Get Mystery Box with random crypto!

የጾም ትርጉም በቤተ ክርስቲያን የቤተ ክርስቲያናችን የሥርዓት መድብል የሆነው ፍትሐ ነገሥት ጾም | ለማርያም ክብር ገና እዘምራለሁ21

የጾም ትርጉም በቤተ ክርስቲያን

የቤተ ክርስቲያናችን የሥርዓት መድብል የሆነው ፍትሐ ነገሥት ጾምን እንዲህ ይተረጉመዋል፡-

ጾምስ በታወቀው ዕለት፣ በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ የሚከለከልበት መከልከል ነው፡፡

አንድም ጾም ሰውን ከምግብ መከልከል ነው፡፡

ይህም ኃጢአቱን ለማስተሰረይ፣ ዋጋውን ለማብዛት እርሱ ወዶ ፈቅዶ ሕግን ለሠራለት እየታዘዘ የፈቲውን ኃይል ያደክም ዘንድ ሥጋን ለነባቢት ነፍስ ትታዘዝ ዘንድ ማዘጋጀት ማብቃት ነው፡፡
ፍት.ነገ.ፍት. መ. አንቀጽ15፣564

በዚህ መሠረት ጾም ማለት ከጥሉላተ መባልዕት /ሥጋ ፣ ቅቤ፣ ወተት፣ እንቁላል እንዲሁም የአልኮል መጠጦች/ መታቀብ ነው፡፡

ጾም ከክፉ ሐሳብ፣ ከክፉ ሥራ ማሰብም መራቅም ነው።

ጾም እግርና እጅን፣ ልብንና ሕሊናን ከመጥፎ ቦታዎች ማቀብ /ወደ መጠጥ ቤት፣ ጭፈረና ዘፋኝ ቤት፣ ጥንቆላና ባዕድ አምልኮ ከመትወስድ መንገድ የምትከለክል ናት።

ጾም ከመንፈሳዊ ተጋድሎዎች አንዱ ነው፡፡

ጾም ለፈቃደ ሥጋም መንፈሳዊ ልጓም ነው፡፡

ጾም ሰው ፈቃደ ሥጋውን እየገታ ነፍሱን የሚያለመልምበት ስንቅ ነው፡፡

ጾም ቁስለ ነፍስን የምትፈውስ፣ ኃይለ ፍትወትን የምታደክም፣ የበጎ ምግባራት ሁሉ መጀመሪያ ናት።

ጾም ጸጋ እግዚአብሔርን የምታሰጥ፣ የጽሙዳን ክብራቸው፣ የድንግልና የንጽሕና ጌጣቸው መገለጫቸው፣ የጸሎት ምክንያት /እናት/፣ የእንባ መገኛ ምንጭ፣ አርምሞን የምታስተምር፣ ለበጎ ሥራ ሁሉ የምታነቃቃ፣ ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትኅትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒተ ነፍስ ናት፡፡
@ethiopianorthodoxs