Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ቀን አንዲት አሮጊት ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘንድ መጣችና ያረሱለላህ አላህ ጀነት | አስ–ሱናህ

አንድ ቀን አንዲት አሮጊት ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘንድ መጣችና
ያረሱለላህ አላህ ጀነት ያስገባኝ ዘንድ ዱዓ አድርጉልኝ አለቻቸዉ
ረሱልም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የእገሌ እናት ሆይ....ጀነት ዉስጥ እኮ አሮጊቶች አይገቡም አሉዋት::
አሮጊትዋም የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ንግግር ሀሳቡ ስላልገባት ማልቀስን ያዘች ነብዩ ግን እየቀለዱባት ነበር::
እዉነቴን ነዉ ጀነት ዉስጥ አሮጊቶች የሉም አሮጊት ሴት ጀነት
የምትገባዉ በአሮጊትነትዋ ሳይሆን ወጣትና ዉብ ሆና ነዉ በማለት ገለፁላት::
በማስከተለም ስለ ጀነት ሴቶች በቁርዓን የተጠቀሰዉን
አነበቡላት:-"( إنا أنشأناهن إنشاء فجعلناهن أبكارا عربا أترابا)"
"እኛ አዲስ ፍጥረት አድርገን ፈጠርናቸዉ ደናግሎችም አደረግናቸዉ" ::
(ኢማሙ ቲርሚዚ ዘግቧል ኢማሙል አልባኒ ሐሰን ብለውታል

https://telegram.me/tewihd