Get Mystery Box with random crypto!

#የላሟ እና የአላህን ፈሪው ልጅ ታሪክ #የመጨረሻው ክፍል ሙሳም አለሂ ሰላም ልጁ | አስ–ሱናህ

#የላሟ እና የአላህን ፈሪው ልጅ ታሪክ
#የመጨረሻው ክፍል

ሙሳም አለሂ ሰላም ልጁን «ለምን አትሸጥላቸውም» ብለው ሲጠይቁት «መሸጥ ያለብኝ በዚህ ዋጋ ስለሆነ ነው»አላቸው ነብዩላህ ሙሳም «በዚህ ካልሆነ አልሸጥም ብሏል የሰውን ንብረት እኛ ካልሸጥክ ብለን ማስገደድ ስለማንችል በሚሸጥላችሁ ዋጋ መግዛት አለባችሁ» አሏቸው። ተንኮል አስበው የተወሰነ ቀብድ ሰጥተውት ሌላ ጊዜ እንሰጥሃለን ብለው በማታለል ጊደሯን ማረድ ፈለጉ። እንዲህም አሉት«የተወሰነ ገንዘብ እንስጥህና ግማሽ ከፍለን ግማሹን ሌላ ጊዜ እንሰጥሃለን አሁን ጊደሯን ሽጥልን የምትለውን ዋጋ በምትፈልገው ጊዜ ሞልተን እንከፍልሃለን እኛም ተቸግረን ነው ባለየን ሰው ገድላቹሃል ተብለን በወንጀል ተጠርጥረን ነፃነታችንን ማረጋገጥ ፈልገን ነውና ልትተባበረን ይገባል »አሉት።

ተንኮለኛ እና አታላይ ሰው ያለ ስለማይመስለው ያሉትን አምኖ ይሸጥላቸዋል። እናም ጊደሯን አርደው የሞተውን በድን ሲመቱት የተባለው በድን ሳይነሳ ሳይናገር ሲቀር ።ለነብዩላህ ሙሳ የሞተው ሰው ይነሳል ብለውን ነበር ያሉትን ብናደርግም ተነስቶ ሊናገር አልተቻለም ።አሏቸው
ነብዩላህ ሙሳ «ለመሆኑ የጊደሯን ዋጋ በሙሉ ከፍላቹሀልን» ዋጋውን ከፍላችሁ ካልጨረሳችሁ ሰውየው ተነስቶ አይናገርም ሲሏቸው በኒ እስራኤሎች ያለ የሌለ ሀብትና ንብረት እየሸጡና እለወጡ ወርቅ በመግዛት ቆዳውን እንሞላለን ብለው ቢጥሩም ሊሞላ አልቻለም ። ምክንያቱም እነሱ ወርቁን በጨመሩ ቁጥር ጅብሪል አለሂ ሰላም የጊደሯን ቆዳ እየተለጠጠ ይሰፋ ያደርገው ስለነበር። በኒ እስራኢሎች በዚህ ላይ እያሉ አንዲት ጧሪ ቀባሪ የሌላት በእድሜዋ የገፋች ሴት በአካባቢው ስለነበረች እሷ እንኳን ሳትቀር ለጊደሯ ዋጋ የሚከፈል ገንዘብ አምጪ ብለው ሲያስገድዷት ( ላኢላሀ ኢለላህ ሙሳ ረሱሉላህ) የሚል ፅሁፍ ያለበት የጣት ቀለበት በስተቀር ምንም ስላልነበራት የጣት ቀለበቷን ሰጠቻቸው ። በቀለበቱ ላይ የአላህ ስም ስለነበረበት ነበር የጊደሯ ቆዳ የሞላው።

እናም ዋጋውን በሙሉ ከከፈሉ ቡሀላ ነብዩላህ ሙሳ የተገደለውን በድን በከፊል ስጋዋ ሲመቱት ከሞት ተነስቶ «የገደለኝ የወንድሜ ልጅ ነው»ብሎ ሲያጋልጠው ። ተገድሎ ከስስታም አጎቱ ጋር ተቀበረ።
#በዋናነት የታሪኩ ሀሳብ በጥልቅ በቁርአን ውስጥ ሱረቱል በቀራ ላይ ከ67―73 ድረስ እንዲህ በማለት ገልፆታል
*
ﻗﺎﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ: } (ﻭَﺇِﺫْ ﻗَﺎﻝَ ﻣُﻮﺳَﻰ
ﻟِﻘَﻮْﻣِﻪِ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻳَﺄْﻣُﺮُﻛُﻢْ ﺃَﻥْ ﺗَﺬْﺑَﺤُﻮﺍ
ﺑَﻘَﺮَﺓً ﻗَﺎﻟُﻮﺍ ﺃَﺗَﺘَّﺨِﺬُﻧَﺎ ﻫُﺰُﻭًﺍ ﻗَﺎﻝَ ﺃَﻋُﻮﺫُ
ﺑِﺎﻟﻠَّﻪِ ﺃَﻥْ ﺃَﻛُﻮﻥَ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﺠَﺎﻫِﻠِﻴﻦَ * ﻗَﺎﻟُﻮﺍ
ﺍﺩْﻉُ ﻟَﻨَﺎ ﺭَﺑَّﻚَ ﻳُﺒَﻴِّﻦْ ﻟَﻨَﺎ ﻣَﺎ ﻫِﻲَ ﻗَﺎﻝَ
ﺇِﻧَّﻪُ ﻳَﻘُﻮﻝُ ﺇِﻧَّﻬَﺎ ﺑَﻘَﺮَﺓٌ ﻟَﺎ ﻓَﺎﺭِﺽٌ ﻭَﻟَﺎ
ﺑِﻜْﺮٌ ﻋَﻮَﺍﻥٌ ﺑَﻴْﻦَ ﺫَﻟِﻚَ ﻓَﺎﻓْﻌَﻠُﻮﺍ ﻣَﺎ
ﺗُﺆْﻣَﺮُﻭﻥَ * ﻗَﺎﻟُﻮﺍ ﺍﺩْﻉُ ﻟَﻨَﺎ ﺭَﺑَّﻚَ ﻳُﺒَﻴِّﻦْ
ﻟَﻨَﺎ ﻣَﺎ ﻟَﻮْﻧُﻬَﺎ ﻗَﺎﻝَ ﺇِﻧَّﻪُ ﻳَﻘُﻮﻝُ ﺇِﻧَّﻬَﺎ ﺑَﻘَﺮَﺓٌ
ﺻَﻔْﺮَﺍﺀُ ﻓَﺎﻗِﻊٌ ﻟَﻮْﻧُﻬَﺎ ﺗَﺴُﺮُّ
ﺍﻟﻨَّﺎﻇِﺮِﻳﻦَ * ﻗَﺎﻟُﻮﺍ ﺍﺩْﻉُ ﻟَﻨَﺎ ﺭَﺑَّﻚَ ﻳُﺒَﻴِّﻦْ
ﻟَﻨَﺎ ﻣَﺎ ﻫِﻲَ ﺇِﻥَّ ﺍﻟْﺒَﻘَﺮَ ﺗَﺸَﺎﺑَﻪَ ﻋَﻠَﻴْﻨَﺎ ﻭَﺇِﻧَّﺎ
ﺇِﻥْ ﺷَﺎﺀَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻟَﻤُﻬْﺘَﺪُﻭﻥَ * ﻗَﺎﻝَ ﺇِﻧَّﻪُ
ﻳَﻘُﻮﻝُ ﺇِﻧَّﻬَﺎ ﺑَﻘَﺮَﺓٌ ﻟَﺎ ﺫَﻟُﻮﻝٌ ﺗُﺜِﻴﺮُ ﺍﻟْﺄَﺭْﺽَ
ﻭَﻟَﺎ ﺗَﺴْﻘِﻲ ﺍﻟْﺤَﺮْﺙَ ﻣُﺴَﻠَّﻤَﺔٌ ﻟَﺎ ﺷِﻴَﺔَ
ﻓِﻴﻬَﺎ ﻗَﺎﻟُﻮﺍ ﺍﻟْﺂﻥَ ﺟِﺌْﺖَ ﺑِﺎﻟْﺤَﻖِّ ﻓَﺬَﺑَﺤُﻮﻫَﺎ
ﻭَﻣَﺎ ﻛَﺎﺩُﻭﺍ ﻳَﻔْﻌَﻠُﻮﻥَ * ﻭَﺇِﺫْ ﻗَﺘَﻠْﺘُﻢْ ﻧَﻔْﺴًﺎ
ﻓَﺎﺩَّﺍﺭَﺃْﺗُﻢْ ﻓِﻴﻬَﺎ ﻭَﺍﻟﻠَّﻪُ ﻣُﺨْﺮِﺝٌ ﻣَﺎ ﻛُﻨْﺘُﻢْ
ﺗَﻜْﺘُﻤُﻮﻥَ * ﻓَﻘُﻠْﻨَﺎ ﺍﺿْﺮِﺑُﻮﻩُ ﺑِﺒَﻌْﻀِﻬَﺎ
ﻛَﺬَﻟِﻚَ ﻳُﺤْﻲِ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺍﻟْﻤَﻮْﺗَﻰ ﻭَﻳُﺮِﻳﻜُﻢْ ﺁﻳَﺎﺗِﻪِ
ﻟَﻌَﻠَّﻜُﻢْ ﺗَﻌْﻘِﻠُﻮﻥ)
«ሙሳም ለሕዝቦቹ«አላህ ላምን እንድታርዱ ያዛችኋል»ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ «መሳለቂያ አድርገህ ትይዘናለህ?»አሉት «ከተሳላቂዎች ከመሆን በአላህ እጠበቃለው» አላቸው። «ለኛም ጌታህን ጠይቅልን እርሷ ምን እንደሆነች እድሜዋን ያብራራልን አሉ።ጊደር ናት ይላችኋል ፤ የታዘዛችሁትንም ስሩ» አላቸው። «ለኛ ጌታህን ጠይቅልን ፣እርሷ ምን እንደሆነች ይግለፅልን ከብቶች በኛ ላይ ተመሳሰሉብን።እኛም አላህ የሻ እንደሆነ በእርግጥ ተመሪዎች ነን»አሉ። እርሱ እርሷ ያልተገራች ምድርን «በማረስ»የማታስነሳ እርሻንም የማታጠጣ «ከነውር» የተጠበቀች ልዩ ምልክት የሌለባት ናት ይላችኋል»«አሁን በትክክል መጣህ»አሉ ሊሰሩ ያልተቃረቡ ሲሆኑ አረዷት።

ነፍስንም በገደላችሁና በርሷም «ገዳይ»በተከራከራችሁ ጊዜ «አስታወስ። አላህም ትደብቁት የነበራችሁትን ሁሉ ገላጭ ነው። «በድኑን በከፊሏም ምቱት»አልን እንደዚሁ አላህ ሙታንን ያስነሳል፤ታውቁም ዘንድ ታምራቶችን ያሳያችኋል» ሲል ሚስጥሩን በቁርአን ውስጥ በነዚህ አንቀፆች ገልፆታል ።


ታሪኩ አስተማሪ ነው ተጠቀሙበት

https://t.me/tewihd/