Get Mystery Box with random crypto!

መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ ምሳ 31:29 | 🌹ትንሹ ሔኖክ

መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ
ምሳ 31:29

ትንሹ ሔኖክ

በነገራችን ላይ አንድ የምነግራችሁ እውነት ቢኖር ዘወትር እንዲህ ስለማርያም እናቴ ስጽፍና በግጥም ሳንበሸብሻችሁ በቤተክርስቲያን ያደግኩና በደንብ ስለ ድንግል ማርያም ሲነገረኝ ያደግኩ እንዳይመስላችሁ። እኔ ማርያምን እጅግ በሚጠሏት ጴንጤ የናቴ ቤተሰቦችና ልክ እንደ ብዙ ኢትዮጵያውያን በማስመሰልና በጥንቁላና ኦርቶዶክሳዊነት በርኩስ መንፈስ በተተበተቡ አባቴና የአባቴ ቤተሰቦች መሀከል ያደግኩ ጴንጤ ነበርኩ። ግን እንዲሁ ከመሬት ተነስቼ ዘወትር አምላኬን እፈልግ ድንግልንም አከብራት ነበር። እና ጊዜው ደርሶ ለብዙ ወዳጆቿና ለኛ ቅርብናት የሚሉ እውሮች ያላደለችውን ፍቅር እምነት ጽናት ጥበብና እውቀት ገልጣልኝ ይኸው አገለግልበት የነበረውን ትልቁ የመንግስት ኃላፊነት ስራዬን ለቅቄ በፍቅሯ ተማርኬ ላገለግላት ወስኜ መጥቼላችኋለሁ። በርግጥ ሰው እሷን አምኖ ምን ሆነ ሲባል ሰማችሁ። በርግጥ ለናንተ ለሁላችሁ አልመጣሁም እሷ ልቦናቸው መልካም የሆኑ ቅንና ደግ ሆነው ዳቢሎስ የሚፈትናቸውን ልጆቿን እንድሰበስብ ነው የመረጠችኝ። ለደቂቃም ቢሆን ክርክር ጭቅጭቅ አላደርግም። የተፈቀደለት በንሰሀ ይመለሳል የተፈረደበት ደግሞ ጥያቄ ላይ ጥያቄ እያነሳ ወደ ገሀነብ ይገባል። ትሰሙኛላችሁ ስሙኝ። ማርያምን ለመጥላት ከኔ የተሻለ እድል የነበረው ሰው አልነበረም። ግን ህሊናዬ ሊቀበለው አልቻለም ምክንያቱም የኔ ህሊና ከልጅነቴ ጀምሮ ያደገው በእውነት ነው። ማርያምን በማለቴ ከገዛ ወላጆቼ ጀምሮ ዳቢሎስ በርሀብ በመከራና ብዙ ከባድ ነገሮች እንደ ኳስ አንጥሮኛል ነገር ግን ፍቅሯን ጨመረልኝ እንጂ እንዳሰበው አልሆነም። በመጽሀፈ ምሳሌ ላይ ያለው ይህ ጥቅስ ከጊዜው ጋር እንመልከተው። አዎ ይህቺ ምድር ብዙ መልካምና ደግ ሴቶች ኖረውባታል። እነ አስቴር ኤልሳቤጥ እና ሌሎችም ታድያ ግን ለምን ማርያምን ከሁሉ ማለት አስፈለገ። እኛ በሰውኛ ኑሯችን እናት በቤት ውስጥ ልጆች ቢኖሯትም እጅግ አብልጣ የምታከብርና የምትወድ ጭንቀቷን የሚረዳ በሀሳብ በገንዘብ እንዲሁም ባለው ነገር ሁሉ የሚደግፋትን ልጅ ነው። ለምሳሌ እኔ በቤት ውስጥ ለናቴ እንዲሁም በሰፈሬ ለጎረቤቶቼ ወጣ ሲል ለአካባቢዬ በደንብ ሲወጣ ደግሞ በጎዳና ለሚኖሩ ቤተሰቦች ሁሉ ትክክለኛው ልጅ ነበርኩ። ታድያ ብዙ ሰዎች ከልጅነቴ ጀምሮ ኑሯቸውን ያማክሩኛል በጣምም ይወዱኛል። እንግዲህ እኔና አንድ የአካባቢውን ጎረምሳ እኩል አይመለከቱም። ይህን ልዩነት ያመጣው አንድ ነገር ነው። እሱም ምግባርና አስተሳሰብ። ነገውን የሚያስብና ዛሬን ብቻ የሚኖሩ ሰዎች ከሁለት አለም ናቸው። እንግዲህ በምድር የነበሩ መልካም የሚባሉ ሴቶች ሁሉ አሁንም በገነት ይኖራሉ ታድያ ማርያምን ከነዚህ ሴቶች ምን ለያት?። የመጀመሪያው በሀሳቧም ድንግል መሆኗ። ይህ ለማሰብም የሚከብድ ነው። ሁለተኛ ያለምንም ሀጥያት በንጽህና መገኘቷ። በቤተ መቅደስ ማደጓ። በመላዕክት ምገባ መኖሯ። በመላዕክት ብስራት መቀበሏ። ፈጣሪ ጌታዋን ያለ ወንድ መጽነሷ። ከማህጸን ጀምሮ ያለ ምንም ጥፋቷ ከሀገር ሀገር መንከራተቷ። የሰማይና የምድር ፈጣሪን በጀርባዋ አዝላ መራቧ መጠማቷ መጨነቋ። ፈጣሪ ጌታዋን ዘወትር ጉንጩን መሳሟ ጡት ማጥባቷ። መልካም በመናገሩና በማስተማሩ በሚደርስበት ዛቻና ነቀፋ ምን ያደርጉብኝ ይሆን እያለች መጨነቋ። ብዙ ስለሆነ ላሳጥረውና ያለምንም ሀጥያት አስረው ገርፈው በሚስማር ቸንክረው ሰቅለውት ልጇን በማየቷ። ስንመልሰው ደግሞ ለአዳም ለሔዋንና ለሰው ዘር በሙሉ መድሀኒት የሆነውን ክርስቶስን ለፍጥረት ሁሉ በማበርከቷ በርግጥም ድንግል እናቴ ከሴቶች ብቻ ሳይሆን ከፍጥረት ሁሉ ትበልጣለች። ይህ እኔ ሳልሆን ዳቢሎስ ራሱ አምኖ ተቀብሎ የሚኖረው የእውነቶች ሁሉ እውነት ነው። ዛሬም ነገም እስከለተ ሞቴ ስለ ድንግል ማርያም አማላጅነት ስለናንተ ከንቱዎች ስለምትሰሩት ክፋት ተንኮል የማስመሰልና የድፍረት ሀጥያት እንዲሁም ክርስቶስ ስለዘረጋላችሁ የመጨረሻ የምህረት እጅ አስተምራለሁ። ለኔ ከእናንተ ልትሰጡኝ የምትችሉት አንዲት ነገር የለም ጠፍታችኋልና በጾም በጸሎት በለቅሶና በስግደት ራሳችሁንና ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያን እንታደግ ዘንድ ተመለሱ እኔ በምድር ባለ ነገር ከተፈጥሮ ውጭ የሚያስደስተኝ አንድም ነገር የለም። ከሁሉም የሚልቀውና ዘወትር የሚያስገርመኝምና የሚያስደንቀኝ ግን የእናቴ የድንግል ማርያም እናትነት ፍቅርና ጸጋ በረከት ነው። ማርያሜ እኔ ትንሹ እንኳንም ያንቺ ሆንኩ። ለነገሩ ሌላ የማን ልሆን እችላለሁ። ከማህጸን ጀምሮ ለወደደኝና ከዳቢሎስ መንጋጋ ላወጣኝ ለልጅሽ ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ምስጋና የይሁን አሜን እንኳን የምንፍቅናውን ባዶ ህይወት በህጻንነቴ አሳየሺኝ እኔ ስለሚከተለኝ ስለሚያደምጠኝና ስለኔ ስለሚባል ነገር ምንም ግድ አይለኝም። ያየሁትን አይቻለሁና እውነቱን እናገራለሁ።

ማርያም እናቴ ውድድድድድ የምታደርገኝ ትንሹ ሔኖክ ነኝ