Get Mystery Box with random crypto!

ልጁ ያለው ህይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ህይወት የለውም 1ኛ ዮሐን.መ 5:12 ት | 🌹ትንሹ ሔኖክ

ልጁ ያለው ህይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ህይወት የለውም

1ኛ ዮሐን.መ 5:12

ትንሹ ሔኖክ

እንግዲህ የዚህ ዘመን ትውልድ ከእውነት መጣላቱ ሳያሳፍረው አይኑን አፍጥጦ በአደባባይ የክርስቶስን እናትን ለመሳደብ ሲወጣ ሳይ ልቤ እጅጉን ያለቅሳል። በርግጥ ይህ ዘመን ለምን እንዲ ሆነ ተብሎ የሚጠየቅበት አይዳለም። ማንም ለማንም የማይሆንበትና ራስን ለማዳን እንኳን የማይቻልና የማይፈቀድበት ዘመን ነው። ቤተሰቦቼ ሀይማኖቴን እንድቀይርና የገሀነቡን በር ከፍተው ሊያስገቡኝ በገንዘብ ድለላ በመናፍቃን የእባብ ምላስና በንግግር ሲያቅታቸው የመጨረሻ የሚሉትን በሰንሰለት ማሰርና ስም ማጥፋት መርጠው አድርገውታል። በቃ እናንተም የራሳችሁን ኑሩ እኔም ከእናቴ ከእመቤቴ መለየት አልፈልግም ብዬ በስርዓት ብነግራቸውም አበደ ማለትና በኔ ላይ ከመሳለቅ ውጭ ወደ ንሰሀና ወደ ትክክለኛው መንገድ መምጣቱን አልመረጡም። አለም እንዲህ ሆናለች ለመጠጥ ለብልግናና ለክፋት ስራ ገንዘብ የሚሰጡንና በለው በዪው የሚሉን ሰዎች ሁሉ ለመልካም ነገር ስንጠይቃቸውና ለነፍስ የሚበጀን ነገር ሲሆን ጠላታችን ይሆናሉ። ለማንኛውም ሰው ነን ብትሉም በጸሎት በስግደትና በመልካም ስራ በውስጣችሁ ያለውን ክፉ መንፈስ ማሸነፍ ባለመቻላችሁ ዳቢሎስ እንኳን የማያውቃቸውን ስራዎች እየሰራችሁ ወደ ገሀነብ ለመግባት እየሮጣችሁ ትኖራላችሁ። ለማንኛውም ወደ እናቴ ልመለስና በዚህ ቃል ውስጥ ልጁ ያለው ህይወት አለው ይላል። ልጁ ማን ነው ካልን ከአብ ዘንድ የተላከው ጌታችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ታድያ ልጁ ያለው ህይወት አለው ማለቱ ምን ማለት ነው ስንል። ሀዋርያት ክርስቶስ ከነሱ ጋር ስለነበር ሙታንን አስነስተዋል እውራንን አብርተዋል ሰዎችን ከሰይጣን እስራት ከደዌ በሽታ ነጻ አድርገው ህይወትን ሰጥተዋል። እንግዲህ ቁም ነገሩ ይሄ ነው። ሀዋርያት ክርስቶስን ያወቁት መቼ ነው?። ከሰላሳ አመቱ በኋላ ነው። ክርስቶስ ከዛ በኋላ የቆየው ሶስት አመት ከሶስት ወር ነው። በዚህች ጊዜ አውቀውት ይህን ሁሉ ተአምር አደረጉ። ጳውሎስ እንኳን ክርስቶስን አንገላቶ ሰቅሎት ነበር። ነገር ግን በንሰሀ ተመልሶ ድንቅን አድርጓል። ታድያ እናቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ልጁን መቼ አወቀችው ? ቃል ሆኖ በማህጸኗ የኖረ በጀርባዋ የተሸከመችው በእጆቿ አቅፋ ጡት አጥብታ ማንም ያላለውን ልጄ እያለች አሳድጋዋለች። ልጁ ያላት ሳይሆን ራሱ ልጇ ሆኖ እንዴት ከሀዋርያት በቢሊዮን እጥፍ አትበልጥም። ከሀዋርያት ብቻ ሳይሆን ከፍጥረት ሁሉ ትለያለች። ከሞት ታስነሳለች እውሩን ታበራለች ሽባውን ትፈውሳለች ያዘነውን ታጽናናለች የታሰረውን ትፈታለች የደከመውን ታበረታለች የጨነቀውን ታረጋጋለች የተራበውን ታጠግባለች ለቸገረው ትደርሳለች ለተናቀውና ለደካማው ምርኩዝ ጋሻ ትሆናለች። ይህ እንዴት ይሆናል ካልከኝ ከኔ ጋር በአካል ስንገናኝ በተግባር አሳይሀለው። ይህ የኔ ፍልስፍና ሳይሆን ዳቢሎስ በሀሰት ትምህርት የሸፈነው ግን በመጽፍ ቅዱስ ያለ እውነት ነው። አገልጋዮቻችን እውነቱን ገልጠው በጎችን ከመጠበቅ ይልቅ ከዳቢሎስ እየተመሳጠሩ ለጸብ ለተቃውሞና ለጬኸት ብቻ እየጠሩ ለሞት ሲዳርጓችሁ መኖራችሁ ያሳዝነኛል። እውነታው ይሄ ነው። ትውልዱ እናቴ ማርያምን እንዲጠላ ክብሯን እንዳያውቅና እንዳይድን በብዙ ብዙ መልኩ ወጥመድ በተዋህዶ ፍሬዎች ላይ ይዘረጋል። ደግሞ ብዙ ልጆቿ በወጥመዱ ተይዘዋል ዛሬም ወደ ወጥመዱ የሚገቡና የሚያዙ ሊወድቁ የተጋጁ ብዙ ናቸው። ግን እውነት እላችኋለሁ ይመስላል እንጂ ሰው ከእናቴ ከማርያም ተጣልቶ መኖርም ሆነ እሷ የመረጠችና የምትወዳቸው ልጆቿን ጫፍ እንኳን መንካት አይችልም። ጊዜው ደርሷል ልጆቿን ከተኩላ ነጥቃ ወደ ቤቷ ትሰበስባለች። የቤተ መቅደስ ተኩላዎችን ደግሞ ገርፋ አዋርዳ ታስወጣለች። ይህ ይሆን ዘንድ ቅርብም ግድም ነው። አይዞሽ ሀገሬ

ማርያም እናቴ ውድድድ ፍቅርርርርቅር የምታደርገኝ ትንሹ ሔኖክ ነኝ