Get Mystery Box with random crypto!

#ለሌሎች_መኖር_ስንጀምር_ህይወት_ውብ_ትሆናለች!! | የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ለሌሎች_መኖር_ስንጀምር_ህይወት_ውብ_ትሆናለች!!

ለራስህ መኖር ስትጀምር ጎበዝ ትባላለህ፥ ለሌሎች መኖር ከጀመርክ ግን ታላቅ ትሆናለህ!!

ህይወት የሚያምረው ለራስ በመኖር ብቻ ሳይሆን ለሰዎች መኖር ስንጀምር ነው። እጃችን የተፈጠረው ለመጉረስ ብቻ ሳይሆን ለማጉረስም ጭምር ነውና። ራስ ወዳድነት እና ብልጣብልጥነት በገነነት አለም ለሌሎች ስለ መኖር ማውራት ሞኝነት ቢመስልም መኖር ግን ያለው ለሌሎች በመኖር ውስጥ ነው። የአንዳችን መኖር ለአንዳችን እጅግ አስፈላጊ ነው። ለሌሎች መኖርን መቆረስን ያየነው ከክርስቶስ ህይወት ነው።

እግዚአብሔር በገንዘብ ሲባርከን ለሌሎች ማካፈል እንድትችል የበረከት ዕድል ሰቶናል ማለት ነው። ይህ ባሉን በሁሉም ባሉን ነገሮች ይሰራል። ትክክለኛውን በረከት የምናገኘው ለሌሎች በመኖር ጭምር ውስጥ ጭምር ነው።

“ሁለተኛይቱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም።”
— ማርቆስ 12፥31
..........
ዘሪሁን ግርማ

የቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ
https://t.me/theideaofs