2022-11-13 23:26:27
☞ወር በገባ በ4 የጻድቁ አባታችን የአቡነ ሙሴ(ዘዲባ) ወርሐዊ መታሰቢያቸው
ነው፡፡
☞አቡነ ሙሴ ዘድባ የትውልድ አገራቸው እስራኤል ልዩ ቦታው ቃና ዘገሊላ ነው፡፡
☞ወደ ግብፅም መጥተው በታላቅ ተጋድሎና በንግሥና ኖረው እንደ ሄኖክና
ኤልያስ በምድር ላይ ሳይሞቱ በሞት ፋንታ የተሰወሩ አባት ናቸው፡፡
☞ብፁዓዊ አቡነ ሙሴ በአባታቸው የእመቤታችን ጠባቂ የሆነው የአረጋዊው
የቅዱስ ዮሴፍ የልጅ ልጅ ሲሆኑ ፡፡
☞በእናታቸው በኩል ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ጋር በቃና ዘገሊላ ሰንግ
የተገኙበት የዮካን ልጅ የዶኪማስ ልጅ ናቸው፡፡
☞የአባታቸው ስም ቅዱስ ዮስጦስ ሲባል የእናታቸው ስም ጵርስቅላ ይባላል፡፡
☞ሁለቱም መካኖች ሆነው ከኖሩ በኃላ በቅዱስ ገብርኤል አብሣሪነት ታህሳስ 8
አቡነ ሙሴ ተወለዱ፡፡
☞በዚህች ቀን ከእናታቸው እቅፍ በመውረድ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
ምስጋና ይሁን ከጨለማ ወደ ብርሃን ላወጣህኝ አምላክ ብሎ ፈጣሪያቸውን
አመግነዋል፡፡
☞40 ቀናቸው ሐዋርያ ጴጥሮስና ያዕቆብ ፊሊጲስ እንድርያስ ሆነው ጥር 17ቀን
ክርስትና አነሷቸው፡፡
☞ወላጆቻቸው ለቤተክርስቲያን ሰጧቸው ቅዱስ ፋኑኤል ቅዱስ ዮናኤልም
ሰማያዊ ኅብስት እያመጡ ይመግቧቸው ነበር፡፡
☞ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ የቤተክርስቲያን ትምህርት አስተምሮ ድቁና
የሾማቸው፡፡
☞ብፁዓዊ አቡነ ሙሴ ወገባቸውን ከጠጉር በተሠራ መታጠቂያ በመታጠቅ
አቡነ ዘበሰማያት በጀመሩ ጊዜ ሰባቱ ሰማያት ተከፍቶላቸው ከአጋዕዝተ ዓለም
ሥላሴ ጀምሮ ሁሉንም ቅዱሳን በግልፅ ያያሉ ፡፡
☞በግብፅ 40 ዘመን ነግሠው ሳለ ንግሥናቸውን ትተው በመመንኮስ እልፍ
መነኮሳትን አስከትለው ወደ ሀገራችን ኢትያጵያ መጥተው እንደ ላሊበላ ያሉ 16
አሰደናቂ ፍልፍል ቤተ መቅደሶችን አንጸዋል፡፡
☞ወደ ኢትያጵያ ይዘው ከመጡት ብዙ መጻሕፍትም ብዙዎቹን ከአረብኛ ቋንቋ
ወደ ግእዝ ቋንቋ ተርጉመው ጽፈዋል፡፡
☞በአጠቃላይ በመላው ዓለም ዐሥር ሺህ ቤተክርስቲያን በኢትያጵያ ከአምስት
መቶ በላይ የዋሻ የሕንጻ ቤተክርስቲያን ሠርተዋል፡፡
☞በአቡነ ሙሴ በኢትዮጵያ ከታነጹ የዋሻ ቤተ መቅደሶች ውስጥ የድባ መቅደስ
ማርያም አቡነ ሙሴ አንድነት ገዳም አንዱ ነው፡፡ የዚህ ገዳም መሥራች
ብፁዓዊ አቡነ ሙሴ ናቸው፡፡
☞ጻድቁ የድባ መቅደስ ማርያም ሲደርሱ ድባ የምትባል አውሬ ያገኛሉ ልክ
እንደሰው አውርተው ይህ ቦታሽ አይደለም ሲሏት ቦታውን ትታ ወጥታ ሄደች
የቦታው ሥያሜም ያገኘው ከዚህ አንጻር ነው፡፡
☞የቤተ መቅደሱን የዋሻ ቤተክርስቲያን መስከረም 20 ቀን በሦስት ሰዓት
ውስጥ ተሠርቶ ተጠናቆ መስከረም 21 ቀን ሥሉስ ቅዱስ ባርከውላቸው
ተቀድሷል፡፡
☞በዚሁ ገዳም ውስጥ አባታችን ከጌታችን ቃል ኪዳን ከተቀበሉ በኀላ
መስከረም 4ቀን ተሰውረዋል፡፡
☞ይህ የጻድቁ አባታችን ከዳም ከተመሠረተ ከአንድ ሺህ ስድስት መቶ ዕድሜ
በላይ ያስቆጠረ ሲሆን በዚህ ዋሻውጥ የጻድቁ አባታችን የአቡነ ሙሴ የእጅ
መስቀላቸው በትረ ሙሴአቸው፤ ጥንታዊ የብራና መጻሐፍት ይገኛሉ፡፡
☞ጻድቁ አቡነ ሙሴ በኢትዮጵያ ካነጿቸው ውስጥ☞ ዋሻ ማርቆስ ከመቅደሱ
ጸበል የሚቀዳ(መቄት) ፤ደብረ ናዙኝ ማርያም (መቄት)፤ አዲስ አምባ
መድኃኒዓለም(መቄት)፤ ዶቃ ደብረ ሲና ሚካኤል (ደቡብ ዉሎ ማሻ ወረዳ) ፤
ወልደ ነጓድጓድ ቅድስ ዮሐንስ(ዋድላ) ፤ጠርጠሪያት ቁስቋም ማርያም( ሰሜን
ወሎ ዳውንት)፤ አርባዕቱ እንስሳ (ሰሜን ወሎ ዳውንት) ውቅሮ ቅዱስ ጊዮርጊስ
(ጋይንት) ከብዙ በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
☞ጸሎቱና በረከቱ ከእኛ ጋር ይሁንና ብፁዓዊ አቡነ ሙሴ ያደረገው ተአምር ይህ
ነው፡፡ ጸሎቱና በረከቱ ከሁላችን ጋር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
☞በአንዲት ዕለት እንዲህ ሆነ በአባታችን በአቡነ ሙሴ መቃብር ቦታ ከዕለታት
በአንድ ቀን ከላዩ ከቤተ ክርስቲያኑ ከዋሻው ተልጦ ትልቅ ድንጋይ ወረደ፡፡
☞የጻድቁን ዝክር የሚዘክሩበት አንድ ቤተ በቤተክርስቲያኑ ስር ነበር፡፡
በውስጡም ለአቡነ ሙሴ የበዓል ዝክር የተጠመቀ በጋን የሞላ ጠላ ነበር፡፡
☞ድንጋዩም ከላይ ወርዶ ቤቱን ሁሉ አፈረሰው፡፡ ለበዓሉ መታሰቢያ ያዘጋጁበትን
ጋኑ ግን ለምልክት ይሆን ዘንድ ጆሮውን ከመሽረፋ በስተቀር አልተሰበረም፡፡
☞ያ ታላቅ አዳራሽ የሚያህል ቋጥኝ ድንጋይ በሱ ላይ አርፎ እሱንም አብሮ
በሰበረው ነበር ተአምምራቱ ለመግለጽ ነው እንጂ፡፡
☞ይልቁንም በውስጡ ያለው ጠላ ሳይፈስና ጋኑም ሳይሰበር መገኘቱ ለአባ
ሙሴ ለተአምራት ነው እንጂ አንዲት የእሳት መጫሪያ ገልስ እንኳ ባልተገኘም
ሰብሮ አፈር ትቢያ ባደረገው ነበር፡፡
☞በአባ ሙሴ በተአምራቱ ኃይል አዳነው እንጂ፡፡
☞የአቡነ ሙሴ ጸሎቱና በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን፡፡
☞(ገድለ አቡነ ሙሴ)
10 views20:26