2021-10-31 10:35:54
ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ !
ክፍል 15
.
.
#የመጨረሻ ክፍል
.
.
"ሰሞኑን ገንዘብ ከየት ነበር የምታመጪው?" እኔ አሁንም ዝም
"ዝምታ ካዋጣሽ እሺ" ብሎኝ ወደ መኝታ ቤታችን ገብቶ ተኛ። የሰውን ልጅ በድላችሁት ዝም
ከሚላችሁ ቢናገራችሁ ፣ ቢሰድባችሁ ፣ ቢመታችሁ ይሻላችኋል። ሶፋው ላይ በለሊት ብቻዬን ቁጭ
ብዬ የሲምቢሮዬ ሁኔታ አስጨነቀኝ። ያለ ልማዱ ዛሬ እንዴት ዝም ብሎኝ ሊተኛ ቻለ? እስከዛሬ
አንዳችን ባንዳችን ቅር ከተሰኘን ቁጭ ብለን ተነጋግረንበት ችግራችንን እንፈታው ነበር። ዛሬ በምን
ምክንያት ነው ዝም ብሎኝ ሊተኛ የቻለው? መቼም የሀበሻ አፍ ሰው ለማጣላት ሲሆን እንደ መርፌ
ይሾላልና አንዱ ጓደኛው አይቶኝ ነግሮት ይሆን እንዴ?.......አይ እሱ እንኳን አይሆንም ፤ ምክንያቱም
ቢዝነስ መስራት እንደጀመርኩኝ ቢያውቅ ሲጥ አድርጎ ይገድለኛል አሊያም አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ
ህሊናዬም ገላዬም ላይ የማይሽር ጠባሳ ጥሎብኝ ነበር የሚያልፈው!......እና ታዲያ ምን ሆንኩኝ
ብሎ ነው ፀባዩ እንደ ጠላ ቂጣ በድንገት የተገለባበጠው? ባዶ ግድግዳው ላይ ፍጥጥ ብዬ
ለሊቱን አነጋሁት። ያፈጠጥኩበት ግድግዳውም መልሶ አፈጠጠብኝ እንጂ ጭንቅላቴ መፍትሔ
አላገኘልኝም ነበር። እንደዚህ ብቻዬን መብሰልሰሌ ለውጥ እንደማያመጣ ስለገባኝ ወደ መኝታ
ቤታችን ለመሄድ ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ። እግሬ ግን እሱ የተኛበት መኝታ ቤት ለመሄድ ድፍረቱን
አጣ። ዓይኖቹን ማየት ፈራሁኝ። እንኳን ዓይኖቹን አይደለም። ከፊት ለፊቴ ግድግዳው ላይ
የተሰቀለውን የተሸጠው ታክሲያችን ላይ የተነሳነውን ፎቶ ራሱ ቀና ብዬ ለማየት ፈራሁኝ። ተመሌሼ
ተቀመጥኩ። እዛው ሶፋው ላይ ተኛሁ።
ጠዋት እንቅልፌን ሳልጨርስ ሶፋው ላይ የተኛሁበት ወገቤን እያመመኝ እየተጨናበስኩኝ ነቃሁ።
የመኝታ ቤቱም የቤቱም በር ክፍት ሆኖ አየሁት። ለአቢ ጡቴን ላጠባው ስገባ የተኛበት አልጋ
ሳይነጠፍ አንሶላውና ብርድልብሱ መሬት ወድቆ አገኘሁት። ሲጋራ ሊገዛ ወጥቶ ይሆናል ብዬ
ስላሰብኩኝ እስኪመጣ ድረስ ቁርስ እየሰራሁ ልጠብቀው ቦርሳዬን ሳየው ተዘረጋግፏል የወዳደቁትን
ዕቃዎች መልሼ እየከተትኳቸው እያለ ማታ የሸቀልኩትን ብር አጣሁት። ያኔ ነገሮች በስሱም ቢሆን
እየገቡኝ መጡ። በርግጠኝነት ማታ እዛ ሚሚ ቂጦ ቤት የሱ የግሉ ብቻ የሆነውን ሴትነቴን ለጨረታ
ሳቀርብ ሚስቱ መሆኔን የሚያውቀኝ ሰው አይቶኝ ነገሮት ነው አመሉ የተለዋወጠብኝ ብዬ
ደመደምኩኝ። አድርጎት የማያውቀውንስ ቤቱ ውስጥ ምንም የሚቀመስ ነገር እንደሌለ እያወቀ ብር
ሰርቆኝስ መሄዱ ለምን አስፈለገው?
አሁን ደግሞ አእምሮዬን አዲስ ጭንቀት ተቆጣጠረው። በኔ ምክንያት ተስፋ ቆርጦ ራሱን ሊጎዳ
ይሆን? 'ጌታ ሆይ እኔ ብበድልህም ባልበድልህም ቅጣት ብርቄ እንዳይሆን አድርገህ ነውና
የፈጠርከኝ እኔኑ እንደፍጥርጥርህ አድርገኝ እንጂ አደራ ባሌን ክፉ እንዳታስነካብኝ' ብዬ እያየኝ
ለማይመለከተኝ እየሰማኝ ለማያዳምጠኝ ፣ እውር አሞራን እየቀለበ እኔን ለዘነጋኝ አምላኬ
ነገርኩት። በሌላ በኩል ደግሞ የሱን ፀባይ እስከማውቀው ድረስ ከሆነ በሰው ተበድሎ ከደረሰበት
ጉዳት በላይ በዳዩን ሳይበቀለው እንቅልፍ እንደማይወስደው ነው። ታዲያ ሲምቢሮዬ በኔ ላይ
ጨክኖ ከሌላ ወንድ ጋር አደረች ብሎ ሊጎዳኝ አስቦ ይሆን?........አይ......አይ........ኧረ
አያደርገውም!
ጭንቅላቴ አንዱን ሀሳብ እያነሳ አንዱን ደግሞ እየጣለ ሰዓቴን ስመለከተው አስር ተኩል ሆኗል።
እስከአሁን ድረስ ባሌ ከፍቶ የወጣውን በር ከፍቶ ተመልሶ አልገባም። እኔ ደግሞ ትናንት ምሳ
የበላሁ እስከአሁን ምንም ስላልቀመስኩ ሆዴ በረሀብ ሻፈደ። ለልጄ እንደገና ደረቅ ጡቴን
አጎረስኩት። ሲምቢርዬ ማታ ገብቶለት መጥቶ ይሰድበኛል ይጠፈጥፈኛል እኔም ሀጢያቴ ስለሆነ
ዝም እለዋለሁ ብዬ ስላሰብኩኝ የሱ ነገር ቀስበቀስ የሚያሳስበኝ መጠን ቀነሰልኝ።
ሆዴ ግን በረሀብ እንደ ወፍጮ ቤት ሞተር ሲጮህ በምን ላስታግሰው? አፌን መረረኝ። ተነስቼ
የመቆም ሀይል እንኳን አጣሁኝ። ጨጓራዬ የሚፈጨው አጥቶ እርስ በርሱ ተፋትጎ ጉሮርዬ ላይ
ጣፋጭ የሚያቃጥል አሲድ መርጨት ጀመረ። እንደምንም አካሌ ሀይል በማጣት ዝሎ መሸልኝ።
ሰውዬዬ እስከምሽቱ አንድ ሰዓት ድረስ አልመጣም።
እኔ ረሀቤን እንደ ምንም ችዬ ተኳኩዬ ሚኒዬን አድርጌ የደላት ሴት መስዬ ልጄን አክሱም ሆቴል
ጀርባ ላለችው አሮጊት ሰጥቼ ሰው ሰውን እንደሸቀጥ ወደሚሸምትባት ቺቺንያ ራሴን ወርውሬ
ዳይቭ ሰመጥኩኝ። ረሀቤን ቢያስታግስልኝ ብዬ ከአመታት በኋላ ከአንዱ ጀብሎ ሲጋራ ዱቤ ወስጄ
አጨስኩኝ። እንኳን ሊያስታግስልኝ የባሰ አዙሮኝ ያለችኝንም አቅም አሟጠጠብኝ። ወደ መጠጥ
ቤቱ ውስጥ ስገባ እንጠጣ እንጂ እንብላ የሚል ቃል ካፋቸው የማይወጣ ወንዶች
'ሪታ....ሪች.....ሪ .....ሪሃና....' ብለው እየጠሩኝ መጠጥ ለመጋበዝ ተሻሙብኝ። ይሄኔ መጠጥ
ከምትጋብዙኝ ባለ ብር ከሀያ
ዳቦ ግዙልኝ ብላቸው ፊታቸው እንደ ቫምፓየር ባንዴ ነበር የሚቀያየረው። ያው ያለነው ኢትዮጵያ
ውስጥ አይደለ? ራበኝ ብለህ አደባባይ ስቶጣ ይሄን ብላ ተብለህ ጥይት የምትጎርሰበት ሀገር ላይ
ሰውም ራበኝ ስትለው መጠጥ ጋባዥ ቢሆን ያን ያህል አይገርምም። ምክንያቱም ሁሉም አመዳም
ኑሮውን ከማስታወስ መደንዘዝን ይመርጣልና! እኔም ምንም አማራጭ የለኝምና አንዱ የቀነዘረበት
የመሰለኝን እሺ ብዬው አንድ ቢራ ከጠጣሁኝ በኋላ መውጫ ቆርጦ ለሾርት ይዞኝ ሄደ። አመሻሽ
ላይ ስራዬን ጨርሼ ወደ ቤት ሄድኩ።
እቤት ስደርስ ብዙም ሳልቆይ በሬ ተንኳኳ። ከፈትኩት። የታክሲ ሹፌር የሆነው የሱ ጓደኛ ጨርቅ
እስከሚሆን ድረስ ስክር ብሎ ቆሟል። በዚህ ሰዓት ቤቴ መምጣቱ እያወዛገበኝ 'ታዴ በሰላም ነው?'
ስለው ገፍተር አድርጎኝ ወደ ውስጥ ገባና በሩን ከውስጥ ቆለፈው። ይባስ ብሎ ሶፋው ላይ ጣለኝና
አስገድዶ ሊደፍረኝ ይታገለኝ ጀመር። 'ታዴ ምን ሆነሀል ሪች እኮ ነኝ!?' ብዬ ከላዬ ላይ ላነሳው ስል
፣ በተሟዘዘ የሰካራም ድምፅ "እኔም'ኮ ለዛ ነው የመጣሁት" 'እሱ የለም ብለህ ነው አይደል እንዲህ
የምትሆነው! ከሰማ ግን የገባህበት ገብቶ ነው የሚዘለዝልህ!!' "ሃሃሃሃሃሃሃ....ሃሃ..ማ? ኤልያስ
ነ...ው የሚመታኝ?
ሃሃሃሃሃሃሃ...ሃሃሃሃ.....ራሱ አይደል እንዴ ሚስቴን ሀምሳ ብር ክፈለኝና አብራቹ ተኙ ያለኝ" ልክ
ይሄንን ቃል ሲናገር መቶ ሀያ ሺህ መርፌዎች አእምሮዬ ላይ የተሰኩብኝ መሰለኝ......አናቴን
በዲጂኖ የተቆፈርኩ ያህል የላይና የታቹ ተገለባበጠብኝ......መላ ሰውነቴን ንዝርዝር
አደረገኝ........በሀምሳ ብር ከባሌ የገዛኝ ታደሰ ልብሴን ለማውለቅ ይታገላል.......እኔ ልክ
እንደልጄ የስሜት ህዋሳቶቼ በድን ሆነውብኝ ወደ ግዑዝ አካልነት ተቀይሬያለሁ በርግጥ ሲምቢሮዬ
እንደሚበቀልኝ እጠብቅ ነበር ፤ ለሰራሁ ሀጢያት ግን ደመወዜን ይሄን ያህል እጥፍ አድርጎ
ይከፍለኛል ብዬ ግን ለአንዲት ሰከንድም አስቤ አላውቅም...
.
.
.
ተፈፀመ
ታሪኩ ይሄ ነበር...........
@terkagetm @terkagetm
624 views07:35