Get Mystery Box with random crypto!

ከኡስማን ወደ ገብረ ስላሴ ትንሹ ሔኖክ ወዳጄ እመቤት ስትወድህ እንዲህ ነው። ስንቱ አጠገቧ | 🌹ትንሹ ሔኖክ

ከኡስማን ወደ ገብረ ስላሴ

ትንሹ ሔኖክ

ወዳጄ እመቤት ስትወድህ እንዲህ ነው። ስንቱ አጠገቧ ሆኖ ጫቱን ሲያመነዥግ ስሟን እየጠራ በየመጠጥና ጭፈራ ቤት ሲያድርና አጉል ኦርቶዶክስ ነኝ እያለ ሲጠላላ ሲነታረክ ሲጨቃጨቅ። እሷ ከናይጄሪያ ልጇን አምጥታ በደጇ ጠምቃ ክርስትናን በደንብ አስተምራ ትሸኛለች። እናንተ ኢትዮጵያውያን ያላችሁን ሀብት የተሰጣችሁን ጸጋና ፍቅር ምንም አታወቁትም። ዝም ብላቹ በምላሳቹ ብቻ የምትድኑ ይመስላችኋል። ድንግል ማርያም ማንም የሚደግፋት ስለሷ የሚከራከር የሚጨቃጨቅና የሚገዳደል ሰው አትፈልግም። ምክንያቱም እሷ ለፍጥረት ሁሉ እናት ናት። ያወቀ ስርዓትን ይዞ በእምነት በትህትናና በጾም በጸሎት ተግቶ የሷን ምልጃ አስቀድሞ ይድናል። ዛሬ ከኡስማን ወደ ገብረ ስላሴ የተለወጠው ውድ ወንድሜ በአለማዊ ቋንቋ ናይጄሪያዊ ቢባልም በክርስትና እውነት የአንድ ዘር ሆነን የተገኝን ወንድሜ ነው። ክርስትናን አታውሩ ኑሩት። እናንተ ወሬአችሁ በዝቶ ነው የተቸገራችሁት። ከሚባለው በላይ በጣም ታወራላችሁ ግን በማህሌት ሰዓት ቤተ ክርስቲያን መቅደሷ ባዶ ናት በቅዳሴ ሰዓት ስጋ ወደሙ የሚወስዱ በቁጥር አንሞላም ለሊት ለጸበል የሚመጡ አብዛኛዎቹ ደካማ እናቶችና ህጻናት ናቸው። እናንተ ግን ለጸብ ለተቃውሞ ለመሰዳደብ ለንጽጽርና ለጩኸት ሲሆን ቤተ ክርስቲያንን ታጨናንቃላችሁ። ክርስትና ምን እንደሆነ ገና አልገባችሁም ሊገባችሁም አይችልም ምክንያቱም ወረኞች ናችሁ። መምህራኖቻችሁም አልገባቸውም። እስታዲየም ገብቶ ኳስ ለማየት ግሮሰሪ ለመቀመጥና በየ ሲኒማና ካፌ ተዘፍዝፋችሁ ጊዜኘችሁን ለማቃጠል የምትሮጡ ሆናችሁ ሳለ አምስት ደቂቃ ለመጸለይ ለመስገድና ነፍሳችሁን ለማዳን መቶ ምክንያት ትደረድራላችሁ። ለነገሩ ምን ታረጉት ተይዛችሁ ነው። እግዚአብሔር ይማራችሁ። እመቤቴ ትድረስላችሁ። ለማንኛውም ክርስትና የሚኖር እንጂ የሚወራ ህይወት አይደለም። አንደበት የሚሆነው ምግባር ነው

ማርያም እናቴ ውድድድድ የምታደርገኝ ትንሹ ሔኖክ ነኝ ወይይይ እንዴትኮ እንደምትወደኝ

ሀምሌ 2/2014 ዓ.ም
ጠዋት 3:00