Get Mystery Box with random crypto!

በወር አበባ ወቅት መከልከል የሚገባው ከምን ከምንድን ነው? ክፍል ሁለት ➋ . #ከመጠመቅ | ተዋህዶ አንዲት ናት😍

በወር አበባ ወቅት መከልከል የሚገባው ከምን ከምንድን ነው?

ክፍል ሁለት


➋ . #ከመጠመቅ


ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ “#ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌ ሆኖ አሁን ያድነናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፡፡

ለእግዚአብሔር በጎ ህሊና ልመና ነው እንጂ” 1ኛ ጴጥ 3÷21 በማለት ተናግሯል፡፡

ስለዚህ ጥምቀት ስጋዊ እድፍን ማስወገጃ ስላልሆነ ከመጠመቅ በፊት #ተጣጥበው ከጠሩ በሗላ መጠመቅ ይገባል እንጂ ከእድፍ ጋር ለመጠመቅ መቅረብ ተገቢ አይደለም፡፡

ሌላው በዚህ በወር አበባ ወቅት ጸበሉን መጠጣት ይቻላል፤ እድፍን ማጥራት እንዳይሆን በሚል መጠመቅ ተከለከለ እንጂ መጠጣት አልተከለከለም፡፡


በነገራችን ላይ መጠመቅ ሲባል ለመጀመሪያ ጊዜ የሥላሴ ልጅነት ለሜገኝ ነው

ለእኛ ደሞ መፀበል ነው የሚባለው

ይቀጥላል

@tewahdo01
@tewahdo01
@tewahdo01