር በእውነት ቃል ..." 2ቆሮ. 6: 4-6

በጾም የደከመ ሰውነት ንስሐ ለመግባት ቀዳሚ ነው። ንስሐና ፆም ሁለት ገፅታ አላቸው። በንስሐ ያለ ሁሌም በፆም፣ በፀሎት እና በስግደት የበረታ ነው።

አንድ ጿሚ ስለ ቀደሞ በደሉና ኃጢአቱ ፈጥኖ ይመለሳል። ሲራክ "በቁጣው ልክ ምሕረቱም የበዛ ነው" እንዳለ የጿሚ ተስፋው የእግዚአብሔር ምሕረት ብዙ ነው ብሎ ይደክማል።

ጿሚ በልቡ ጥርጣሬ የለበትም። ጌታችን፦ "በልቡ መጠራጠርን ያሰበ ቢኖር ይፀፀት፤ በሕሊናው አሳብ ዝሙት ያለበት አይቅረብ፤ በአሳቡ ድውይ የሆነ ቢኖር ይወገድ" በማለት ያወገዘውን ቃል ያስባል። እሱ ማለት ጿሚው እራሱን ለካህን አሳይቷልና።
@ethiopianorthodoxs
787 views04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ