Get Mystery Box with random crypto!

ጥያቄ ሰላም ዶ/ር እርግዝና ላይ እግር የሚያብጥ በምን ምክንያት ነው? ሌላው የሚያብጥ ስንተኛ | TenaSeb - ጤና ሠብ

ጥያቄ
ሰላም ዶ/ር
እርግዝና ላይ እግር የሚያብጥ በምን ምክንያት ነው? ሌላው የሚያብጥ ስንተኛ ወሯ ላይ ነው? 4 ወሬን ጨርሸ 5ኛ ወሬን ይዣለሁ እና እግሬ አበጠ የሰላም ነው ወይ በዚህ ወር ላይ ማበጡ?

መልስ-
እግር ማበጥ ብዙን ጊዜ በእርግዝና ላይ ሊከሰት የሚችል ነገር ሲሆን ይህም የሚሆነው በሆድ ውስጥ ያለው ከታችኛው የእግሮችሽ ክፍል ደም የሚመልሰው የደም ቧንቧ በፅንሱ በተወሰነ መልኩ ሂደቱ ስለሚሰተጓጎል ደም እንደ በፊቱ ዘና ብሎ ወደ ልብ አይሄድም ፤ በዚህም ምክንያት እግር አካባቢ ደም ስለሚጠራቀም በዛ ምክንያት የእግር እብጠት በእርግዝና ጊዜ በተለይ ብዙ ቆመው እና ቁጭ ብለው የሚሰሩ ላይ የሚከሰት ነው።

ከመቼ ጀምሮ ይህ እብጠት ሊከሰት ይችላል ለሚለው ከእርጉዝ እርጉዝ ቢለያይም አንዳንዶች ላይ ከ 4 ወር ጀምሮ የሚከሰትበት ጊዜ አለ።

መጠንቀቅ ያለብሽ :- ከእግር ሌላ ፊት ፣ እጅ ላይ እብጠት ከጀመረ - የግፊት ምልክትም ሊሆን ስለሚችል ሀኪምሽን አማክሪ።
ዶ/ር ዳዊት (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)- https://t.me/DrDawitMOBGYN
***

TenaSeb - ጤና ሠብ
Youtube -http://shorturl.at/kDEP5
Telegram- https://t.me/tenaseb
TikTok - www.tiktok.com/@tenaseb
Telegram group - https://t.me/tenasebeth