Get Mystery Box with random crypto!

የምትሰሙትን ሰው ለይታችሁ እወቁ! አጭርና ግልጽ ምክር፡- ውጤቱን አብሯች በማይሸከም ሰው ወሬ፣ | ሚሥጢሩ(The Secret)

የምትሰሙትን ሰው ለይታችሁ እወቁ!

አጭርና ግልጽ ምክር፡- ውጤቱን አብሯች በማይሸከም ሰው ወሬ፣ ግፊትና አጉል ምክር ምክንያት አንድን ውሳኔ አትወስኑ፡፡

ከፋም ለማም፣ ሞላም ጎደለም፣ ተሳካም አልተሳካም ውጤቱን እናንተው የምትሸከሙትን የግል ውሳኔያችሁን መወሰን ያለባችሁ እናንተው ናችሁ፡፡

በተለይም የሕይወታችሁን አቅጣጫ እስከወዲያኛው የሚለውጥን ምርጫና ውሳኔ ስታደርጉ የማን ሃሳብና ምክር በሕይወታችሁ ስፍራ ሊያገኝ እንደሚገባው በሚገባ ለይታችሁ እወቁ፡፡ ምንም እንኳን ግራ በገባችሁ ጉዳይ ላይ መካሪ የመፈለጋችሁ ሁኔታ ትክክለኛ ሂደት ቢሆንም፣ ለምን አይነት ሰው ወሬና ግፊት ምላሽ ልትሰጡ እንደሚገባችሁ ግን ራሳችሁ ካላወቃችሁበት በኋላ የምትጸጸቱበትን አቅጣጫ ከመከተል አታመልጡም፡፡

ፍክት ያለ ቀን ይሁንላችሁ
@Abresh129
@the_law_of_attraction1