Get Mystery Box with random crypto!

#ከመላመድ_መናናቅ_መጠበቅ!! ከሰው ጋር መቀራረብ አብሶ መስራት እና ይበልጥ መተዋወቅ እጅግ ጠቃ | የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ከመላመድ_መናናቅ_መጠበቅ!!

ከሰው ጋር መቀራረብ አብሶ መስራት እና ይበልጥ መተዋወቅ እጅግ ጠቃሚ ነው። ለሰው አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች መሐል ሰውን ማወቅ፥ አብሮ መስራት ህብረት ማድረግ ነው። ከሰው ጋር መስራት ደግሞ መላመድ የሚባልን ነገር ያመጣል። መላመድ በራሱ ችግር ባይኖረውም በመላመድ ውስጥ በጣም መቀራረብ አለና ያኔ ሰውየውን መሰልቸትና መናናቅ እንዳይመጣ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

'ሰዎች በጣም ስትቀርባቸው የሚንቁህ በጣም ስትርቅ የሚያከብሩህ' ምክንያቱ ሰትቀርባቸው አንተንና የአንተን ነገር ስለሚላመዱ እና መላመድ ደግሞ ሚዛናዊ ሰው ካልሆነ መናናቅና መሰላቸትን ስለሚያመጣ ነው። ይህን ለማወቅ ሰዎች በሩቅ ሲያውቁህ ስላንተ ያላቸው ግምት ከፍ ብሎ የነበረ ከነበረና እያገኙህ ሲመጡ ግን ከቀለልክባቸው እነዚህ አይነት ሰዎች የመላመድ በሽታ ውስጥ ናቸው።

መላመድ እጅግ ጥሩ ነው። እንደ በሰለ ሰው ከተጠቀምንበት ሰዎችን ለማወቅና ለመረዳት እና ለመርዳት ይጠቅማል። ማወቅ ያለንብን ቀረብ ብለን ስናየው ማንኛውም ሰው የራሱ የሆነ ክፍተት አለው። ወደ ማንኛውም ሰው ከመቅረባችን በፊት ስለ ሰዎች ያለንን 'የተጋነነ' አመለካከት ማስተካከል ከቀረብነው በኃላ በሚዛናዊነት መሔድ ያስፈልጋል። የመላመድ ሌላው ችግር በሰዎች ውስጥ ያለውን እቅም እንዳይቀበል ማድረጉ ነው።

ሰዎች ሌሎች ሰዎች እንዲቀርቧቸው የማይፈልጉ ብዙ ሰዎች አሉ። ምክንያቱ ደግሞ የመላመድ በሽታ የሚያመጣውን ችግር ስለማይፈልጉ ነው። ለበሰለ ሰው መላመድ የመፋቀር በር ነው። ሰውን በጣም ባወቅነው ቁጥር ልንወድው እንጂ እንድንንቀው አይገባም። ከሰዎች ጋር ያለ ልክ ተቀራርበህ እና ተላምደህ ከሚያሳዩህ ነገር የተነሳ ከመጣላት ተራርቆ ተዋዶ መኖር ሌላኛው አማራጭ ነው።

ዘሪሁን ግርማ

የቴሌግራም ቻናሌን ተቀላቀሉ
https://t.me/theideaofs