ይድረስ ..ለማይደርስልን መንግስት ። ። እንደምነህ መንግስት ፥ እኛ አለን በደህና ባመቻቸህልን ፥ የለውጥ ጎዳና ሺዎችን ገብረን ፣ ለአንድ ብልፅግና ከሶስት አመት በላይ እየተሰበርን ፣ " ሰበር" በሚል ዜና ተራ እየጠበቅን ፣ ለሞት ተሰልፈን ግፍኛን ተቃውመን ፣ ግፈኛን ደግፈን ደብዳቤ እየላክን ፣ በደማችን ፅፈን እኛ አለን በስጋት ፣ እኛ አለን በተድላ በቀን ሶስት ግዜ ቁርስ ምሳና ራት ፣ መከራ ስንበላ አንተ ግን እንዴት ነህ? እንደምነህልን ፣ ካልንህስ በኋላ?! እኛ አለን በድሎት እኛ አለን በፀሎት ከገዳያችን ጋር ፣ ቀብር ስናስፈጥም ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ምን እንደሆንን ፣ ባናረጋግጥም እኛ አለን በተአምር ፣ እኛ አለን በደህና እየተገደልን "ስልታዊ ማፈግፈግ" ፣ በሚል ፍልስፍና አንተ ግን እንዴት ነህ? እልፎች ሚቃወሙህ ፣ እልፎች ሚደግፉህ እልፎች ሚያወድሱህ ፣ እልፎች የሚነቅፉህ እንዴት ነው መንግስትህ ከአዲስ ምእራፍ ጋር ፣ የተመሰረተው? አንድ አንተን ለማፅናት ፣ ስንቶች ነን ምንሞተው? #ሼርርር @tebasemidea @tebasemidea @tebasemidea 1.0K views ☞net, 12:14