Get Mystery Box with random crypto!

#ንጽህና_ከጸሎት_ይቀድማል!! አንድ በቅርበት የማውቀው ወጣት አገልጋይ አለ ይህ ልጅ አባቱም አገ | የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ንጽህና_ከጸሎት_ይቀድማል!!

አንድ በቅርበት የማውቀው ወጣት አገልጋይ አለ ይህ ልጅ አባቱም አገልጋይ ናቸው። ልጁ በተደጋጋሚ ሲጸልይ ያዩታል። አንድ ቀን ልጃቸውን "ጸሎት ብቻ አታብዛ ህይወትህ ንጹህ እንዲሆን ትጋ" እንዳሉት አጫውቶኛል። በጸሎት ንጽህና እንደሚጠበቅ አምናለሁ። ከዛ በላይ ግን አኪያሄድን እንደ እግዚአብሔር ቃል በማድረግ ይጠበቃል። ጸሎት ለግልም ለአካሉም እጅግ አስፈላጊ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የብዙዎቻችን ጸሎት፣ የአንዳንዶቻችንን ይቅርታ፤ የብዙዎች ንስሃ ሳይ ጥያቄ ይፈጥርብኛል። ጸሎት በማብዛት ብቻ ህይወት አይጠራም እግዚአብሔር ራሱ የማይሰማው የጸሎት አይነትና ህይወት አለና።

የህይወታችን ንጽህና እንደ ቃሉ ብንሰራው ይቅርታችን የእውነት፤ንስሃችን የፍሬ ፤ ፍቅራችን ያለ ማስመሰል፤ አኗኗራችን ለጌታ ቢሆን ጸሎታችን ታላቅ አቅም ይኖረዋል። "በተሳሳተ መንገድ ላይ ቆመን የምናበዛው ጸሎት ለውጥ አያመጣም።" አቋቋማችንን፤ አረማመዳችን ማጥራት ለጸሎታችን ታላቅ ሐይልን ይሰጣል።

ጸሎታችን መንገዳችንን ከማስተካከል ጋር ቢሆን፤ ይቅርታ ስንጠያየቅ ከልባችን ቢሆን፣ ንስሃ ስንገባም ከመመለስ ጋር ቢሆን ለምድሪቱ ለቤተክርስቲያንም ታላቅ ለውጥ ይሆናል። ጸሎታችን ከእውነተኛ ልብ ጋር ቢሆን ፍሬያችን የበዛ ይሆናል።

ዘሪሁን ግርማ
የቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ!!
https://t.me/theideaofs