Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለሁላችሁም የእናቴ ልጆች እንደምን አላችሁ? #ይህ_የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረ_ገጽ_ነ | የካሌብ ጽሑፎች

ሰላም ለሁላችሁም የእናቴ ልጆች እንደምን አላችሁ? #ይህ_የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረ_ገጽ_ነው። መልካም ቆይታ

ከህይወት ብዙ ተምሬያለሁ

ብስለት የሚመጣው ከሚያጋጥሙን ተሞክሮዎች ዓይነት እና ከተሞክሮዎቹ ከቀሰምናቸው ትምህርቶች እንጅ ካከበርናቸው የልደት በዓሎች ብዛት እንዳልሆነ ተምሬያለሁ።

እንዳንዴ የቱንም ያህል ለሌሎች ብጨነቅ እና ግድ ብሰጥ አንዳንዴ አንዳንዶች በመልሱ ግድ ላይሰጡ እንደሚችሉ ተምሬያለሁ።

ቤተሰብ ሁልጊዜም መከታ ድጋፍ እንደማይሆን ተምሬያለሁ። ጓደኞች ምንም ያህል ጥሩ ቢሆን አልፎ አልፎ ማስቀየማቸው እንደማይቀር ተምሬያለሁ። ባስቀየምናቸው ሰዎች ይቅር መባል በቂ ያለመሆኑንና ራስንም ይቅር ማለትም እንደሚያስፈልግ ተምርያለሁ።

መታመንን ለመግንባት ዘመናት እንደሚያስፈልግ ፤ ለማውደም ግን ሰከንዶች ብቻ እንደሚበቁ ተምሬያለሁ።

አንዳንድ ጊዜ ተንሸራትተህ ስትወድቅ ይረጋግጡኛል ብለህ የምትጠብቃቸው እና የምትፈራቸው ሰዎች ብድግ አድርግው በማንሳት እንደሚያስገርሙህ ተምሬያለሁ።

በአስተዋይነት "እምቢ" ማለት ሁልጊዜም
የንፉግነት ምልክት ያለመሆኑን “እሺ” ማለትም ሁልጊዜ ምግባረ ሰናይነትን እንደማያሳይ ተገንዝቢያለሁ።

ራስን ከጥፋተኝነት ስሜት እንዲሁም ከጥላቻ የምንገላገልበት ብቸኛ መንገድም የአለፈውን ጊዜ ረስተን ከአሁን ጋር እርቅ ማድረግ ስንጀምር እንደሆነ ተምርያለው።

መልካም ምሽት! ቻናሉን ላልተቀላቀሉ አእምሮአዊያን ሰዎች ሁሉ በቅንነት ይጋብዙ

@TheHabesha0
@TheHabesha0
@TheHabesha0

እንደተለመደው ማንኛውንም ጥያቄና አስተያየታችሁን በ @Kalebo19King ላይ ብታደርሱኝ በተቻለኝ መጠን ለመመለስ እሞክራለሁ።