Get Mystery Box with random crypto!

ተወዳጆች ሆይ Entrance Exam ላይ በየአመቱ ከዚህ part ላይ ፈተና ስለሚወጣበት ደጋግሜ ለ | University of Ethiopia

ተወዳጆች ሆይ Entrance Exam ላይ በየአመቱ ከዚህ part ላይ ፈተና ስለሚወጣበት ደጋግሜ ለቀቁላችሁ። እንዳትሰላቹ ።


Future Perfect Tense
_________________

Affirmative form
Sub + will + have + V3.

Negative form
Sub + will not + have + V3.

Question form
Will + Sub + have + V3?

Usage

#1) to talk about an event that will be finished and complete before a specified time in the future.

ከተገለፀው ወይም ከተጠቀሰው ጊዜ በፊት የሚከናወን የወደፊት ድርጊትን ለመግለፅ - ማለትም ወደፊት ወይም future ላይ የሚከናወን አንድ ድርጊት አለ ፡ ታድያ ይህ ወደፊት የሚከናወነዉ ድርጊት ከ ተጠቀሰው ጊዜ በፊት አስቀድሞ የሚከናወን ከሆነ ፡ ይህ ከተጠቀሰው ጊዜ በፊት አስቀድሞ፡ future ላይ ወይም ወደፊት የሚከናወነው ድርጊት በ future perfect ይገለፃል ማለት ነው። ስለዚህ ሁለት ሀሳቦችን መረዳት አለብን።

ሀሳብ 1 -- የተጠቀሰው ወይም የተገለፀው ጊዜ(specified time).
ምሳሌ ከ 2021 በፊት÷ ቀጣይ ሳምንት እህን ጊዜ፡ ከማግባቴ በፊት ወዘተ።

ሀሳብ 2: ወደፊት ወይም future ላይ የሚከናወነው ድርጊት።

ስለዚህ ከተጠቀሰው ወይም ከተገለፀው ጊዜ በፊት አስቀድሞ: future ላይ ወይም ወደፊት የሚከናወነውን ድርጊት ለመግለፅ future perfect ን እንጠቀማለን ማለት ነው። ምሳሌዎችን እንመልከት፡

ምሳሌ 1-- መምህራችሁ assignment ዛሬ ሰጣችሁ፡ ከዛ ከነገ ጀምረህ እየሰራህ እስከ ሰኞ መጨረስ አሰብክ። ከዛ ጓደኛህ አሳይመንቱን መቼ ትጨርሳለህ ብሎ ሲጠይቅህ ከሰኞ በፊት እጨርሳለሁ አልከው። ስለዚህ

ሀሳብ 1: የተገለፀው ወይም የተጠቀሰው ጊዜ ማለትም ከሰኞ በፊት።

ሀሳብ 2: future ላይ ወይም ወደፊት የሚከናወነው ድርጊት፡ እርሱም ነገ፡ ነገወድያ ምናምን አሳይመንት ሰርቶ መጨረስ።
ስለዚህ አሳይመንት ሰርቶ መጨረስ ወደፊት የሚከናወን ድርጊት ነው፡ ታድያ ይህ ድርጊት ከተገለፀው ጊዜ በፊት ማለትም ከሰኞ በፊት የሚከናወን ድርጊት ስለሆነ future perfect እንጠቀማለን ማለት ነው።

I will have finished the assignment by monday.(by means before.) ከሰኞ በፊት አሳይመንቱን ሰርቼ እጨርሳለሁ።

ምሳሌ2: አሁን ላይ አንተ የድግሪ ወይም ቅድመ ምረቃ ተማሪ ነህ፡ ገና አላገባህም። እናም ከማግባትህ በፊት ማስትሬት ድግሪ የመስራት ሀሳብ አለህ ወይም እሰራለሁ ብለሀል። ስለዚህ ሁለት ሀሳቦችን ልንረዳ ይገባል።

ሀሳብ 1: የተጠቀሰው ጊዜ ማለትም ከ ማግባትህ በፊት።

ሀሳብ 2: ወደፊት ወይም future ላይ የሚከናወነው ድርጊት ፡ ማለትም ማስትሬት መስራትህ።

ስለዚህ ማስትሬትህን መስራት ወደፊት የሚከናወን ድርጊት ነው። ታድያ ይህ ወደፊት የሚከናወነው ድርጊት ከተጠቀሰው ጊዜ በፊት ማለትም ከማግባትህ በፊት የሚከናወን ነው፡ ስለዚህ ከተጠቀሰው ጊዜ በፊት የሚከናወነውን ይኸን ድርጊት በ future perfect እንገልፀዋለን ማለት ነው።

By the time I get married, I will have made M.SC degree in Ecology.(ከማግባቴ በፊት በ Ecology የማስትሬት ድግሪ እሰራለሁ።)

I will have made M.Sc degree in Ecology by the time I get married.( ከማግባቴ በፊት በ Ecology የማስትሬት ድግሪ እሰራለሁ።)

ሁለቱም ምሳሌዎች possible ናቸው። 'by' ማለት 'before' እንደማለት ነው።

#2) to make prediction about future event that will be complete before a specified future time.(ከተጠቀሰው ጊዜ በፊት ፡ ይከናወናል ወይም አይከናወንም ተብሎ የተተነበዬን ድርጊት ለመግለፅ።) ሁለት ሀሳቦችን ልንረዳ ይገባል።

ሀሳብ 1: የተጠቀሰው ወይም የተገለፀው ጊዜ።

ሀሳብ 2: ወደፊት ወይም future ላይ ይከናወናል ወይም አይከናወንም ተብሎ የተተነበዬ ድርጊት።

ስለዚህ ከተገለፀው ወይም ከተጠቀሰው ጊዜ በፊት ይከናወናል ወይም አይከናወንም ተብሎ የተተነበየውን የወደፊት ድርጊት ለመግለፅ፡ future perfect ን እንጠቀማለን ማለት ነው።

ምሳሌ፡ በአሁኑ ሰአት የ corona virus መድሓኒት አልተገኘለትም። እናም አንተ ሳይንቲስቶች መድሀኒቱን ከ 2022 በፊት ያገኙታል ብለህ ተነበይክ። ስለዚህ ሁለት ሀሳቦችን እንረዳ፡

ሀሳብ 1: የተጠቀሰው ጊዜ ማለትም ከ 2022 በፊት።

ሀሳብ 2: ወደፊት ይከናወናል ብለህ የተነበይከው ድርጊት፡ እርሱም የኮሮና መድሐኒትን ሳይንቲስቶች ማግኘት።

ስለዚህ ወደፊት ይከናወናል ብለህ የተነበይከው ድርጊት ማለትም ሳይንቲስቶች የኮሮና መድሐኒት ማግኘት ከተጠቀሰው ጊዜ በፊት ማለትም ከ 2022 በፊት ይከናወናል ወይም ይደረጋል ብለህ ስለተነበይክ future perfect ን ትጠቀማለህ።

Scientists will have discovered the cure for corona virus by the year 2022.(ከ2022 በፊት ሳይንቲስቶች የኮሮና መድኒትህን ያገኛሉ።)

ነገር ግን 2022 ላይ ሳይንቲስቶች የኮሮና መድሐኒት ያገኛሉ ብለህ ከተነበይክ ወይም predict ካደረክ future perfect ን ሳይሆን simple future ን ነው የምንጠቀመው። ልዩነቱ፡

Scientists will have discovered the cure for corona virus by the year 2022.( ሳይንቲስቶች ከ 2022 በፊት የኮሮና መድሐኒትን ያገኛሉ።)

Scientists will discover the cure for corona virus in 2022.(ሳይንቲስቶች 2022 ላይ የኮረና መድሐኒትን ያገኛሉ።)

ማስታወሻ -- Entrance Exam ላይ በየአመቱ future perfect ን የተመለከቱ ጥያቄዎች ስለሚወጡ፡ በደንብ ልንረዳው ይገባል።

join and share

@Temihert