Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለሁላችሁም ውድ ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያውያት #የካሌብ_ጽሑፎች የቴሌግራም_ድህረገጽ_ቤተሰ | የካሌብ ጽሑፎች

ሰላም ለሁላችሁም ውድ ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያውያት #የካሌብ_ጽሑፎች የቴሌግራም_ድህረገጽ_ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ? እንዴትስ አመሻችሁ..!

<< አንድ ሕዝብ ወይም ማኅበረሰብ በጥቅሉ ፈሪ፣ ጠማማ፣ ሰነፍ፣ ገብጋባ ወይም ሌላ ሊባል አይችልም። እነዚህ ጠባዮች የግለሰብ ጠባይ ናቸው። ኅብረተሰብ ወይም ማኅበረሰብ የግለሰቦችን ጠንካራ ጠባይ በማቀናጀት ለተሻለ እሴትና ሞራል የተፈጠረ ተቋም ነው። በዚህ እድገቱ ከግለሰብ ላቅ ያለ ጠባያት ያሉት ነው። ስለሆነም አንድን ሕዝብ ወይም ሕብረተሰብ ፈሪ፣ ጠማማ፣ ገብጋባ፣ ማድረግ ኅብረተሰብ የዕድገት ውጤት መሆኑን አለመረዳት ነው። የማንኛውም ሕዝብ መገለጫ ጠንካራው የግለሰብ ጠባያት ናቸው። የግለሰብ ደካማ ጠባያት የሕዝብ ወደ መሆን ከተቀየረ ማኅበረሰቡ አርጅቷልና ፈርሶ መሰራት ይኖርበታል ማለት ነው።

በመሆኑም እንደ ታናሽና ታላቅ ወንድም ሲበላ ሲጠጣ የሚነገርን ተረብ ቁም ነገር አድርጎ የሕዝብ መለያ ጠባይ አድርጎ መውሰድ ማይምነት ነው። በሌላ በኩል እንዲህ ያለውን የወንድማማችነት ለከትን የፖለቲካ ካባ አልብሶ የብሔር ቁርሽ ማነሳሳት እጅግ አሳፋሪ ነው። ብሔርተኞች እንዲህ ያለውን ነገር ሲያገኙ የጭቆና ካባ አልብሰው ሕዝብን ሊያሰላልፉበት ይችላሉ። ብሔርተኝነት በሰፊ ሜዳ መሮጥ የማይችሉ ድኩማን የሚጠጉበት የጨለማ ዋሻ ነውና። >>



ምንጭ ፦ "መርበብት...ገጽ 149-150
ደራሲ ፦ ዶክተር አለማየሁ ዋሴ

፨ ከላይ ያሰፈርኳትን የመጽሐፍ ክፍል ባነበብኩ ቁጥር ሁሌም የማስታውሰው የኛን አገር የብሔር ማልያ ለብሰው የሚጫወቱ ድኩማንን ነው። እነሱ ለብቻቸው ቢሆኑ ወይም ብቻቸውን ቢጠፉ ችግር አልነበረውም ግን ብዙ ተከታይ መንጋዎች አሏቸው ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ እንዳለው "መንጋጋት እንጂ ማንጋት" የማይችሉ። የሚገርመው ደግሞ የነሱ ክፉ ሃሳቡ ከመልካሙ አተያይ በፈጠነ መልኩ መሰራጨቱ እና ሀይ ባይ ማጣቱ ነው። ምን ይደረግ እንግዲ አንድ በርሜል ውሃ በአንድ ብልቃጥ መርዝ አይደል የሚበከለው! ትንሽ ያልናቸው ድከማን ትንሽ ሃሳቦቻቸውን የሚሸከሙላቸው የአስተሳሰብ ወዛድሮች ከስራቸው እንደ አሸን ፈልተዋል አምላካችን እሱ በጎውን ዘመን መልካሙን ዘመን ያምጣልን እኔ በዚሁ አበቃሁ

ይህ #የካሌብ_ፅሁፎች ነው።

ስለመረጡን አክሮታችን ላቅ ያለ ነው! ቻናሉን ያልተቀላቀላችሁ ከታች አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ቀለም ልብ ቅርጽ መሀል ያለውን ሰማያዊ ሊንክን በመንካት #Join ያድርጉ ድህረገጹ አስተማሪ እና ቁምነገር አዘል ሆኖ ካገኙት ሌሎችም ይቀላቀሉን ዘንድ በቅንነት #Share #Forward በማድረግ አብረውን ይቀጥሉ

@TheHabesha0
@TheHabesha0
@TheHabesha0